Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ከ መቀለ መሰደድ ተከለከለ! የ ነፋሪት ጥቃት ህዝብ እያራደ ነው። ስደት የሚከጅል፥ እርምጃ ይወሰድበታል

Post by Za-Ilmaknun » 21 Oct 2021, 16:51

ከመቐለ መሰደድ አይቻልም የሚል ህግ ወጣ!
-
በተከታታይ ለሶስተኛ ቀናት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፣ የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችና የጁንታው የሥልጠና ማእከል በአየር ተመቷል። ወያኔ ማስቆም ባለመቻሉ በትግራዋይ መካከል ተቃውሞ ተነሳ ። ህዝቡ ለወያኔ ያቀረበው ጥያቄ “እስከ መቼ ይህንን የአየር ጥቃት መሸከም እንደሚቻል በግልጽ ንገሩን” የሚል ሲሆን ሁሉም ግራ ተጋብቷል።
“ቁጭ ብለን አብይን መስደብ ከቦንብ አያድነንም” “የወያኔ ከፍተኛ አመራር መልስ ካልሰጠን ቤተሰቦቻችንን ይዘን ራሳችንን ማትረፍ አለብን” እያለ አብዛኛው ማህበረሰብ መሰደድ ጀምሯል።
የህዝቡን ጥያቄ በግልጽ መመለስ ያልቻሉት የወያኔ አመራሮች “ማንም ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም አቅጣጫ ከመቐለ መውጣት አይችልም” የሚል ህግ ዛሬ ማምሻውን አውጥተዋል። በ”እግራችን አፋር ገብተን ራሳችንን እናትርፍ” የሚለው ህዝብ እየጨመረ ሲሆን አሁን በተቀመጠው መቐለን የማሸግ ተግባር ምክንያት በሁሉም አቅጣጫ ለመሰደድ የሚጎርፈው ህዝብ ከወያኔ ሰራዊት ጋር መጋጨት ጀምሯል።
ሁሉም የወያኔ ወታደር ለተቀመጠው ህግ መመራት አለበት፤ እምቢ ያለውን በቀጥታ ተኩሶ መግደል እንደሚችልም ዛሬ በመቐለ የታወጀው የነጻ እርምጃ ህግ ያስረዳል።
ዘ-ሃበሻ እንደዘገበው