Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ከጠ/ሚ አቢይ ይልቅ መለስ ዜናዊ በብዙ መልኩ የተሻለ ነው" አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በደሴ ሉሲ ሆቴል ላይ የነበርው የወሎ ምክክር በጦርነቱ ዙርያ የተናገሩት

Post by sarcasm » 12 Oct 2021, 09:50

"ጠ/ሚ ዓቢይ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከሹመት ልጧቸዋል። በእርግጥ ባለፈው ደሴ ሉሲ ሆቴል ላይ የትህነግን ወረራ እንዴት እንመክት ተብሎ ወሎየው ሁሉ በአንድ ላይ ሲመከር አቶ ገዱ ስለሆነ ጉዳይ ንግግር ሲያደርጉ ከጠሚ ዓቢይ ይልቅ መለስ ዜናዊ በብዙ መልኩ የተሻለ ነው ብለው ሲናገሩ ደንግጫለሁ። አቶ ገዱ በጠሚ ዓበይ መንግስት አያስፈልጉም ተብለው እንደተገፉ ኋላ ነው መረጃውን ያገኘሁት።

ይሁንና አቶ ገዱ በግለሰብ ደረጃ ሥልጣን ባይሰጣቸውም መቼም እሳቸው አንበሳ ናቸው አማራ ክልል ላይ ግን ሥርዎ መንግስታቸውን ለማስቀጠል ሲለፉ ከርመው ተሳክቶላቸዋል። የአቶ ገዱ ሥርወ መንግስት ከክልል አልፎ በዞን ደረጃ የውሳኔ ሰጭ ሹመቶችን በእጁ አስገብቷል። በክልሉ የሁሉም ዞኖች ሹመት የአቶ ገዱ እጅ አለበት። እስከ ዛሬም የእሳቸው ሥርዎ መንግስት ስለነበረ አሁንም ከሰወቹ መለዋወጥ በቀር የእሳቸው ሥርወ መንግስት ስለቀጠለ አዲስ ለውጥ ይመጣል የተሻለ የመንግስት ሥርዓት ይኖራል ብዬ ተስፋ አላደርግም። ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ ችግሩን መፍታት አይቻልም። አቶ ገዱ ግን የብአዴኑ ስብሀት ነጋ ለመሆን ችለዋል።


Please wait, video is loading...