Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአብይ አህመድ መቀሌን የመደብደብ ምክንያቶች ፦ ሃይሉ ለሊሳ ኦቦሮ

Post by sarcasm » 20 Oct 2021, 16:55

የአብይ አህመድ መቀሌን የመደብደብ ምክንያቶች ፦

1. ለገጠመው መራራ የጦር ሜዳ ሽንፈት ምክንያት የተስፋፊውን የአማራ ቡድን ጩሄቶችን ለማስታገስ ነው፣ የዚህ ቡድን የጥላቻ ስሜት፣ ጠላቴ የሚለው ህዝብ ስደማ የራሱን የሆነውን ጉዳይ ይረሳል፣ ስሜቱ ይቀዘቅዝና፣ ግዛዊ ወደ ሆነው ደስታ ይቀየራል፣ ምን ይጠቅመኛል ብሎ አይጠይቅም፣ አሁን ከተደሰተ ሌላው ችግሩ አይደለም፣ ይህ ደስታው ተኖ ስያልቅ፣ አብይ አህመድ አሁንም ሌላ ግዛዊ የጥላቻ ማስታገሻ ይሰጣቸዋል፣

2. በመቀሌ የሚገኙት፣መንግስታዊ ያልሆኑ፣አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ትግራይን ለቀው እንድወጡ የማድረግ ሙከራ ስሆን፣ ይህ ነገር ባለፈው ጊዜ 7 ከፍተኛ የUN እርዳታ ሰራተኞችን ከሃገር ብያባርርም፣ በትግራይ ያለው የአብይ አህመድ ሰራሽ የህዝብ እልቂቶችን ከአለም አቀፉ ማህበረብ መደበቅ ባለመቻሉ፣ ሌላ ሙከራ ይመስላል፣

3. አብይ አህመድ በትግራይ ላይ ያደረገው ኢሰብአዊ ድርጊቶችን በሙሉ፣ የትግራይ ሰራዊት በያዛቸው ቦታዎች ሁሉ እንዲያደርግ ይፈልጋል፣ ይህ እንድደረግለት ያልፈናቀለው ድንጋይ የለም፣ ሌላው ቀርቶ የህዝቡን መኖሪያ ቤቶች በከባባድ መሳሪያ ከእኔ ቤተሰብ ያጋይ እና በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች የሽብር ቡድኑ ህወሓት ነው ያደረገው በማለት ይለፍፋል፣ ይህ ነገር እስከ አሁን የተሳካለት ነገር ስላልሆነ፣ የትግራይ ሰራዊትን በማነሳሳት እንድፈጸምለት በመፈለግ መቀሌን ላይ ቦምብ እያወረደ ይገኛል፣

4. የአንድ ቡድን ስርኣት ተስፋ ሲቆርጥ የሚያደረገው ተፈጥሮኣዊ ጉዳይ ነው፣ ደርግ አልቆለት፣ ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ/ አምቦን ስይዝ እንኳን የተለያዩ ከተሞችን በጄት ይደበድብ ነበር፣ ይህ የአብይ አህመድ ድርጊት ፣ተሸናፊ ስርኣቶች በስተመጨረሻቸው ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፣ ምናልባት አብይ አህመድ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ውስጥ፣ በፍጹም የማያገኘውን የፖለቲካ የድርድር ጥያቄን በአደባባይ ልጠይቅ ይችላል፣ ከዚያ ቀጥሎ እድሉን ካገኘ የሚቀረው ነገር መፈርጠጥ ብቻ ይሆናል፣
Please wait, video is loading...