Page 1 of 1

Re: TWEET: ጌቾ: 1000s OF ABIY'S SOLDIERS PERISHED|TDF በፍፁም አይደፈርም ተብሎ በራሽያ እንጂነሮች የተገነባውን የአምባሰል ተራራ ምሽግ ደረመሰው።ሰራዊቱ ወደ አፋ

Posted: 12 Oct 2021, 03:50
by TGAA
You are right 140 milk vs 6 million the result is a forgone conclusion. Weysnne save us cry is supposedly a tactical move to deceive and ambush with weysnne trade mark offensive KORETA😂
http://aigaforum.com/documents/Tigray-G ... Tigray.pdf

Re: TWEET: ጌቾ: 1000s OF ABIY'S SOLDIERS PERISHED|TDF በፍፁም አይደፈርም ተብሎ በራሽያ እንጂነሮች የተገነባውን የአምባሰል ተራራ ምሽግ ደረመሰው።ሰራዊቱ ወደ አፋ

Posted: 12 Oct 2021, 08:19
by TGAA
Silly boy the movie has already started get your popcorn handy and enjoy the end of weysnne's sordid show. Once weysnne is out of other regions and it's military muscle is e shambles the final blow comes from Tigran people. Haven't Told you wait till the end of the rainy season. Here we are.
የመከላከያ ሰራዊታችን በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ግን ሕወሓት “ተጠቃሁ” ብሎ ለመናገር እንኳ ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት። – ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
October 12, 2021 –
ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ።

የጁንታው የድረሱልኝ ጥሪ …

አሸባሪው ህወሃት በሰጠው አሁናዊ መግለጫው… “…የኢትዮጵያ ሠራዊት በአነስተኛ ወይም ትናንሽ ማጥቃት ሲፈፅም የቆየውን አሁን ላይ በከባድ መሳሪያ፣ በአየር ኃይል ታግዞና ሁሉንም የፀጥታ ኃይሎች አቀናጅቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ነው።…” ይላል።

የጦርነቱን ዓላማ ሲገልፅም “…በትግራይ ህዝብ ላይ ዳግም ወረራ ለመፈፀም፤ ሰቆቃውን ለማብዛትና ለማጥፋት እንዲሁም ውጊያውን ትግራይ መሬት በማድረግ ሊጨርሰን ነው ” ይላል።

ይህንን ባለበት አንደበቱ “…የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሠራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል…” ይላል።

“ተጠቃሁ” ከሆነ ወደፊትና ወደ ጎን እንቅስቃሴ አለ ማለት ሲሆን፣ “አኮማትሬያለሁ” ግን ተዘርግቶም ሆነ ወደፊት መንቀሳቀስ የማይችል አድርጌዋለሁ ማለት ነው።

ሽብርተኛው ሁልጊዜ ውሸት ቀለቡ ነው፡፡ አንድ ነገር ሲፈልግ መጀመሪያ የሚያቅደው እንዴት ልዋሽ ብሎ ነው ፡፡ ቅጥፈቱ ደግሞ እልም ያለ ከመሆኑ የተነሳ “ይታወቅብኝ ይሆን? ” የሚል ጭንቀት የለበትም ፡፡

የዛሬው ፈሊጥ ደግሞ አይናችሁን ያዙ ላሞኛችሁ ዓይነት ሆኗል ፡፡ ለጋላቢዎቹ “መጠነ ሰፊ ጥቃት” ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ እያለ ሲማጸን ፤ ለሚጋልባቸው ደግሞ “አኮማትሬያለሁ” እያለ መዘላበድ ሆኗል ፡፡

ይህ መንታ ምላስ እራሱ ወሮና አጥቅቶ ህዝብ ያጎሳቆለው ሳያንስ እና ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልሙን በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እና በመላው የፀጥታ ኃይላችን አልሳካ ሲለው፤ በተለመደ ውሸቱ ዓለምን ለማደናገር የድረሱልኝ ጥሪውን ያቀርባል።

“እንጦጦ እንደርሳለን” ያለ ኃይል ፣ ተገልብጦ “ድረሱልን…!” ፡፡ ወሮ “ተወረርን…!” አጥቅቶ “ተጠቃን…!” እያለ ውሸት የማያልቅበት ኃይል ነው።

የመከላከያ ሰራዊታችን በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ግን “ተጠቃሁ” ብሎ ለመናገር እንኳ ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት።

የዚህ አሸባሪ የጁንታ ቡድን ውሸትና ማደናገሪያ እድሜው የመሸበት የቁራ ጩኸት ነው። በመሆኑም ህዝባችን በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስታቸው ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደው ድጋፍ እንዳይለየን እንላለን።

ጥቅምት 01/2014 ዓ.