Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4077
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ይኼ ጦርነት ትህነግ በጥጋብ ተወጥሮ የለኮሰው ስለሆነ፥ በደንብ ማስገሳት ያስፈልጋል--- ሙስጠፌ

Post by Za-Ilmaknun » 21 Oct 2021, 19:06

"የትእቢት ጦርነት ነው ብለን ነው የምናስበው"

(ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሀመድ)

#Ethiopia : ይሔ ጦርነት ለ27 አመት አገር ሲያደማ የነበረው ጁንታ መንግስት ሆኖ አገር ማፍረስ ስላልቻለ አሁን ደግሞ ሽፍታ ሆኖ አገር ለማፍረስ የሚያደርገው እንቅሰቃሴ አድርጌ ነው የማየው። አገር አፍርሶ ሰላም የሚሆን አካባቢ አይኖርም።

የአማራና የትግሬ ግጭት ነው የሚለው የነሱ ካራከታራይዜሽን ነው። በነገራችን ላይ እነሱ ብቻ አይደሉም እኛ አካባቢም ፀረ አማራ ፕሮፖጋንዳ የሚነዙ የሶማሌ አክቲቪስቶች አሉ።

ብዙ ጊዜ ምክንያታቸውን ወደኋላ ስናይ ከራሳቸው እንዳልሆነ እንረዳለን እዚህ ያለ ሶማሌን የበደለ አማራ አላይም፣ ግን ጥላቻው በአዲስ ተቀስቅሶ ይሔ ብሔር እየመጣባችሁ ነው የሚለው እርግጥ ሶማሌ ችግር መጥቶበት ነው የሚለው መሬት ላይ ስለሌለ… ጁንታው አማራ ጠላቴ ነው ስለሚል… የጁንታው ጠላት የሶማሌም ጠላት መሆን አለበት። በነሱ ጀሌዎች አካባቢ አማራ ኤክስፓንሺን የሚል እንቅስቃሴ እናያለን ።

ከዛ ውጪ ይህ ጦርነት በአገራችን ላይ የተቃጣ፣ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣ ወረራ ነው። ወያኔ ብቻ ነው ብለን አናምንም የውጪ ሀይሎች እንዳሉበት እናውቃለን። ከእንቅስቃሴያቸው ከዲፕሎማሲው አሻጥሮች የሚታይ ጉዳይ ነው። ወያኔና ጀሌዎቹ ትላንት የሰሩትን የሚደግሙበት ወይም የባሰ…የትላንትናው ሕዝቡን በቀኝ አዙር መግዛትና መግደል ነበር አሁን ደግሞ አገር አፍርሶ ሕዝቡ እንዲሰቃይ የሚሰሩት ስራ ነው።

ምክንያታቸው ደግሞ ያናድዳል፣ እኛ ካልተመቸን ሌላው እንዳይመቸው እኛ ስልጣን ካልይዛን ወይም እኛ ያስቀመጥነው ስልጣን ካልያዘ ሌላው ሰው ሌላው ብሔር መኖር የለበትም የምትለዋ የጥጋብ ምክንያት ስለሆነች… እነሱ ከማንም ስለማይሻሉ…እነሱ አልተመቸንም ብለው ሶማሌ የሚበጠበጥበት፣ አማራ የሚረበሽበት፣ ኦሮሞው ደቡቡ ሰላም የሚያጣበት ምክንያት… ትምክህተኛ ይላሉ፣ ግን ከዚህ በላይ ትምክህተኝነት የለም።

እኔ ስልጣን ላይ ከሌለሁ አገነጠላለሁ ብቻ አይደለም እያሉ ያሉት አገር እናፈርሳለን ነው… እንደዚህ አይነቱን ትእቢት ፣የትእቢት ጦርነት ነው ብለን ነው የምናስበው። በርግጠኝነት ይሔ ትእቢት እነሱንም ጎድቷቸዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ጥቅምት 9/2014 ዓ.ም ለESAT TV በሰጡት ኢንተርቪው "… ጦርነቱ የአማራና የትግሬ ነው የሚሉ አሉ። ጦርነቱን እንዴት ትመለከቱታላችሁ" በሚል ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ላቀረበላቸው ጥያቄ ከ19ኛው እስከ 23 ኛው ደቂቃ ድረስ የሰጡት ምላሽ።

ሙስጠፌ ከ መሳይ መኮንን ጋር