Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 22 Oct 2021, 08:52

የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድ"ና የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

የትግራዩ የቅዱስ ያሬድ ክለብ ከዚህ በፊት “ደቂቀ እስጢፋኖስ” በመባል ይታወቅ የነበረው ክለብ ሲሆን፡ የኢትዮጵያው ቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብም ከዚህ በፊት ንጉሥ ዘርአያዕቆብ በመባል የሚታወቀው ክለብ መሆኑ የክለቦቹ የታሪክ ማህደር ይገልጻል። ጨዋታዉን በመሃል ዳኝነት የሚመሩት የቢዘኑ ቅዱስ ፍሊጳስ ሲሆኑ የመስመር ዳኞች ደግሞ ሁለት ትግርኛ ተናጋሪ ፓትሪያርኮች መሆናቸው፡ የዳኝነቱን ሂደት ውስብስብ አላደረገውም። :mrgreen:

የትግራዩ ቅዱስ ያሬድ ክለብ

የቡድኑ መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ኣሰልጣኝ ጌታቸው (ጐይትኦም) ረዳ (ረዳእ)
ረዳት አሰልጣኝ ወዲ ወረደ

የኢጦቢያው ቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ

የቡድኑ መሪ ዶ/ር ኣብዪ ኣሕመድ
ኣሰልጣኝ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ረዳት አሰልጣኝ ባጫ ደበሌ

ባጭሩ ወደ ውጤቱ ስንመለስ፦

የጨዋታው ፊሽካ እንደተነፋ በቅጽበት፦ ትግራይ 1 - ኢትዮጵያ 0
ኢትዮጵያ በቲፎዞ ድጋፍ መቀሌ ስትገባ፦ ትግራይ 1 - ኢትዮጵያ 1
ትግራይ አንዳንድ ተጫዋቾቿ በስብራትና በልብ ድካም ከጨዋታ ውጪ ሲሆኑ፦ ትግራይ 1 - ኢትዮጵያ 2
ኢትዮጵያ ተጫዋቾቿ ስለተዘረሩ ሙሉ በሙሉ ከሜዳ ለማስወጣት ስትገደድ፦ ትግራይ 2 - ኢትዮጵያ 2

በዚህ ውጤት የእረፍት ግዜ ሆኗል።

ከእረፍት በኋላ ጨዋታዉ በአዲሱ ሜዳ እንዲቀጥል ተወስኗል፡ የጨዋታው ውጤትም ይህን ይመስላል

ትግራይ በወሎና በአፋር በጎንደርም በኩል ተከታታይና ተደጋጋሚ ጥቃት ስትፈጽም፦ ትግራይ 5 - ኢትዮጵያ 2
ኢትዮጵያ በቅጣት ምት ከመሃል ሜዳ ተከታታይና ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ስትፈጽም፡ - ትግራይ 5 - ኢትዮጵያ 4

የእስካሁኑ ጨዋታ ውጤት ይህን ይመስላል፡ ቀጣዩን በቀጣዪ እንዘግብላችኋለን። :lol:

የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ባጠቃላይ ስፖርታዊ ጭዋነት የተላበሰ አካሄድ ሲታይባቸው፡ በሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች መካከል አንዳንድ ጋጠወጥ አካሄድ የነበራቸው ሰዎችን ታዚበናል። ኣብዛኞቹ ጋጠወጥ አካሄድን ሲያዘወትሩ የተገኙት ደግሞ የአስር አለቃ ነገራ ልጆችና ድርቡሾች እንደሆኑ ለማረጋገጥ ችለናል።

ይህ “የወዳጅነት ጨዋታ” በሰላም እንዲጠናቀቅ የሁሉም ስፖርት አፍቃሪዎች ምኞትና ፍላጎት መሆኑንም ለማስተዋል ችለናል። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 28 Oct 2021, 08:38

ጨዋታው እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ ቢሆንም፡ አንዳንድ የኢትዮጵያው የቅዱስ ተክለኃይማኖት ቡድን ተጫዋቾች ኳስ በሌለችበት ቦታ፡ በተደጋጋሚ የትግራዩን የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾችን ሲጎነትሉና ደጋፊዎችንም ጭምር ሲያደሙ በመስተዋላቸው፡ ዳኛው የመስመር ዳኛውን ምክር በመስማት የኢትዮጵያውን የቅዱስ ተክለኃይማኖት ቡድን ተጫዋቾችን በርካታ የማስጠንቀቂ ቢጫ ካርድ ሲያሳዩ ተስተውለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ የጨዋታው ነጥብ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተቀየረም ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ለመገንዘብ ችለናል።
:mrgreen:

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by sarcasm » 28 Oct 2021, 09:43

Meleket wrote:
28 Oct 2021, 08:38
ጨዋታው እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ ቢሆንም፡ አንዳንድ የኢትዮጵያው የቅዱስ ተክለኃይማኖት ቡድን ተጫዋቾች ኳስ በሌለችበት ቦታ፡ በተደጋጋሚ የትግራዩን የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾችን ሲጎነትሉና ደጋፊዎችንም ጭምር ሲያደሙ በመስተዋላቸው

Eritrea has loaned all of it's players to Ethiopia so it cannot be an honest and impartial judge. You need to find an impartial judge.

As for Ethiopian strategy, checkout the coach explaining his game plan.

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 29 Oct 2021, 03:58

sarcasm wrote:
28 Oct 2021, 09:43
Meleket wrote:
28 Oct 2021, 08:38
ጨዋታው እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ ቢሆንም፡ አንዳንድ የኢትዮጵያው የቅዱስ ተክለኃይማኖት ቡድን ተጫዋቾች ኳስ በሌለችበት ቦታ፡ በተደጋጋሚ የትግራዩን የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾችን ሲጎነትሉና ደጋፊዎችንም ጭምር ሲያደሙ በመስተዋላቸው

Eritrea has loaned all of it's players to Ethiopia so it cannot be an honest and impartial judge. You need to find an impartial judge.

. . .

ወዳጄ sarcasm ይህን “የወዳጅነት ጨዋታ”፡ በሰላማዊዋ ጎረቤታችሁ በኤርትራ መዳኘቱን የሚቃወሙ ጥቂቶች ባይሆኑም እንኳ ቅሉ፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የነዚህ ሁለት ክለቦችን ጥበብም ሆነ ተንኮልና ሴራቸውንም ጠንቅቀው ስለሚያውቁ፡ እንከን በሌለበት ሁኔታ ይህን “ሰላማዊ የወዳጅነት ጨዋታ” እንደሚዳኙት የሚመሰክሩ ብዙዎች ናቸው። ምክንያቱም እንዳልንህ የሁለቱን ክለቦች ጥበብ ሆነ ተንኮልና ሴራቸውን፡ ከኤርትራዉያኑ በላይ ሊያውቅ የሚችል እዚህ ምድር ላይ እስከአሁን አልተፈጠረምና ነው! :mrgreen:

እርግጥ ነው ኤርትራውያን ተጫዋቾች፡ የቅዱስ ያሬድን ክለብ ተጫዋቾች፡ እግርኳስ ምን ማለት እንደሆነና፡ እንዴት መጫወት እንደሚገባ፡ ክለቡ ይመሰረትበት በነበረ ግዜ አንስተው አሰልጥነዋቸዋል፡ ከዚያም ኣለፍ ብለው "የስፖርት ትጥቅ" ድጋፍም ሳይቀር አድርገውላቸዋል። የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ የቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጫዋቾች፡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክለቦች የተመረጡ ተጫዎቾችን ክለባቸው ውስጥ ቀላቅለው፡ ባንድ ወቅት ከኤርትራውያን ተጫዋቾች ጋርም “የወዳጅነት ጨዋታ” አድርገው ነበር፤ ዳኞች የተፈጠረውን የማደናግር ስልት ስለተገነዘቡ፡ ኤርትራ በሜዳዋ ላይ ባስተናገደችው ጨዋታ "በፎርፌ እንድታሸንፍ" እንደወሰኑም ይታወቃል። ይህ ሁሉ ታሪክ ነው። :lol:

በተመሳሳይ መልኩም የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾችንም ኤርትራውያን ተጫዋቾች እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በሞራልም ሆነ በሃሳብ እንደደገፏቸው እናውቃለን። ምን ይሄ ብቻ የመጫወቻና የመለማመጃ ሜዳዎችን ሳይቀር ለቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች ኤርትራ ውስጥ ክፍት በማድረግና በማመቻቸት እንዳሻቸው እንዲለማመዱ፡ በተጨማሪም አስፈላጊውን ሁሉ "ስፖርታዊ ትጥቅ" በመለገስ ድጋፍ እንዳደረጉላቸውም እናውቃለን። ይህም የቅርብ ታሪክ ነው። :lol:

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤርትራዉያን ተጫዋቾች በአሁኑ ሰዓት የነዚህ ሁለት ክለቦችን ጨዋታ በትኩረት ከመከታተልና ጥሩ ለተጫወተ ክለብ ሞራል ከመስጠት ባለፈ ያደረጉት ጣልቃ ገብነት ስለሌለ፡ ጨዋታውን ኤርትራዊ የመሃል ዳኛና፡ የመስመር ዳኝነቱንም ሁለት ትግርኛ ተናጋሪ ፓትሪያርኮች እንዲመሩት ተወስኖ፡ ጨዋታው ከተጀመረ ቆየ’ኮ። በተጀመረ ጨዋታ መሃል ደግሞ ዳኛ ይቀየርልኝ ማለት አይቻልም። የጨዋታው ግዜ እስኪያልቅ የምትደግፈውን ቡድን ሞቅ ባለ ሁኔታ መደገፍ ብቻ ነው ካንተ የሚጠበቀውና የሚያዋጣህ፡ ካልሆነ ግን ክለብህ ይሸነፋል።

በነገራችን ላይ፡ እስከ አሁን ድረስ የተቀየረ ውጤት የለም። ቀጣዩን በቀጣይ እንገልጥላችኋለን።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 01 Nov 2021, 05:10

የጨዋታውን ውጤት በጉጉት ለምትከታተሉ የስፖርት አፍቃሪዎች

የቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጫዋቾች፡ በቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች ሜዳ ተከታታይ ማጥቃት በማድረግ፡ የጎሉን ቋሚና አግዳሚ ከግራም ከቀኝም በተከታታይ ሲመቱት ተስተውለዋል፤ በዚህ ኣያያዛቸው፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች ወጥረው ካልተከላከሉ፡ የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾች በቅርቡ ተከታታይ ጎሎች ሳያስመዘግቡ ኣይቀሩም የሚሉ ብዙዎች ናቸው።

ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችም ጨዋታውን በኣጥጋቢ ሁኔታ እየዳኙት እንደሆነ ይነገራል።

የጨዋታውን ውጤት በቀጣይ! :mrgreen:

Tog Wajale E.R.
Member+
Posts: 9652
Joined: 31 Oct 2019, 15:07

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Tog Wajale E.R. » 01 Nov 2021, 07:50

ሁለት፡ጥምብ፡ግማ*ታም፡ዓጋሜ፡ሲላቐሱ፡ማየት፡እንዴት፡ደስ፡ይላል፡

ዴዴብ፡ እውነትም፡ ዴዴብ፡ ረሀብተኛ፡ ሁላ።

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 01 Nov 2021, 08:47

በTog Wajale E.R. የሚመሩ የ፲ ኣለቃ ነገራና የ፲ ኣለቃ ኩራባቸው ልጆች ይህን የወዳጅነት ጨዋታ ለማሰናከል ቢሞክሩም፡ :lol: ጨዋታው በቅዱስ ተክለኃይማኖት ሜዳ በሞቀ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው። የቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጫዋቾች አሁንም በከፍተኛ ወኔ በማጥቃት ላይ ይገኛሉ፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾችም በቁርጠኝነት ወጥረው በመከላከል ላይ ይገኛሉ።

በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኝነት የሚካሄደውን የዚህን የወዳጅነት ጨዋታ ውጤት በቀጣይ እናቀርብላችኋለን። :mrgreen:

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:lol:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 03 Nov 2021, 04:22

የወዳጅነት ጨዋታው ቀጥሏል።

የቅዱስ ያሬድ ክለብ በደሴና ኮምቦልቻ አካባቢ “እየተሽሎኮለከ” አንድ ግብ አስቆጥሯል፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አምበል “ኦፍሳይድ” ነው በማለት ግቡን ለማስሻር ጥረዋል፤ ቢሆንም ግን ከኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እይታ የተሰወረ ስላልነበረ፤ ግቡ ትክክለኛ ግብ መሆኑ ተመዝግቧል።

የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አሰልጣኝ፡ በቅዱስ ያሬድ ክለብ ውስጥ የዉጪ ዜጎች ተቀላቅለው ተጫውተዋል የሚል ስሞታ፡ ለቴክኒክ ክፍሉ ያቀረቡ ሲሆን የቅዱስ ያሬድ አሰልጣኝ ስሞታውን አስተባብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ “በደብረ-እመን” አበምኔት የሚመራው የቴክኒክ ክፍል ጉዳዩን እያጣራዉ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በተጨማሪም የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ አሰልጣኝ የደከሙ ተጫዋቾቻቸውን በአዳዲስ ተጫዋቾች ለመቀየር ደፋቀና ሲሉም ተስተውለዋል።

የእስካሁኑ ውጤት ሲጠቃለል፡ ትግራይ ደሴና ኮምቦልቻ ስትገባ፡

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 06 Nov 2021, 03:35

ጨዋታዉ ቀጥሏል፡ ሁለቱም ክለቦች ትንፋሻቸውን ዋጥ አድርገው መጫወት የተሳናቸው ይመስላሉ።

በእስካሁኑ ውጤት የረካ የሚመስለው፡ የቅዱስ ያሬድ ክለብ አሰልጣኝ፡ የማጥቃት ሂደቱን ገታ አድርገን፡ ወደ መከላከል ብናደላ ኣይከፋም የሚል ኣመለካከቱን ለደጋፊዎቹ በማሰማቱ፡ የክለቡ ደጋፊዎች ያልተለመደ ጩኸት ሲያሰሙ ተስተውለዋል። ለምን የደከሙ ተጫዋቾችን ኣይቀይርም? በማለት ሲንጫጩም፡ አንዱ ተጫዋቻቸው በደረሰበት ግጭት የራስ ቅሉ ላይ ኣደጋ በመድረሱ ከጨዋታ በቃሬዛ ሲወጣ ታይቷል። በመሆኑም የቡድኑ ደፋፊዎች 8 የተላያየ “የቴክኒክ ብቃት ያላቸውን” ተጫዋቾች በደላላ በኩል ከያሉበት በመለቃቀም ወደ ክለቡ ለማስገባት ሲቋምጡ ተስተውለዋል። የነዚህ 8 አዳዲስ ተጫዋቾች ሚና ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ባይቻልም፡ ከዚህ ቀደም ይህ ነው የሚባል የረቀቀ ስልትና የቴክኒክ ብቃት ስላላሳዩ፡ የጨዋታዉን መንፈስ ሊቀይሩት ይችላሉ የሚል ተስፋ ኣይጣልባቸውም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ያሬድ ደጋፊዎችን ሞራል ለመስበር፡ ረዳት አሰልጣኛቸው “በልብ ድኻም” እንዳሸለበ የሚያስመስል ወሬ በስታዲየሙ ውስጥ በስፋት ሲናፈስ ተደምጧል። ረዳት አሰልጣኙ ግን “ጾመ ትግራይን” በቁርጠኝነት በመጾም ላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ። እልህ የተሞሉት የቅዱስ ያሬድ ክለብ ተጫዋቾች፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ በረኛን በተከታታይ “የጥቃት ምት ቀጠና” ውስጥ ለማስገባት ሳያሰልሱ በመስራት ላይ የሚገኙ ይመስላሉ። :mrgreen:

የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ቡድን መሪ፡ ብርቱ የማጥቃት ሂደቱ በሜዳቸው ቀጠና ውስጥ መበራከቱ እልህ ውስጥ እንዳስገባውና፡ ተጫዋቾቹ በሙሉ በአዲስ መንፈስና ቁርጠኝነት የመልሶ ማጥቃት እንዲፈጽሙ መክሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጨዋታው በረጋና በሰከነ ሁኔታ እንዲቀጥልና አላስፈላጊ መቃቃር እንዳይፈጸም የሚሹ አካላት ከውጭ ሃገር የአግባቢነት ትወና ለመተወን ተፍተፍ ሲሉ ታይተዋል። የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ቀንደኛ ደጋፊ የሆኑት የእዉቁና የስመጥሩው ያብዲሳ ኣጋ ልጅ በበኩላቸው፡ ፈጣሪ ከኛ ጋር ስለሆነ እውነትም ከኛ ጋር ስለሆነ፡ በቴክኒክ ብቃትና በብልሃት ይህን ጨዋታ በኣሸናፊነት ቡድናችን ያገባድደዋል እያገባደደውም ነው በማለት በልበሙሉነትና በቁርጠኝነት ሲናገሩ ቢደመጡም፤ እስከአሁኗ ደቂቃ ድረስ ግን ቡድናቸው ይህ ነው የሚባል ግብ ሲያስቆጥር ሆነ በቅዱስ ያሬድ ክለብ ሜዳ ላይ እዚህ ግባ የሚባል ጥቃት ሲፈጽም አልታየም። የቡድኑ ደጋፊዎችም በተቀናጀ መልኩ የተጫዋቾቻቸውን ሞራል ሊጠግንና ሊያበረታታ ለበለጠ የማጥቃት እርምጃም በሚገፋፋ መልኩ ሲያዜሙለትና ሲያወድሱት ኣልታዩም። :mrgreen:

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ :lol: ጨዋታዉን ለመታዘብ ስታዲየሙ ውስጥ የነበሩ ከተለያዩ ኣገር የመጡ ስፖርት አፍቃሪዎች፡ የጨዋታው አዝማሚያ ስላልጣማቸውና ወደ ግርግር እንዳያመራ በመስጋት፡ ከሜዳው ሲወጡና መሰሎቻቸውንም እንዲወጡ ሲመክሩ ተደምጠዋል።

እንደ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እይታ፡ የጨዋታው መንፈስ ቀዝቀዝ በማለቱም ውጤቱ ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አልታየም። በመሆኑም ዉጤቱ ኣሁንም ይህን ይመስላል፦

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 07 Dec 2021, 11:04

ጨዋታዉ ኣሁንም እንደቀጠለ ነው። ኩመካውና ቅብብሎሹ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጧጡፏል። ነገር ግን ጨዋታው ከተኽለኃይማኖት ክለብ ግብ ወደ መሃል ሜዳ እየተጠጋ ይገኛል። በመሆኑም የቅዱስ ያሬድ ቡድን አጥቂዎች ጨዋታውን በድል እናጠናቅቃለን የሚል ተስፋ ያነገቡ ቢሆንም እንኳ፡ የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ ተከላካዮች ብርቱ የመከላከልና አጋጣሚዎች ሲመቹም በማጥቃት የጨዋታውን ትኩረት ወደ መሃል ሜዳው ለመሳብ ችለዋል። ጨዋታው ከአፋርና ከሰሜን ሸዋ ተስቦ ወደ ደቡብና ሰሜን ወሎ ማለትም ወደ ላሊበላና ደሴ ኮምቦልቻና ወልድያ መጠጋቱና ማቅናቱም የዚህ ውጤት መሆኑ ይነገራል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጨዋታውን መንፈስ ለመቀየር የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ቡድን መሪ ዘለዉ የጨዋታው ሜዳ ውስጥ ለመግባት ሲጣጣሩና ተጨዋቾቻቸውን በያገኙት አጋጣሚ ሞራል ለማስነቅ ተግተው ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል። በግራ የተሰለፈው አጥቂዬ ነገ አንድ ጎል ያስመዘግባል ሲሉ እንዲሁም ነገ ከነገ ወዲያም በቀኝ በኩል ያለው አጥቂዬ የጎሉን ፖል ይመታዋል ሲሉ አከፋፋዬ ከመሃል ሜዳ የሚመታት ኳስ ጎል መግባቷ ኣይቀሬ ነው እያሉ ሲናገሩም ተደምጠዋል።

በተመሳሳይ መልኩ የቅዱስ ያሬድ ቡድን መሪም፡ በቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተከላካዮችና አጥቂዎች አማካኝነት ለደረሰባቸው ተከታታዪ ጥቃት፡ የተጫዋቾቻቸውን አሰላለፍ እንደቀየሩና የኋላ ኋላ ማሸነፋቸው እንደማይቀር ሲናገሩ ተደምጠዋል። ከዚህ በፊት አጋጥሟቸው የነበረውን የጨዋታ ታሪክ በመጥቀስም ጉና ላይ 1 ኣመት ሙሉ ተከላክለው እንደነበረና ከዚያም እንደገና መልሰው በማጥቃት፡ ድሉን ለ27 ዓመታት አጣጥመው እንደነበር ትዝታቸውን በሰከነ ሁኔታና “ሳግ እየተናነቃቸው” ለተጨዋቾቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው መግለጫ ሲሰጡም ተደምጠዋል።

ስለሆነም እስከአሁን በተደረገው ጨዋታ፡ የኣሰላለፍ ለውጥ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ቢታይም፡ ይህ ነው የሚባል ግብ እንዳልተመዘገበ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ገልጠዋል። ስለሆነም የእስካሁኑ ውጤት ለውጥ ባለማምጣቱ

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:

Abere
Senior Member
Posts: 10893
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Abere » 07 Dec 2021, 11:22

የስፓርት ጋዜጠኛው ማስተካከያ ማድረግ ይጠበቅብሃል - ዘግይተው የደረሱ መረጃዎች ያሉህ ከሆነ።
በርካታ የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾች ተጎድተው በቃሬዛ ከሜዳ ውጭ ሁነዋል። የቅዱስ ያሬድ ቡድን በጎደሎ የሚጫዎት በመሆኑ 8 በግብ ተበልጦ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የባከ ጊዜ 3 ደቂቃ ተጨምሮ ጨዋታው በቅዱስ ያሬድ ግብ ክልል ተወስኗል።

Meleket wrote:
07 Dec 2021, 11:04

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Wedi » 07 Dec 2021, 11:44

Meleket wrote:
07 Dec 2021, 11:04
ጨዋታዉ ኣሁንም እንደቀጠለ ነው። ኩመካውና ቅብብሎሹ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጧጡፏል። ነገር ግን ጨዋታው ከተኽለኃይማኖት ክለብ ግብ ወደ መሃል ሜዳ እየተጠጋ

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:
ዳኛው አድሎኛ መሆኑን እያረጋገጥ ነው!! :lol: :P

ይህ ሁሉ እንደ ጎል ካልተቆጠረ ምኑ ነው ጎል ሊባል የሚችለው?

ይህ በቪድዮ የኢታየው በጋሸና ግንባር በትግሬ ወራሪዎች ላይ የተቆጠረ ጎል ነው
:P :P

Educator
Member
Posts: 1968
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Educator » 07 Dec 2021, 12:15

At leas one Tigray town or city must be captured.
Wedi wrote:
07 Dec 2021, 11:44
Meleket wrote:
07 Dec 2021, 11:04
ጨዋታዉ ኣሁንም እንደቀጠለ ነው። ኩመካውና ቅብብሎሹ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጧጡፏል። ነገር ግን ጨዋታው ከተኽለኃይማኖት ክለብ ግብ ወደ መሃል ሜዳ እየተጠጋ

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:
ዳኛው አድሎኛ መሆኑን እያረጋገጥ ነው!! :lol: :P

ይህ ሁሉ እንደ ጎል ካልተቆጠረ ምኑ ነው ጎል ሊባል የሚችለው?

ይህ በቪድዮ የኢታየው በጋሸና ግንባር በትግሬ ወራሪዎች ላይ የተቆጠረ ጎል ነው
:P :P

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 08 Dec 2021, 03:38

ወዳጃችን Abere ከኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እይታ የተሰወረ ምንም ጉዳዪ የለም። በስሜት ብቻ ማሸነፍ ኣይቻልም። እንደ ወዳጃችን sarcasm ዳኞች ይቀየሩልኝ ማለትም አይቻልም፡ እንደ ወዳጃችን Wedi ዳኞችን መዝለፍም አያዋጣምም። በቲፎዞ ጫጫታ የወገን ተጫዋች ይበረታታ ወይም የተቃራኒ ተጫዋች ደግሞ ይርድ ይሆናል እንጂ፡ ቲፎዞ ስለተንጫጫ የቲፎዞ ጫጫታ እንደጎል ተቆጥሮ ኣይመዘገብም። :lol:

በጨዋታዉ ከሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች እየተጋጩ እንደወደቁ አስተውለናል፤ ይህ ማለት ግን ጎል ተመዝግቧል ማለት ኣይደለም።

እርግጥ ነው ወዳጃችን Abere ሆንክ Wedi የምትደግፉት ቡድናችሁ ጥሩ ጨዋታ እያሳየ እንደሆነ ልትነግሩን መጣራችሁ ለቡድናችሁ ያላችሁን ልባዊ ድጋፍና ቀናዒነት ያስመሰክር ይሆናል እንጂ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የናንተን ልባዊ መሻት አይተን እንደ ግብ ልንቆጥርላችሁ አንችልም። ስለ ዳኝነቱ ሂደት ርትዓዊነት በምሳሌ አድርገን ለአንባቢ ጥቂት ፍንጭ እንስጥህ።

ወዳጃችን Wedi እንበል አንተና አንድ ሰውየ በብትር ተደባደባችሁ፡ ሰውየው ተሽቀዳድሞ ራስን (ወሎህን)፣ ቅልጥምህን (ሸዋህን) እና ትከሻህን (ጎንደርህን) በበትሩ መትቶ አሳበጠህ እንበል፤ ከዚያም አንተም ተፍጨርጭረህ ተደባድበህ ሰዉየው ካንተ እንዲርቅ አደረግህ እንበል፤ ከዚያም ራስህን ቅልጥምህንና ትከሻህን በደንብ እንደ ወጌሻ አሽተህ እብጠቱ እንዲጎድል አድርገህ ሁኔታህን አሻሽለህ ጤንነትህን ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ መለስክ፡ ታድያ ይህን በማድረህ የሰውዬውን ራሱን (ወሎውን)፣ ቅልጥሙን (ሸዋዉን)እና ትከሻዉን (ጎንደሩን) አሳብጠሀዋል ማለት ኣይደለም። ይህ ማለት ግን ለመጪው ግዜ አታሳብጠውም ማለት አይደለም። እርቅ ካላደረጋችሁ በስተቀር ማለት ነው። :mrgreen:

እንግዲህ ይህ ከገባህ ዘንዳ፡ ቡድንህን ወጥረህ ደግፍ፡ ልዩ ጥበብ ካለህም አሰልጣኙን በግል ምከረው ወይ ደግሞ ጎበዝ ተጫዋች ከሆንክ ደግሞ የቡድንህን መሪ አግኝና ሜዳው ላይ ገብተህ የተቀናቃኝህን “ወሎውን ሸዋዉንና ጎንደሩን” ብለህ ጎል አስመዝግብ።

ወዳጃችን Educator እዚህ ላይ ጨዋታዉን ደህና አድርጎ ያነበበ ይመስላል፡ ድሮ ድሮ” የተማረ ይግደለኝ” ይባል ነበር አሁን አሁን ግን “የተማረ ያስተምረኝ” ሆኗል ዘመኑ።
:mrgreen:
Abere wrote:
07 Dec 2021, 11:22
የስፓርት ጋዜጠኛው ማስተካከያ ማድረግ ይጠበቅብሃል - ዘግይተው የደረሱ መረጃዎች ያሉህ ከሆነ።
በርካታ የቅዱስ ያሬድ ተጫዋቾች ተጎድተው በቃሬዛ ከሜዳ ውጭ ሁነዋል። የቅዱስ ያሬድ ቡድን በጎደሎ የሚጫዎት በመሆኑ 8 በግብ ተበልጦ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የባከ ጊዜ 3 ደቂቃ ተጨምሮ ጨዋታው በቅዱስ ያሬድ ግብ ክልል ተወስኗል።

Meleket wrote:
07 Dec 2021, 11:04
ጨዋታዉ ኣሁንም እንደቀጠለ ነው። ኩመካውና ቅብብሎሹ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጧጡፏል። ነገር ግን ጨዋታው ከተኽለኃይማኖት ክለብ ግብ ወደ መሃል ሜዳ እየተጠጋ ይገኛል። በመሆኑም የቅዱስ ያሬድ ቡድን አጥቂዎች ጨዋታውን በድል እናጠናቅቃለን የሚል ተስፋ ያነገቡ ቢሆንም እንኳ፡ የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ ተከላካዮች ብርቱ የመከላከልና አጋጣሚዎች ሲመቹም በማጥቃት የጨዋታውን ትኩረት ወደ መሃል ሜዳው ለመሳብ ችለዋል። ጨዋታው ከአፋርና ከሰሜን ሸዋ ተስቦ ወደ ደቡብና ሰሜን ወሎ ማለትም ወደ ላሊበላና ደሴ ኮምቦልቻና ወልድያ መጠጋቱና ማቅናቱም የዚህ ውጤት መሆኑ ይነገራል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጨዋታውን መንፈስ ለመቀየር የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ቡድን መሪ ዘለዉ የጨዋታው ሜዳ ውስጥ ለመግባት ሲጣጣሩና ተጨዋቾቻቸውን በያገኙት አጋጣሚ ሞራል ለማስነቅ ተግተው ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል። በግራ የተሰለፈው አጥቂዬ ነገ አንድ ጎል ያስመዘግባል ሲሉ እንዲሁም ነገ ከነገ ወዲያም በቀኝ በኩል ያለው አጥቂዬ የጎሉን ፖል ይመታዋል ሲሉ አከፋፋዬ ከመሃል ሜዳ የሚመታት ኳስ ጎል መግባቷ ኣይቀሬ ነው እያሉ ሲናገሩም ተደምጠዋል።

በተመሳሳይ መልኩ የቅዱስ ያሬድ ቡድን መሪም፡ በቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተከላካዮችና አጥቂዎች አማካኝነት ለደረሰባቸው ተከታታዪ ጥቃት፡ የተጫዋቾቻቸውን አሰላለፍ እንደቀየሩና የኋላ ኋላ ማሸነፋቸው እንደማይቀር ሲናገሩ ተደምጠዋል። ከዚህ በፊት አጋጥሟቸው የነበረውን የጨዋታ ታሪክ በመጥቀስም ጉና ላይ 1 ኣመት ሙሉ ተከላክለው እንደነበረና ከዚያም እንደገና መልሰው በማጥቃት፡ ድሉን ለ27 ዓመታት አጣጥመው እንደነበር ትዝታቸውን በሰከነ ሁኔታና “ሳግ እየተናነቃቸው” ለተጨዋቾቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው መግለጫ ሲሰጡም ተደምጠዋል።

ስለሆነም እስከአሁን በተደረገው ጨዋታ፡ የኣሰላለፍ ለውጥ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ቢታይም፡ ይህ ነው የሚባል ግብ እንዳልተመዘገበ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ገልጠዋል። ስለሆነም የእስካሁኑ ውጤት ለውጥ ባለማምጣቱ

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን"!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 21 Dec 2021, 10:56

ጨዋታዉ የተጋጋለ መስሏል፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች በፈጣን ቅብብል፡ በቅዱስ ያሬድ ክለብ የግብ ክልል እያንዣበቡ ታይተዋል። ተደጋጋሚ የማጥቃት ሙከራዎች በማድረግም የግቡን አግዳሚ በተከታታይ ሲመቱት ተስተውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ያሬድ ክለብ መሪ፡ ከ50 በላይ ለሆኑ የተለያዩ ክለብ መሪዎች፡ የተጫዋቾቻቸውን የአጨዋወት ስልት በተመለከተ ማብራሪያ ልከዋል። የቅዱስ ተክለሃይማኖት ክለብ ደጋፊዎች በበኩላቸው በተለያዩ ከተሞች “በቃ” የሚል መፈክር አንግበው የቡድናቸውን ጨዋነት የተላበሰ አጨዋወት ለዓለም ለማስገንዘብ ሲሞክሩ ተስተውለዋል። ከዋነኞቹ የቅዱስ ያሬድ ክለብ መስራች የክብር አባላት አንዱ በእድሜ መግፋት ምክንያት በሞት የተለዩ ሲሆን፡ በህይወት ዘመናቸው የክለባቸው ቁመና ተስተካክሎ ኣሉ ከሚባሉ የቀጠናቸው ክለቦች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ እጅግ ደስተኛ እንደሆኑ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር። የሳቸው በህይወት መለየት በክለባቸው ላይ የሚያመጣው ጫና ይኑር አይኑር በውል ባይታወቅም በሂደት ሊታይ እንደሚችል ታውቋል። ጨዋታው አሁን ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች አቻ ለመሆን ከዚያም አልፎ ጨዋታውን ለማሸነፍ የሚችሉበት ቁመና ላይ የሚደርሱ ይመስላሉ። አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚሉት ከመጋረጃ ጀርባ የተሸረበ ሴራ ቢኖር ነው እንጂ እስከአሁን የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ግቦች ባስቆጠረ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። :lol:

ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተሳካ መልኩና በልዩ ጥበብ እየዳኙት ያለው ጨዋታ ውጤትም እስከ አሁኗ ደቂቃ እንደሚከተለው ነው፦ :lol:

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን፣ ስፖርት ለድርድር!"!
:mrgreen: :mrgreen:

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Abe Abraham » 21 Dec 2021, 11:30

  • መለኸት

    ሓደ መዓልቲ ንዓኻ ምስናይ ናይ ቋንቋ ክእለቱ መጽሓፍ ምጽሓፍ ኣብዩ ኢሎም ኣብ ቤት-ፍርዲ ከሲሶም ብሕጊ ከእስሩኻ እዮም ። ሃብሮም ከሎኻ ግን እዛ " ዳኛን ሓላው መስመርን " ትብላ ዘሎኻ ፈጺማ ኣይተረዳኣትንን ። ቅድሚ ቅሩብ ይገብር ዛንታኻ ምሉእ ግበሮ ፡ መንጎኛታት ኢና ክትብል እንከሎኻ ከመይ ማለትካ እዩ ፡ ዘይምሉእ ዘረባ ደርቢኻ ኣይትኺድ ዘስምዕ ዛዕባ ምሳኻ ምስ ኣልዓልኩ ኮሪኻ ሓደ ጎስጢ ደርቢኻለይ ። ሕራይ ጎስጢ እኳ ኣይነበረን ። ሒደት ኩራ ግን ነይሩ/ነቢሩ ።

    ምስ ብዙሕ ሰላምታ

    ካብ ሓውኻ ወዲ ኣብራሃም

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 22 Dec 2021, 09:28

ጨዋታው በተጧጧፈበት ወቅት፡ አንድ ወፈፌ ጨዋታ ለማደፍረስ፡ ወደ ኳስ ሜዳው ድንጋይ ሲወረውር ስለተገኘ የጸጥታ ኣካላት ቀፍድደው ኣስወጥተውታል። :lol: ወፈፌው የየትኛው ቡድን ደጋፊ እንደሆነ እስከአሁን ድረስ በውል አልታወቀም። ከዚህ በፊት፡ “ሃገሬ ድል የተጎናጸፈችው በሰንበት ትምህርት ቤቴ ልጆች ወዝና ደም ነው" እያለ፡ ያገሩን የተለያዩ ትምህርት ቤቶችንና የቁርዓን ትምህርት ቤቶች ያፈሯቸውን ብልህ ተጫዋቾች ህልዉናና ጕልህ ሚና ክዶ፡ በጠባብ ጎጠኝነት በየሰፈሩ አሉባልታ ሲነዛና የ ‘ሃገሩን’ ክለብ የአንድነት መንፈስ ለመከፋፈል ለከንቱ ደፋቀና ሲል ተስተውሎ እንደነበር፤ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አረጋግጠዋል።

'ወፈፌው'፤ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችን በጨዋታ መሃል፡ “ጥያቄዎቼን ይመልሱልኝ” ብሎ ቢጠይቅም፤ ጥያቄው ግዜና ሁናቴን ግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጎበታል። ተመሳሳይ ጨዋታዎችን እንዳያደፈርስም ብርቱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውም የዓይን ኣማኞችን ሲገልጹ ተደምጠዋል።
:mrgreen:
Abe Abraham wrote:
21 Dec 2021, 11:30
  • መለኸት

    ሓደ መዓልቲ ንዓኻ ምስናይ ናይ ቋንቋ ክእለቱ መጽሓፍ ምጽሓፍ ኣብዩ ኢሎም ኣብ ቤት-ፍርዲ ከሲሶም ብሕጊ ከእስሩኻ እዮም ። ሃብሮም ከሎኻ ግን እዛ " ዳኛን ሓላው መስመርን " ትብላ ዘሎኻ ፈጺማ ኣይተረዳኣትንን ። ቅድሚ ቅሩብ ይገብር ዛንታኻ ምሉእ ግበሮ ፡ መንጎኛታት ኢና ክትብል እንከሎኻ ከመይ ማለትካ እዩ ፡ ዘይምሉእ ዘረባ ደርቢኻ ኣይትኺድ ዘስምዕ ዛዕባ ምሳኻ ምስ ኣልዓልኩ ኮሪኻ ሓደ ጎስጢ ደርቢኻለይ ። ሕራይ ጎስጢ እኳ ኣይነበረን ። ሒደት ኩራ ግን ነይሩ/ነቢሩ ።

    ምስ ብዙሕ ሰላምታ

    ካብ ሓውኻ ወዲ ኣብራሃም

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Abe Abraham » 22 Dec 2021, 12:09

Meleket wrote:
22 Dec 2021, 09:28
ጨዋታው በተጧጧፈበት ወቅት፡ አንድ ወፈፌ ጨዋታ ለማደፍረስ፡ ወደ ኳስ ሜዳው ድንጋይ ሲወረውር ስለተገኘ የጸጥታ ኣካላት ቀፍድደው ኣስወጥተውታል። :lol: ወፈፌው የየትኛው ቡድን ደጋፊ እንደሆነ እስከአሁን ድረስ በውል አልታወቀም። ከዚህ በፊት፡ “ሃገሬ ድል የተጎናጸፈችው በሰንበት ትምህርት ቤቴ ልጆች ወዝና ደም ነው" እያለ፡ ያገሩን የተለያዩ ትምህርት ቤቶችንና የቁርዓን ትምህርት ቤቶች ያፈሯቸውን ብልህ ተጫዋቾች ህልዉናና ጕልህ ሚና ክዶ፡ በጠባብ ጎጠኝነት በየሰፈሩ አሉባልታ ሲነዛና የ ‘ሃገሩን’ ክለብ የአንድነት መንፈስ ለመከፋፈል ለከንቱ ደፋቀና ሲል ተስተውሎ እንደነበር፤ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አረጋግጠዋል።

'ወፈፌው'፤ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችን በጨዋታ መሃል፡ “ጥያቄዎቼን ይመልሱልኝ” ብሎ ቢጠይቅም፤ ጥያቄው ግዜና ሁናቴን ግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጎበታል። ተመሳሳይ ጨዋታዎችን እንዳያደፈርስም ብርቱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውም የዓይን ኣማኞችን ሲገልጹ ተደምጠዋል።
:mrgreen:
Abe Abraham wrote:
21 Dec 2021, 11:30
  • መለኸት

    ሓደ መዓልቲ ንዓኻ ምስናይ ናይ ቋንቋ ክእለቱ መጽሓፍ ምጽሓፍ ኣብዩ ኢሎም ኣብ ቤት-ፍርዲ ከሲሶም ብሕጊ ከእስሩኻ እዮም ። ሃብሮም ከሎኻ ግን እዛ " ዳኛን ሓላው መስመርን " ትብላ ዘሎኻ ፈጺማ ኣይተረዳኣትንን ። ቅድሚ ቅሩብ ይገብር ዛንታኻ ምሉእ ግበሮ ፡ መንጎኛታት ኢና ክትብል እንከሎኻ ከመይ ማለትካ እዩ ፡ ዘይምሉእ ዘረባ ደርቢኻ ኣይትኺድ ዘስምዕ ዛዕባ ምሳኻ ምስ ኣልዓልኩ ኮሪኻ ሓደ ጎስጢ ደርቢኻለይ ። ሕራይ ጎስጢ እኳ ኣይነበረን ። ሒደት ኩራ ግን ነይሩ/ነቢሩ ።

    ምስ ብዙሕ ሰላምታ

    ካብ ሓውኻ ወዲ ኣብራሃም

መለኸት

ውግእ ናባኻ እንዳ መጽኣካ ከመይ ጌርካ መንጎኛታት ኢና ትብል ? እቲ ናይ ኦርቶዶክስ ሱቕ ኢልካ ግደፎ ። ርጉጽ ነገር እዩ ። ኣከለ-ጅግና ጥራሕ 60% ካብ ደቃን ደቂ ኤርትራን ንበይና ንናጽነት ኤርትራ ከፊላ ። ኩሉ በብዝከኣሎ ኣበርኪቱ ኩሉ ግን ብማዕረ ኣይባሃልን እዩ ። ንሳቡር ዝሃብካዮ ናይ ሓሶት ናእዳ ኣንቢብናዮ ኣሎና ። ዲክታቶር ኢሉ ዝጻረፍ ብዛዕባ ኣበርክቶ ክዛረብን ክምስክርን ኣይክእልን እዩ ።

ካብ ሓውኻ ወዲ ኣብራሃም ወዲ ዓላ

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 23 Dec 2021, 03:58

ጨዋታዉ አሁንም በቅዱስ ያሬድ ክለብ የግብ ክልል ዳርቻ በተሟሟቀ መልኩ እንደቀጠለ ነው። የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ተጫዋቾች በተከታታይ የቅዱስ ያሬድ ክለብን የግብ ቋሚና አግዳሚ ከቅርብና ከርቀት በሚለጉ ኳሶች ሲወቅሩት ታይተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “አቋጥሩኝ” በማለት ሰላማዊውን ጨዋት የውጊያ አውድ ለማስመሰል “ወፈፌው” ኣሁንም በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተለቀቁ በኋላም ማንገራገራቸውን ቀጥለዋል። እንደ ወፈፌው አባባል፡ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ “ለምን የአንድ አሰልጣኝን የቴክኒክ ብቃት ያሞግሳሉ? ለምንስ የአንድ ተጫዋችን ብቃትና ጨዋነት ያደንቃሉ? አሰልጣኙም ሆኑ ተጫዋቹ ከዚህ በፊት የአንድ ክለብን መሪ ወርፈዋል በሃሳብም ሞግተዋል ወዘተ ወዘተ እንዲሁም፤ ጨዋታው ከደራና ክለቦቹ ከፈረጠሙ የኋላ የኋላ ‘ክለባችንን’ ችግር ውስጥ ያስገባሉ” በማለት ሰንካላ ምክንያት እየደረደሩ ከስፖርታዊ ጭዋነት በራቀ መልኩ፡ በስሜታዊነት እየተንገዳገዱም ቢሆን ሊሞግቱ ሲሞክሩ ተስተውለዋል። ወፈፌው የዘነጉት አንድ ሃቅ ሲኖር እሱም “አይደለም አሰልጣኝና ተጫዋች ይቅርና ማንኛውም ተመልካች ጭምር የፈለገውን ክለብ መሪ ‘በሃሳብ የመሞገት የማይገረሰስ ስፖርታዊ መብት’ እንዳለው ነው።” ወፈፌው ለአንድ ክለብ መሪ ጥብቅና ለመቆም የሞከሩ ቢመስሉም፡ የሌሎች ክለብ መሪዎችን ደግሞ እንዳሻቸው ሲያንቋሽሹና ሲወርፉ፡ ‘ስፖርታዊ መብቱ’ ለሳቸው ብቻ የተፈቀደ አስመስለውታል። ይህ የሚያሳየው ወፈፌው ምን ያህል በጠና ‘እንደወፈፉ’ ነው! :mrgreen: በመሆኑም ለወፈፌው የውፍፍናቸውን መጥናትና የዕድሜያቸውን መግፋት ግምት ውስጥ በማስገባትና በማስተዋል አስፈላጊው ህክምና እንዲደረግላቸው ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ኣበክረው አሳስበዋል። :mrgreen:

የብልግና ቃላት በማዘውተር የብዙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እሴትና ማንነትም ሲክዱና ሲንዱ ሲያጠለሹም፡ ቍምነገር የሰሩ የሚመስላቸው ወፈፌው፤ አሁንም አሁንም “አቋጥሩኝ” በማለት በየገቡበት ሰፈር ነውረኛ ቃላቶችን ሲጸዳዱ፣ በብልግና የተሞሉ መፈክሮችን አንግበው ሲያቅራሩ ያላስተዋለ ተመልካች አልነበረም። የወፈፌው አንዱ ጥያቄ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ‘ለምን ወገንተኞች አይሆኑም ለምንስ አያዳሉም’ የሚል ቢሆንም እንኳ፡ በኅሊና መሪነት የተሰጡትን የዳኝነት ኮርሶችን በሚገባ የወሰዱት ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ጨዋታውን ከስሜት በጸዳ መልኩ በጥበብና በማስተዋል በብቃትና በንቃት እየዳኙ እንደሚገኙ ብዙዎች መስክረዋል። :mrgreen:

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስካሁኑ ውጤትም ይህን መስሏል፦

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . . "ስፖርት ለሥልጣን፣ ስፖርት ለድርድር፣ . . . ስፖርት ለሰላም!"
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የትግራዩ "ቅዱስ ያሬድና" የኢጦቢያው "ቅዱስ ተክለኃይማኖት" የእግርኳስ ክለቦች ጨዋታ አሁናዊ ውጤት

Post by Meleket » 11 Jan 2022, 10:36

የወዳጅነት ጨዋታው በትግራዩ የቅዱስ ያሬድና የኢትዮጵያው ቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለቦች መካከል አሁንም በጦፈ መልኩ ቀጥሏል። አሁናዊ የጨዋታው ሂደት እንደሚያመለክተው፡ ሁለቱም ክለቦች ኳስ በሚይዙበት ወቅት የተዋጣለትና ወደር የሌለው የቅብብል ቴክኒካዊ ብቃት ሲያሳዩና ተመልካቾችን ሲመስጡ ተስተውለዋል።

የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ መሪ፡ ባንድወቅት “እኛ ግቦች በብዛት ስናስቆጥር የተለያዩ ክለብ መሪዎች ‘ኧረ ግቡን ቀዝቀዝ አድርጉት ጨዋታው እኮ ለዛ አጣ’ በማለት ደጋግመው ይነዘንዙናል፡ ቡድናችን ተከታታይ ግቦች ሲቆጠርበት ግን አንድም የክለብ መሪ በኣካል አግኝቶ ያጽናናን የለም” በማለት "ትዝብት ነው ትርፉ" በማለት ሲገልጹ ተስተውለው ነበር። አሁናዊው የሜዳ ላይ ጨዋታው እንደሚያሳየን ደግሞ፡ አንድ ግዙፍ የፈረንጅ ክለብ መሪ መጀመሪያ በመልእክተኛቸው በኋላም በአካል እኒህን የቅዱስ ተክለኃይማኖት መሪ እንዳገኟቸው እየተነገረ ነው፤ ይህም የሚያሳየው ቡድናቸው አሁንም በከፍተኛ የማጥቃት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ነው ሲሉ ውስጥ አዋቂ ነን የሚሉ ታዛቢዎች ሲለፍፉ ተሰምተዋል። የቅዱስ ተክለሃይማኖት ክለብ መሪ ያነጋገሯቸው የግዙፉ የፈረንጅ ክለብ መሪ በቅርቡ ከሮማዉ ሊቀጳጳስ ጋር በዝግ ቤት ውስጥ ሆነው ስለ ዓለም ሰላም የተዋጣለት ምክክር እንዳደረጉም የዓለም የመገናኛ ብዙሓን መዘገባቸው ይታወሳል:mrgreen:

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ቡድን መሪ የተጫዋቾቻቸውን ሞራል ከፍ ለማድረግ በርካታዎቹን ተከላካዮች አጥቂዎችና አከፋፋዮችን ለቡድኑን ረዳት አሰልጣኝም ሳይቀር የጥቅማጥቅም ድጎማ በመስጠት ሊያንፈላስሷቸው እንዳሰቡ በይፋ ሲናገሩ ተደምጠዋል። የቡድኑ መሪ ይህ የወዳጅነት ጨዋታ በተሳከ መልኩ ይከናወን ዘንድ ያላችውን በጎ አመለካከት ለማሳየት ሲሉ፡ ለበርካታ የቅዱስ ያሬድ ቲፎዞዎች እንዲሁም የክለቡ አንጋፋ የቀድሞ መሪ ኣቶ ኩነኔ መሸ ጭምር ለሚገኙበት የአዛውንቶች ስብስብ “እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል። የቅዱስ ተኽለኃይማኖት ክለብ መሪ ካንጋፋይቱና ኃይለኛዋ የፈረንጅ ክለብ የቴክኒክ ክፍልና መሪ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከመርካታቸው የተነሳ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው የተለያዩ ክለብ አሰልጣኞችን የአሩሲውን የዴራ-ኣባ ሜንጫ ክለብ መሪንም ጭምር ሳግ እየተናነቃቸው “እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰህ” ሲሉ ተስተውለዋል። ይህ የክለብ መሪ ባንድወቅት ነውጠኛ ባህሪ አሳይተሃል ክለቦችንም ደም አቃብተሃል ተብሎ ከጨዋታ ሜዳ ለዓመታት ታግዶ ቆይቶ ነበር። በተመሳሳይ መልኩ የበራራ-ኮከቦች ክለብ መሪንም 'እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰህ' በማለት የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ለክለቡ ቦርድ ሰብሳቢ ለጋዜጠኛዉ እስክንሞሽር መሸ፡ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ መሪ ሲያስተላልፉለት ተደምጠዋል። ይህ ዓላማዉና ኣቋሙ እንደብረት የፀና መሆኑ የሚነገረለት የበራራ-ኮከቦች ክለብ መሪ፡ እሱን ለእስርና እንግልት ለመዳረግ በሃሰት የመሰከሩበትን ዋሽቶ-አደሮች በሙሉ ፈጣሪ ሺ ግዜ ይቅር እንዲላቸው ሲለምንላቸው ተደምጧል:lol:

የጨዋታው መራዘም ያሰለቻቸው የሚመስሉት የቅዱስ ያሬድ ቡድን ተጨዋቾች፡ በየስርቻው በድካም ሲዘረሩ የተስተዋሉ ሲሆን፤ የቡድኑ መሪ በበኩላቸው፡ “ተጫዋቾቻቸው በመልካም ቁመና ላይ እንደሚገኙ፤ በፈለጉት ሰዓት ያሻቸውን ያህል ግብ ማስቆጠር እንደሚችሉ፤ ለግዜው የወዳጅነት ጨዋታው እንዳይደፈርስ ዝምታን እንደመረጡ” ሲናገሩ ተስተውለዋል። የቡድኑ የአሰልጣኝም “ቡድናችን ይህን ያህል ጥቃት የደረሰበት በሜዳው በስተሰሜን የሚገኙት ራሰ በራው የባህር ቀበሮዎች ክለብ መሪና አሰልጣኝ ከነደጋፊዎቻቸው፡ ለቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ ያላሰለሰ ድጋፍ በመስጠታቸው ነው” በማለት ራሰበራውን የባህር ቀበሮች ክለብ መሪና አሰልጣኝ ከነደጋፊዎቻቸው ሲወርፉና ሲወነጅሉ ተስተውለዋል። :lol:

በሜዳው በስተሰሜን በኩል ከነደጋፊዎቻቸው ሰላማዊውን ጨዋታ በመታዘብ ላይ የሚገኙት ራሰ በራው የባህር ቀበሮዎች ክለብ ቡድን መሪም በበኩላቸው፤ እኛ እርግጥ ነው ለቀጣዩ ጨዋታችን ይረዳን ዘንድ የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብን መደገፍ መብታችን ነው። የቅዱስ ያሬድ ክለብ ቡድን እፍርተኛና የዳኞችን ይግባኝ የሌለውን ብይን ሳይቀር ከመቀበል አሻፈረኝ በሚሉ ተጫዋቾችና አምበሎች እንዲሁም የቡድን መሪዎች የተሞላ በመሆኑ፡ ይህንን ነውጠኛና አደፍርስ የሆነ ክለብ በፍጹም በሞራል ሆነ በማቴሪያል አንደግፍም፡ ለወደፊቱ ከማንኛውም የወዳጅነት ጨዋታ ውስጥ ይህ ነውጠኛ ክለብ ባይካተትም እንመርጣለን” ሲሉ ተደምጠዋል። ክለባቸው ማንኛውንም ዓይነት ክለብ የመግጠም ዓቕምና ብቃት እንዳለውም አክለው ሲገልጹ፤ ከቻይና ፍልፈሎች ጋር ሰፋ ያለ የልምምድ መድረክ መፍጠር እንደሚሹ ሲናገሩ ተደምጠዋል፤ ይህን ጉዳይ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም ያሜሪካ ጠብደሎች በብድር የተሞሉ፡ ማንም ወረቀት ላይ ዶላር እያተሙ የዓለምን ክለቦች ለመደለል ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውን በመገንዘብ፡ ክለባቸው በዋነኝነት ከቻይና ፍልፈሎች ጋር በወዳጅነት መቆራኘት እንደሚመርጥ ይፋ ባልሆነ መልኩ ሲናገሩ ተደምጠዋል። :mrgreen:

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወዳጅነቱ ጨዋታ በደራበት በዚህ ቀውጢ ሰዓትከዚህ መጣ የማይባል ብርቱ ዝናብ በመዝነቡ፡ በጨዋታው መካከልም በርካታ የሁለቱ ክለብ ተጨዋቾች በመጎዳታቸውም፡ ሃኪሞች ፋታ አግኝተው እስኪያክሟቸው ድረስ፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ጨዋታውን ላልተወሰነ ግዜ ሊያቋርጡት እንደሚችሉ በርካታ ታዛቢዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። :lol:

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስካሁኗ ደቂቃ ውጤትም እንደሚከተለው ነው፦

የቅዱስ ያሬድ ክለብ 6 - የቅዱስ ተክለኃይማኖት ክለብ 4 ማለትም ትግራይ 6 - ኢትዮጵያ 4

የቀሪውን ጨዋታ ዘገባ በቀጣዪ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ስፖርት ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለወንድማማችነት. . .

"ስፖርት ለሥልጣን፣ ስፖርት ለድርድር፣ . . .

ስፖርት ለሰላም .. .. .. ስፖርት አዛውንት የጦር ምርኮኞችንም ለመፍታት!"
:mrgreen:

Post Reply