Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 17 Feb 2022, 09:23

የበርካታ ስፖርት አፍቃሪዎችን ልብ አንጠልጥሎ የቆየው የወዳጅነት ጨዋታ በጣለዉ ዶፍ ዝናብ ምክንያት ሊቋረጥ ይችላል ተብሎ በብዙዎች ቢጠበቅም፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ጨዋታው እንዲቋረጥ ባለመወሰናቸው፡ የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ጭቃዉ ላይ እየተንሸራተቱና እየተንደባለሉ ጨዋታዉን በእልህና በቁርጠኝነት ቀጥለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ያሬድ ክለብ ዋንኛ ደጋፊ በመሆን የሚታወቁት ተጽእኖ ፈጣሪ ‘ሁነኛ ሰዎች’ ተሰባስበው፡ ከዚህ በፊት ከቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ቡድን ጋር ያደረግናቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ኣልጠቀሙንም። ተጫዋቾቻችን በተለያዩ ወቅቶች ያገጠጠና ዓይን ያወጣ ወንጀል በቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ደጋፊዎች ሲደርስባቸው፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ መሪና አሰልጣኝ ሆኑ ተጽእኖ ፈጣሪ ሁነኛ ሰዎች ጭምር ድርጊቱን ኣላወገዙም በማለት ሲወነጅሏቸው ተደምጠወል። ራሱ “ቅዱስ ተክለኃይማኖት” የሚለው የክለቡ ስምም ጭምር የቅዱስ ያሬድ ክለብ ታዳጊ ወጣቶች የክለባችን ስም ነው፡ ስማችንን ተሰርቀናል በማለትም ማመልከቻ ለቴክኒክ ክፍሉ ማስገባታቸው ታውቋል። በዚህ ያኮረፉ ሲመስሉም፡ ለወደፊቱ “የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ” የሚለው ስያሜ በይፋ እስኪመለስልን ድረስ ዳግም አንጫወትም እስከማለት መድረሳቸው አፍቃሪ ስፖርት የሆኑ በርካታ ዜጎችን አሳስቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ “የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ” በሚለው ስም ምትክ፡ “የቅዱስ ኣቡነ ጴጥሮስ ክለብ” የሚለውን ስም ቢተኩ ይሻላቸዋል የሚል ምክር ቢጤ ለተቀናቃኞቻቸው ለመለገስ ሲሞክሩም ተደምጠዋል። በተጨማሪም ክለባችን ራሱን ይችል ዘንድ ከውጭ መንግሥታት ይለገሰው የነበረን የገንዘብ ሆነ የቁስ ድጋፍ በውስጣዊ ኣቅማችን መተካት ይገባል በማለት ለውስጥና ለውጭ ደጋፊዎቻቸው ሲገልጹ ተደምጠዋል የክለቡ ተጽእኖ ፈጣሪ 'ሁነኛ ሰዎች'።

የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ኣሰልጣኝ በበኩላቸው “ባንዴራችን የተባለው የዓፋሩ ክለብ” ደጋፊዎች ላይ በቅዱስ ያሬድ ክለብ ደጋፊዎች ኣማካኝነት ዓይን ያወጣና ያገጠጠ ድብደባ ተፈጽሟል፡ በመሆኑም ክለባችን ከባጀቱም ቢሆን የተወሰነ ክፍል ለዓፋሩ ባንዴራችን ክለብ ደጋፊዎች ማገገሚያ እንለግሳለን በማለታቸው፡ የቅዱስ ያሬድን ክለብ ደጋፊዎች አስቆጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ያሬድ ክለብ ኣጥቂዎች በምስራቁና በርካታ የዓፋሩ ባንዴራችን ክለብ ደጋፊዎች ጨዋታውን ለመከታተል በተከማቹበት የስታዲየሙ አቅጣጫ ተደጋጋሚ የማጥቃት ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በአንጻሩ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች ፈታና ዘና ባለ ቀላል ቅብብሎሽ የቅዱስ ያሬድን ክለብ ተጫዋቾች እልህ ውስጥ በማስገባትና በማዘናጋት ላይ እንዳሉ ለማጤን ተችሏል።

የቅዱስ ያሬድ ክለብ አሰልጣኝ ለደጋፊዎቻቸው በሰጡት አጭር መግለጫ “እኒህ ስማችንንም የሰረቁ ‘የቅዱስ ተክለኃይማኖት’ ክለብ ተጫዋቾች ያላሸነፉን፡ ማሸነፍ ኣቅቷቸው እንጂ ራርተውልንና ሊያሸንፉን ስላልፈለጉ አይደለም፤ በመሆኑም የበላይነታችን እንደተጠበቀ 3 ነጥብ ይዘን ጨዋታውን ማገባደድ ይጠበቅብናል” በማለት ጸሃይና ቁር ላይ ተጥደው ጨዋታውን በመከታተል ላሉ በሺዎች ለሚቆጠሩት ደጋፊዎቻቸው ሲገልጹ ተሰምተዋል። የቅዱስ ተክለሃይማኖት ክለብ መሪ በበኩላቸው፡ ክለቡን እንዴት ዳግም በአዲስ መልኩ እንደሚያደራጁና የጨዋታ ስልታችውንም በምን መልኩ እንደሚቀይሩ በማጥናት ላይ መሆናቸውን ለደጋፊዎቻቸው ሲገልጹ ተደምጠዋል። በተጨማሪም ለክለቡ አዲስ ሜዳ ለማሰራት እንዲሁም ጨዋታዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመቅረጽ የሚያስችሉ ዘመን አመጣሽ ድሮኖችንና ድሮን ላይ የሚተከሉ ካሜራዎችን ለመግዛት የውጭ ሃገር አማካሪዎችን ቀጥረው በቅጡ እያስጠኑ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አሰልጣኝ ለወደፊቱ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ካጯቸው የውጭ ሃገር ክለቦች ጋር ለመነጋገር ያመቻቸው ዘንድ የክለባቸውን ገጽታ ለመገንባት ሳያሰልሱ በመስራት ላይ እንዳሉ ብዙ የስፖርት አፍቃሪዎች ለመገንዘብ ችለዋል።

በአጠቃላይ በእስካሁኑ ጨዋታ ይህ ነው የሚባል የውጤት ለውጥ ባለመምጣቱ

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . .

"ስፖርት ለሥልጣን፣ ስፖርት ለድርድር፣ . . .

ስፖርት ለሰላም .. .. .. ስፖርት ራስን ለመቻል!"

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 05 Dec 2022, 06:20

በጣለው ዶፍ ዝናብ ምክንያት ተመልካቾችን ያሰለቸው ጨዋታ ቀዝቀዝ ብሎ የቆዬ ቢሆንም፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አጥቂዎች ከተለያዩ አካላት ባገኙት ምክር መሰረት በጥሩ ቅብብል ምግብና መድኃኒቶችንም ሳይቀር ሜዳ ላይ ሲቀባበሉ ተስተውለዋል። የሁለቱ ክለቦች አሰልጠኞችም “ፕሪቶሪያና ናይሮቢ” በተባሉ የዓይን ጥቅሾች ከተነጋገሩ ወዲህ ይበልጥ በመግባባታቸው፡ የጨዋታው መንፈስ ሰላማዊ እየሆነ መራገጥና መዳማቱም እጅግ እንደቀነሰ ለማስተዋል ችለናል። ይህን ተከትሎም “ቢጫ ሆነ ቀይ” የታየበት ተጫዋች እስከአሁኗ ደቂቃ እንዳላጋጠማቸው፥ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጫዋቾች ድካም ዬሚታይባቸው ሲሆን፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አሰልጣኝ፡ አጥቂዎችን በመቀያየሩ፡ አንዲት ጉል ለማግባት በቅቷል። የተመዘገበችውን ጎል ተከትሎም፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች፡ ከምግባቸውና ከመድኃኒቶቻቸው ለቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጨዋቾች ሲለግሱ ተስተውለዋል። ይህን መሰሉ ሰላማዊ ስፖርታዊ መንፈስ በስቴዲየሙ በመስፈኑ፡ በርካታ ተመልካቾች የደስታ ድባብ በፊታቸው ታይቷል። ይህ ሰላማዊ የሰላም ድባብ ያላስደሰታቸው አንዳንድ ተመልካቾችም፡ ጨዋታውን መመልከት ትተው ከሜዳው ሲወጡ አልፎ አልፎም ድንጋይ ቢጤ ወደ ሜዳው ሲወረውሩ ተስተውለዋል

በአጠቃላይ በእስካሁኑ ጨዋታ የተመዘገበው ውጤት እንደሚከተለው ነው።

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 5 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 5

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

"ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . .

ስፖርት ለሥልጣን፣ ስፖርት ለድርድር፣ . . .

ስፖርት ለሰላም .. .. .. ስፖርት ራስን ለመቻል! . . .

ስፖርት ለይቅርባዪነት . . . ስፖርት ለመቻቻል . . . ስፖርት ለፍቅር!" :mrgreen:

Post Reply