Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 11789
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

ይድረስ ለታምራት ላይኔ

Post by Selam/ » 23 Sep 2021, 22:08

December 30, 2020

ይድረስ ለታምራት ላይኔ፤ የቁና ገብስና የስኒ ቅቤ ነጻሪ (ቲኦረቲሺየን) – ፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ

ለትውስታዎ እንዲረዳዎ፦

1ኛ. በጭራቁ መለስ ትእዛዝና በገነት እሽክም እሽቅንጥ ባይነት 40ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ስንባረር እርስዎ ውሳኔው ተገቢ መሆኑን ለህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በእርሶ የሚመራ ብሄራዊ ኮሚቴ አቊዋቁመው በደምፍላት በየሚዲያው ሲያስወግዙን ነበር።

2ኛ. በበደኖ በኢንቁፍቱ በአርባጉጉ አማራው በዘር ተለይቶ ሲጨፈጨፍ እርሶ ልብዎ በደስታ ከመጋሉ ብዛት አላስችል ብልዎት አሰላ መጡ። ህዝቡም ከወልኬሳ ወንዝ እስከ አረንጉዋዴው ስታዲየም ድረስ በፈረስ አጅቦ ተቀበለዎ። ስታዲየም ደርሰው ያደረጉት ንግግር እንዲህ ይላል። “ነፍጠኞች እዚህ ምን ሊያደርጉ መጡ? እናንተን ሊጨቁኑ ሊገዙ ሊረግጡ ነው። እና ነፍጠኛ ዛሬስ እዚህ ምን ይሰራል?” ወዘተ የሚል ቀጥተኛ የጄኖሳይድ ቅስቀሳ ነበር።

3ኛ. በአማራው ላይ እየደረሰ የነበረውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ቢቻል ለማስቆም ባይቻል ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ ፕሮፌሰር አስራት ወደድሬዳዋ ሲሄዱ የሶማሌ ህዝብ በታላቅ ሰልፍ ከአውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በማጀብ ደማቅ አቀባበል አደረገላቸው። ያነዜ ኒኦፋሺስታዊ የቀወተ አንደበትዎን በላላዎትና ወደድሬ ሄዱ። እዛም እንደደረሱ። ” አማራን ለምን ትደግፋላችሁ? እኛን የህዝብ ልጆች አባከና ሳትሉ፣ ፕሮፌሰር አስራትን እንደምን በክብርና በፍቅር ትቀበላላችሁ? ነፍጠኞች እኮ እናንተን እንትን ለባሽ ….እንትን እንትን እያሉ ሲጠሩዋችሁ አልነበረም? ” የሚል በስድብ የታጀለ ሰይጣናዊ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ አደረጉ።

4ኛ. የትህነግ አሽከር የነበረውን ኢህዲንን ብአዴን የሚል አዲስ ከፈን ጌታው ትህነግ ያሰፋለት መሆኑን አስመልክታችሁ በባህርዳር ዳንኪራ ስትረግጡ አንድ ታዳሚ ” አማራው በምስራቅ በመሀል እና በደቡባዊ ኢትዮጵያ ሲጨፈጨፍ እኛ ምን ሰራንለት?” ብሎ ሲጠይቅ ” አማራው እዛ ለምን ሄደ? ሊጨቁንና ሊበዘብዝ ነው። እና ለአንተ እዚህ ላለኸው አማራ አንድ ቁና ገብስ እና አንድ ስኒ ቅቤ ልኮልሀል… አሁን ደርሶ ለእሱ የምትከራከርለት?? ” በማለት መለስ ያጎረብዎትን ኒኦፋሺስትነት ሲያስታውኩ ዋሉ።የአማራውን በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ተዘዋውሮና ሰርቶ የመኖር ተፈጥሯዊ ህጋዊና ታሪካዊ መብት የሚገፍ ፋሺስታዊ መርዝ ተከሉ። በዚሁ ስብሰባ ላይ “ከአማራ ክልል ውጭ ያለው አማራ በስብሰባው ለምን አልተወከሉም? ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽዎ ከድንቁርና የመነጨ ከፋሺስቶች የተጫጨ እና “ከአማራ ክልል ውጭ አማራ የለም ። ያለው ነፍጠኛ ነው” የሚል ነበረ።

5ኛ. መተከል ወደቤጉ እንዲከለል የአውራጃውን ህዝብ ወኪሎች በፓዊ ሰብስበው መርዛማ ሰበካ ቢያደርጉም ተሰብሳቢው እምቢ አለ። ሳይወድ በግዱ ለማሳመን ከታደሰ ካሳ ጥንቅሹ ጋር ለሶስት ወር የማያባራ ስብሰባና ዛቻ እስርና ድብደባ በአማራውና በአገው ህዝብ ላይ አደረሱ። ህዝቡ እንዲህም ሆኖ ” እኛ ጎጃሞች ነንና መከለል ያለብን ወደአማራ ነው ” ብሎ ቢል ከፊሉን አሳስረው ከፊሉን አስገርፈው በራስዎ ግዜ መተከል ወደቤጉ እንደከለል አደረጉ። እናም ዛሬ በየቀኑ ለሚታረደው አማራና አገው የመጀመሪያውን ኒኦፋሺስታዊ የመሰረት ድንጋይ ጣሉ።

ይህንን ሁሉ የፈጸሙት በእንዱቅዱቅ ካድሬነትዎ፣ በትህነግ አሳፋሪ አሽከርነትዎ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነትዎ በሰጠዎ ትልቅ ሀገራዊ ስልጣን ጭምር ነው። ቢያንስ ቢያንስ የኢትዮጵያን ህዝብ ባጠቃላይ ፣ የአማራንና የአገውን ህዝብ በተለይ፣ ይቅርታ በይፋ ሊጠይቁ ይገባል!!!!

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ይድረስ ለታምራት ላይኔ

Post by Sam Ebalalehu » 23 Sep 2021, 22:45

Selam, I am very thankful for your posting this informative letter. At the beginning of the TPLF administration I was a struggling student, social media was not as is now, and I missed so many important information. I have not known Tamrat was the number one enemy of Amharas as this letter clearly shows.
If I were him, I keep going to church, and totally avoids giving any political statement to any social media.
But he is an opportunist of the highest degree. He could not do that.
Whenever he feels there is an opportunity to sell himself, he will show up.

Post Reply