Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"በሁሉም መስፈርት አሁን ካለው ሁኔታ በመለስ ጊዜ የነበረው ሁኔታ በጣም የተሻለ ነው። ብዙዎችም የመለስን ዘመን የሚናፍቁበት ሁኔታ ነው ያለው።" ግርማ ካሳ

Post by sarcasm » 16 Oct 2021, 17:49

አቶ መለስ ዜናዊ አሁን አገራችን ላለችበት ችግር ምክንያት የሆነው የጎሳ ፖለቲካ ያመጣው እርሱ ነው።፡ የሕወሃቶች መርዝ ነው አንዱ ለችግራችን ምክንያት የሆነው።
ይሄ እንደተጠበቀ ግን በሁሉም መስፈርት አሁን ካለው ሁኔታ በመለስ ጊዜ የነበረው ሁኔታ በጣም የተሻለ ነው። ብዙዎችም የመለስን ዘመን የሚናፍቁበት ሁኔታ ነው ያለው። ይሄንን የሚያሳይ አንድ ጦማር አነበብኩ። እንደሚከተለው አጋራኋችሁ

Gonder tube / ጎንደር.

አቶ መለሥ ዜናዊ ይቅርታ አድርጉልን‼

ምንም አንባገነን ምንም በዘር ቀንበር ስር ሆነው ሀገር ቢመሩም በርሶ ዘመን የዚህን ግዜ ያህል ሞት እና ግድያ አልነበረም‼
በእርስዎ ዘመን አንድ ንፁህ ዜጋ በአሸባሪዎች ተገድሎ አያውቅም‼
በእርስዎ ዘመን ፓለቲካ ውስጥ እስካልገባን ድረስ ደህንነታችን ተረጋግጦ እንኖር ነበር ‼
ዛሬ ግን ፖለቲካ ውስጥ ገባንም አልገባህም የጥይት እራት እንሆናለን ።ህፃንም ሆነ አዛውንት ባላሰብነው መንገድ እንገደላለን።በዚህ ሶስት አመት ውስጥ #ሞት ባህላዊ ዜናችን ሁኗል።‼
ተራ የመጠበቅ ጉዳይ እንጂ በየአንዳንዳችን ቤት ሞት አፍጥጧል‼
በእርስዎ ዘመን ሌላው ሁሉ ቢቀር በሠላም ወጥተን በሠላም እንገባለን ! ማንም ከክልላችን ዉጡ ብሎ አልገደለንም !‼
ሌላው ሁሉ ችግር እንዳለ ሆኖ ቢያንስ በሠላም ሠርተን በሰላም እንገባ ነበር !‼
በሰላም ከዳር እስከ ዳር ኢትዮጵያ እንኖር ነበር‼
በየመንገዱ አንገደልም ነበር ! በእጅጉ የህግ የበላይነት የከበረ ነበር !‼
ኦነግ እንደ አሁኑ በመንግስት እየታገዘ አይጨፈጭፈንም ነበር‼
አሁን ለመኖራችን ዋሥትና የለንም ጥበቃ የለንም። ሞተን እንኳ ቀብራችን አያምርም በዶዘር ታፍሰን እንቀበራለን።
አቶ መለሥ ዜናዊ እርሶን በዳይ አርገን ኮንነናል፡ ሠድበኖታል ብዙ ብዙ የማይገባ ነገር አርገናል‼
አሁን ግን ከርሶ የባሠ ግዜ መጥቶብን ተጨንቀናል። በየቀኑ እንገደላለን። በየቀኑ እንፈናቀላለን‼
ንብረታችን ይወድማል አካላቺን ይጎላል ብንኖርም እንኳ ደሥተኞች አይደለንም‼
ኑሮዉ ከብዷል ተወዷል በዚህም ተጨንቀናል። በዚህ ምክንያት ያ የርሶ ዘመን የተሻለ ሆኖ አገኘነዉ። እናም ተመኘነዉ‼

በድለኖታል ይቅር በሉን.

Please wait, video is loading...


Post Reply