Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Debre Berhan, Capital City of North Showa Zone Declared a Night Curfew - The War Has Reached Showa

Post by sarcasm » 20 Oct 2021, 17:54

ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከፓሊስና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩ ዙሪያ ዉይይት በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳለፈ።

በውይይቱ እንደተገለጸው በከተማው በተለያዩ ጊዜያት ሰርጎ ገቦች እየገቡ በመሆኑና በዞኑ ማጀቴ አካባቢ በቅርቡ የተከሰተው አደጋ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልልና ከሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በከተማችን ሁሉም ቀበሌዎች የተጠለሉ ተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ አካባቢያችን ከስጋት ነፃ አለመሆኑንና የጁንታውም ሆነ የኦነግ ሽኔ የሽብር ቡድኖች የትኩረት ቦታ መሆኑን ማሳያ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት ስጋቱን ለመቅረፍ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ስራ ከተሰማሩና ከጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጪ ይሉ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽት 2:30 ድረስ ብቻ የእግረኞች እንቅስቃሴ ደግሞ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽት 4:00 ድረስ ብቻ እንዲሆን የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ ሊሻሻል እንደሚችል ተገልጿል።


በተጨማሪም የአንኮበርና ጅሩ መስመርን ጨምሮ በአራቱም ኬላዎች የተጠናከረ ፍተሻ እንዲካሄድ፣
የተጠናከረ የ24 ሰዓት ፓትሮል/ጥበቃ እንዲደረግ፣
በርካታ ህዝብን የሚያከብሩና የህዝቡን ህልውና አደጋ ላይ የማይጥሉ ወጣቶችን መመልመል ማደራጀትና ማሰልጠን፣
የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት ከጸጥታ ኃይለለ ጋር በማቀናጀት ስምሪት እንዲሰጥ፣
ተመላሽ ሰራዊት አባላትን አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ፣
አከራይ ተከራይን መለየት 50ለ5 የብሎክ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፣
የፓለቲካ አመራሩና የቀበሌ አመራሩ ህብረተሰቡን የማነቃቃት ስራ እንዲሰሩ
በየቀበሌው የስጋት ቦታዎች ተለይተው ልዪ ጥበቃ እንዲደረግ
ለጸጥታ ሃይሉ አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉ
የህብረተሰቡን ስነ ልቦና በመገንባት ማረጋጋትና ማነቃቃት እንዲቻች
ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በየቀበሌው የተጠለሉ ወይም የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ማንነት መለየት
ህገወጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ወደህጋዊ መስመር ማስገባት
የመረጃ ስርዐቱ ከወትሮው በተለየ የተጠናከረ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፎ ለሚመለከተው ስምሪት ተሰጥቷል።
Please wait, video is loading...