Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4071
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የ ገበሬውን በሬ አርዶ ሊበላ ያሰፈሰፈው ረሃብተኛ ወራሪ ሽፍታ፥ በአየር ሃይል አመድ ሆነ፥

Post by Za-Ilmaknun » 22 Oct 2021, 14:54

:mrgreen: :lol: :x

የውሎ ሪፖርት
አሳዬ ደርቤ
➖➖
⓵ ወረባቦ ጎሃ ትምህርት ቤት አካባቢ የአርሶ አደሩን በሬ አርዶ ጥብስ ለመብላት ሲዘገጃጅ የነበረው አሸባሪ አየር ሃይላችን በወረወረው መብረቅ ገላው ተጠባብሶ እንዳይሆኑ ሆኗል!

⓶ ወሎን ሊዘርፍ በ22 ተሳቢ ተጭኖ የመጣው አሸባሪም መኪናው ላይ ታጭቆ የሚዘርፈውን የሐይቅ ከተማ አሻግሮ እያዬ ሳለ አየር ሃይላችን ከሰማይ በደፋበት እሳት ከመኪናው ሳይወርድ ተረፍርፏል፡፡

⓷ ወደ ደሴ ለመግባት አስቦ በቦሩ በኩል ወረራ የፈጸመው ጉጅሌ በጀግኖቹ ክንድ ተደቁሶ ደሴን ለመቆጣጠር እንደናፈቀ ወደ መቃብር ተሸኝቷል፡፡

⓸በአፋርና በአማራ በኩል ወረራ ፈጽሞ እልፍ አእላፍ ጓዶቹን የተጠነቀው ትርፍራፊ ጦር የአዛዦቹን ትዕዛዝ ተቀብሎ ወደ መቃብር በመውረድ ፈንታ ‹‹ሞት በቃኝ›› ብሎ አፈሙዙን ወደ አለቆቹ ማዞር ጀምሯል፡፡

⓹መቀሌ ላይ ተቀምጠው የሰማይ አሞራ ሳይቀር የሚያስበረግጋቸውና ህልማቸው መክሸፉን የተረዱት የአሸባሪው ቡድን መሪዎችም አሁን ከመሼ ‹‹አሸንፈናል›› በሚል ፉከራ ጀምሮ ‹‹ታደጉን›› በሚል ልመና የሚጠናቀቅ መግለጫ ለማውጣት ተገድደዋል፡፡
‹‹ማርከን እና ገድለን›› በሚል የድል ዜና የሚጀምር መግለጫቸውን ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ሽንፈት የተጎነጨ መንግሥትህን በቃህ ብለህ አስጥለን›› በሚል ልመና የሚደመድም መግለጫቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በወገን በኩል ደግሞ…

➖ዘመቻውን ሕዝባዊ ያደረገው የአፋር ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱና ከክልሉ ላይ ሃይል ጋር ተቀናጀቶ ባካሄደው የማጽዳት ዘመቻ ወራሪውን ሃይል እንደ ቅጠል በመረፍረፍ የሽብር ቡድኑን መሪዎች ተስፋ የለሽ አድርጓቸዋል፡፡

➖ወገናቸውን ከወራሪ ሊታደጉ ከጎንደር፣ ከሸዋና ከጎጃም ገስግሰው ወደ ወሎ የመጡ ፋኖዎች የአማራ ፋኖን እውን አድርገው በፈጸሙት ጀብዱ የጦሳ ተራራን አኩርተውታል፡፡

➖በዚሁ ግንባር የተሠለፈው የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ሃይልም ተጨማሪ ጓዶቹን አስተናግዶ ጠላትን በመለብለብ ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ደቡብ ወሎ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ተቀልብሶ ሰሜን ወሎን ነጻ የምናወጣበት መሆኑ እርግጥ ነውና የደሴና የኮምቦልቻ ወጣቶች ለሠራዊታችን ደጀን የመሆን ተግባራችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ!

ድል ለእኛ!
Share

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4071
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የ ገበሬውን በሬ አርዶ ሊበላ ያሰፈሰፈው ረሃብተኛ ወራሪ ሽፍታ፥ በአየር ሃይል አመድ ሆነ፥

Post by Za-Ilmaknun » 22 Oct 2021, 15:08

ማምሻውን ህወሀት መግለጫ አውጥቷል። እንደተለመደው የኢትዮጵያን ጦር ሰልቅጠን በላን፣ አንድም ሳናስተርፍ ደመሰስን በሚል ቀረርቶ የታጨቀ መግለጫ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ልጁን ለጦርነት ልኮ እየረገፈበት ነውና በመንግስት ላይ ያምጽ የሚል ጥሪም ታክሎበታል። መቼም ሴጣን ሳይቀር በክፋቱና እኩይ ተግባሩ የሚቀናበት ህወሀት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሆዱ ተንቦጭቡጮ በሀዘኔታና ርህራሄ ልጅህን አታስገድል ብሎ ምክር ሲሰጥ መስማት የክፍለዘመኑ ስላቅ ነው ቢባል ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም። የሚገርመው መግለጫው የራሱን ጉድና አስነዋሪ ገበና በሌላው ላይ በመለደፍ ጩኸት ለመቀማት የተደረገውን መፍጨርጨር የሚያሳይ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ጦር ህጻናትን አሰልፏል፣ አንድ ጠመንጃ ለአምስት ወታደሮች መድረስ አልቻለም፣ ሽማግሌዎች በጦርነቱ እያለቁ ነው፣ እያለ ይዘበዝባል። ይህ ድርጊት የማን መገለጫ እንደሆነ ምስክርነቱን ለሶስተኛ ወገን መስጠቱ ይመረጣል። መግለጫ መኮረጅ ጥበብና ስልት ነው ከተባለም አንድ ነገር ነው።

ወደ መሬት እንውረድ። ጦርነቱን በሁለት ሳምንት እናጠናቅቃለን የሚለው የጻድቃን ፉከራ ውሃ በልቶታል። ደሴና ኮምቦልቻን በቀናት ውስጥ እንቆጣጠራቸዋለን ብለው ለቀለብ ሰፋሪዎቻቸው ምዕራባውያን መንግስታትና ለእብደታቸው የደም ግብር ለሚከፍልላቸው የትግራይ ህዝብ ቃል ከገቡ ሳምንት አልፎ ሁለተኛው እያበቃ ነው። ሀሙስ ዕለት ከጭፍራ እስከ ቢስቲማ መስመር ጀሌዎቻቸውንና ከባድ መሳሪያዎቻቸውን የጫኑ 15 ተሳቢ ተሽከርካሪዎች በድሮን መጋይታቸውን ሰምተን ሳንጨርስ ዛሬ በወገል ጤና ከ50 በላይ ተሽከርካሪዎቻቸው በተመሳሳይ ዶግ አመድ መሆናቸው ተነገረን። ከጋሸና ሸሽተው የተበታተኑት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቻቸው አድፍጦ ሲጠብቃቸው በነበረው የሚሊሺያ ሰራዊት ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፉ ተደርገው መደምሰሳቸውንም በመረጃ ሹክ ተባልን። በሀይቅ ማዶ አከርካሪው ተመቶ ካፈገፈገው ጀሌ የተረፈው የህወሀት ሃይል በዛሬው ዕለት መመታቱንም እንዲሁ ሰማን። እናም ማምሻውን የወጣው የህወህት መግለጪያ እነዚህን ኪሳራዎች ለማድበስበስና ለመደበቅ ታልሞ የተጻፈ ድርሰት ነው ቢባል አያስኬድምን?

አየር ሃይላችን መቀሌና ሌሎች አከባቢዎች የሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎችን እያደባየ አራተኛ ቀኑን ተያይዟል። የጦርነቱን ጨዋታ እየቀየረው ያለው ይህ የአየር ሃይል ድብደባ የህወሀትን የደመነፍስ ግስጋሴ ከመግታት ባሻገር የጦርነቱን ሜዳ ወደ ትግራይ ምድር ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነ ይነገራል። የሰማዩ ላይ ጥቃት ህወሀትን ክፉኛ እያሳመመው እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ዒላማቸውን የማይስቱት፣ የተደበቀውን ሳይቀር አነፍንፈው የሚመቱት የኢትዮጵያ ጄቶች የህወሀትን የመሳሪያ ደጀን በዜሮ እያስቀሩት መሆኑ ተሰምቷል። የመቀሌ ነዋሪ በጥቃቱ ምክንያት ከህወሀት ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱም እየተነገረ ነው። ከተማዋን ጥሎ የሚሸሽ እንዳይኖር የሰጋው የህወሀት አመራር ከትላንት ጀምሮ ለታጣቂዎቹ ጠንከር ያለ ትዕዛዝ አስተላፏል። እግሩን ከመቀሌ ሊያስወጣ የሞከረን በጥይት ነድላችሁ ጣሉት ተብለዋል ታጣቂዎቹ። ዛሬ ዶቼቬሌ ከመቀሌ እንደዘገበው ህዝቡ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲያበቃ በግልጽ መጠየቅ ጀምሯል።

ከመከላከያ አከባቢ እንደሰማሁት በድሮን መሪ አጥቂነት የሚካሄደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የህወሀትን ግልብ ምኞት አጨናግፎታል። በህዝብ ዕልቂት ወደፊት ለመግፋት በህወሀት አመራሮች በኩል እየተደረገ ያለው የእብደት ጦርነት መልሶ እየለበለባቸው ነው። ድሮኗ የህወሀትን የከባድ መሳሪያ አቅም እያሟሸሸች በመሆኑ ከሞርታር በላይ የታጠቀውን መሳሪያዎች ማንቀሳቀስ አልቻለም። በኢትዮጵያ በኩል የጦርነቱን ባህሪ በሚመጥን መልኩ ዝግጅቱ ተጠናቆ በቂ ሃይል በየግንባሩ ከቷል። ጄቶች በትግራይ ሰማይ እየተመላለሱ ወታደራዊ ይዞታዎችን እየደበደቡ ይቀጥላሉ። መድሃኒታቸው የሆነችው ድሮን እያሳደደች የኮንቮይ እንቅስቃሴአቸውን አፈር ከድሜ ማብላቷን ለአፍታም አታቋርጥም። የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ በወሎና አፋር የሚርመሰመሰውንና ወደ መግደያ መሬት ሰተት ብሎ የገባውን የህወሀት ጀሌ መጠራረጋቸውን አጠናክረው ይገፉበታል። ከታሰበው ጊዜ ትንሽ ይዘገይ እንደሁ እንጂ የህወሀት መወገድ የማይቀር እውነት ይሆናል።

Mesay Mekonnen

Post Reply