Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጀፎረ፣ የጉራጌ ማህበረሰብ አሰፋፈርና አከታተም ስልጣኔ

Post by Horus » 24 Sep 2021, 02:18

የቃሉ ስር ገፈረ ወይም ጀፈረ ከሚለው የመጣ ሲሆን ትርጉሙ የተተወ ማለት ነው ። ግፈር፣ ጅፈር ማለት ተው ማለት ነው ። ጀፎረ ለጋራ ማህበራዊ ግልጋሎት የተተወ የወል መንገድ፣ ቦታ፣ መሬት ማለት ነው። ለምሳሌ መሬቱ ተራራማ ወይም አስቸጋሪ በሆነባቸው አካባቢዎች ጀፎረ ጌፎለ ወይም ከቤቶች ርቆም ቢሆብ ለተመሳሳይ የጋርዮሽ ጥቅም የሚወል የግጦሽ፣ የበአል፣ የለቅሶ አደባባይ በሁሉም ጉራጌ አለ ። ይህ ጥንታዊ የመሬት ቅየሳና የጋራ አደባባይ ጽንሰ ነገር አሁን ለዚህ በቅቶ መማሪያ እየሆነ ነው የኬር መስቀር፣ የኬር መስቀል፣ የኬር መስቃን ይሁንላችሁ !!