Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የሼህ ሁሴን ጅብሪል እና ዐፄ ዮሐንስ ጉዳይ ---- << የኋላ ኋላ የልጅ ልጆችህ የፍፃሜው መካነ-መቃብራቸው ወሎ ነው >> ሼህ ሁሴን ጅብሪል

Post by Abere » 17 Oct 2021, 13:36

የሼህ ሁሴን ጅብሪል እና ዐፄ ዮሐንስ ጉዳይ ---- << የኋላ ኋላ የልጅ ልጆችህ የፍፃሜው መካነ-መቃብራቸው ወሎ ነው >> ሼህ ሁሴን ጅብሪል

ለብዙዎች ይህን ትንግርታቸውን ለሚያምኑ ዘመኑ አሁሼህ ን የደረሰ ይመስላል። በርካታ ታዳጊ ወጣት ጎልማሳ ፣ አሮጊት ሽማግሌ፣ በዐንቀልባ ልጅ ያዘለች፣ ነፍሰጡር ሳይቀር በጅምላ ወደ ወሎ ምድር ሰተት ብለው ገብተው አሁን በርካታ የትግሬ ሰው እያለቀ ነው። በሰው ኅሌና ይህ ጥፋት መሆኑ እያወቀ ወደ ሞት ምድር አይሄድም። ትድያ ወደ ሞት ሽቅድምድም የሚቡበት ምክን ያት የፈጣሪ ትዕዛዝ እና ቀነ ቀጠሮ ካል ሆነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል። በእውነትም እኝህ ሼህ በትክክል ታይቷቸው ነበር ለማለት ይቻላል።

በዘመናችው ዐፄ እጅግ በጎጃም እና ወሎ ላይ ክፋት እና አረመኔ ተግባር ይፈፅሙ እንደ ነበር እና በተለይም የራያ አካባቢ ህዝብ ብሎም በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ያሳድ ዱ ስለነበር ሼህ ሁሴን ጅብሪል በዐፄ ዮሐንስ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ወደ አምላካቸውም አቤቱታ ኣአብዝተው ያቀርቡ ነበር ይባላል

ለክፋታቸው ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ዐፄ ዮሐንስ በመምሬ ግርማ አማካኝነት ሼህ ሁሴንን ደሴ ላይ ለማጥመቅ ይሞክራሉ ነገር ግን የማጥመቁ ስራ አልተሳካላቸው። መምሬ ግርማ ቀድመው አብደው ጨርቃቸውን ቀደው አዝዋ ገደል ገብተው ሞቱ ይባላል። ሼሁ ግን ቀደም ብሎ ታይቶቷቸው ነበር እና ይህን አሉ:-

ወንዝ ለወንዝ ሂጄ - እበላለሁ ዓሣ፣
ለጥቂት ቀን - ብዬ አልበላም ነጃሳ።

ያለየህም እየው - ያልሰማህም ስማ፣
ቆቡ ተቀደደ የመምሬ ግርም።

በመጨረሻም ዐፄ ዮሐንስ በባዕዳን እጅ እንደሚወድቁ እና እንደ ሚማረኩ ሲገልጹ:-

የዮሐንስ በቅሎ ብረኪ ብረኪ፣
መተማ ላይ ሄደሽ እንዳት ማረኪ።

ብለው ተንብየዋል ይባላል:: በመጨረሻም የትግሬ ጦር የኋላ ኋላ (አዱኛ እንደ ድር ስትቀጥን እንደ እርሳቸው አባባል) ወሎ ምድር ላይ ይፈታል የትግሬ እሬሳ እንደ ቆሎ በየሜዳው ይፈሳል ብለዋል። እግዜር ለትግሬዎች ልብ ሰጥቷችው ከዚህ ምፅዓተ ዕልቂት ይታደግ ከማለት በስተቀር ሌላ ምን ይባላል::