Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethioscience
Member
Posts: 3872
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ጥይታቸው ነው! Agames lies and ignorance exposed!!

Post by ethioscience » 16 Oct 2021, 14:36


የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ጥይታቸው ነው!

ዘንድሮ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሕዝብ ሲረብሽ ተመልክተናል። ከግንባር ጦርነት በላይ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሽብር ፈጥሯል። ሀሰተኞች ዛሬም ቀጥለዋል። አማራው ቴዎድሮስ አያሌው ጭፍራ በትህነግ እጅ አልገባችም ብሎ የለጠፈውን ፎቶ የትግሬ ፌስቡከኛ "ጭፍራን ያዝን" ብሎ ሀሰት ሲያወራበት ውሏል።

እነሱ ሀሰት ሲያወሩ ችግር የለባቸውም። ተናብበው ሀሰት ያወራሉ። እየተመቱም ቢሆን እነ ፃድቃንና ጌታቸው ረዳ ሀሰት ሲያወሩ የሚዘምትባቸው የራሳቸው ወገን የለም። ወይ አብሯቸው ይዋሻል፣ አሊያም ዝም ይላቸዋል። ጌታቸው ረዳ ውሸት እያወራ መሆኑን እያወቁ አጀንዳ አይጎተቱትም። በሌላው ወገን ያለው ደግሞ ተቃራኒ ነው። እውነት እንኳን ሲያወራ የራሱ ወገን የሚጎትተው ሞልቷል። እየተጠቃ፣ ጠላቶቹ በሀሰት እያጠቁት በመራራው እውነት አንድ አለመሆን ለሽንፈት የሚዳርግ ስህተት ነው።

ለእነሱ ሀሰት ከጥይት በላይ ነው። ከጦር ግንባር በላይ ፕሮፖጋንዳ ማጥቂያቸው ነው። ጠላት ይህን ያህል እየሰራ ታዲያ የራስ እውነት ጋር መጣላትን እንደ ትግል የያዘው፣ የራስን ወገን እውነት እየተናገረም መጎተትን፣ ምክንያት ፈጥሮ መቃረንን እንደ ትግል የያዘ ሌላ ወገን ደግሞ አለ።

ለሀሰት ፕሮፖጋንዳ መሸበር ተደጋግሟል። አሁን ሊታረም ይገባል። ደንደን ማለት ያስፈልጋል። በራስ እውነት ዙርያ መሰባሰብ ደግሞ ትልቁ ቁም ነገር ነው። እነሱ በሀሰት ሲሰባሰቡ በራሳችን እውነት ዙርያ መሰባሰብ ግዴታችን፣ መዳኛችን ነው!