Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"አሁን ግን እውነት በመናገራችን ከድሮው ህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ በበለጠ በብዙ እጥፍ ዋጋ ሊያስከፍሉን የከበቡን እጅግ ብዙ ኃይሎችና አሰላለፎች ተፈጥረዋል" የለውጡ ትሩፋቶች በብሩክ አበጋዝ

Post by sarcasm » 20 Oct 2021, 18:20

የለውጡ ትሩፋቶች በብሩክ አበጋዝ

አንዳንድ ሰወች የምታውቁትን እውነት ንገሩን ይላሉ። እውነትን መናገር ዋጋ እንደሚያስከፍል እንዴት እንንገራቸው።

በህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ጊዜ እውነትን ስንናገር የምንሰጋውም ሆነ ዋጋ ለመክፈል የምንዘጋጀውም ከህወሓት በኩል ያለውን ነበር፤ ኃላፊነቱንም በህወሓት/ኢህአዴግ ላይ እንጥል ነበር።

አሁን ግን እውነትን በመናገራችን ከድሮው በበለጠ በብዙ እጥፍ ዋጋ ሊያስከፍሉን የከበቡን እጅግ ብዙ ኃይሎችና አሰላለፎች ተፈጥረዋል።

ባይሆን ዋጋ የሚያስከፍለውን እውነት ትተን ዋጋ የማያስከፍለውን እውነት ማውራት ይሻላል። በዚህ ዘመን አለመዋሸት በራሱ ትልቅ ነገር ነው ፤ ምናልባት ጊዜው ተለውጦ አፈሙዝ ደግነው ዋሹ የሚሉን ካልኖሩ በቀር።

ይሄ ሁሉ የሚሆነው በማኅበረሰባዊ ንቃተ ሕሊና መዝቀጥ ምክንያት ነው። ማኅበረሰባችን ወደ መታነቂያው የሚወስዱትን አይዟችሁ እያለ እያጨበጨበ ፤ ልታደግህ ልውጣ ልውረድልህ የሚሉትን ደግሞ ለማሳደድና ለማጥፋት ጊዜና ጉልበቱን የሚፈጅ ነው። ሕዝብ የጥቂት ባለሟሎችና ባለጠጎች ቁሳዊ ንብረት ሆኖ ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም።
Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/abegazbiruksis ... 6175223456