ባሁን ወቅት አሜሪካ እያሳየችው ያለው ባህሪ የሃያልነትና ልበ ሙሉነት ሳይሆን የድካሟ ምልክት ነው ። አለም አሜርካንን የተከተለው ከሁሉ የተሻለ የፖለቲክና ኢኮኖሚ ሰርዓት አላቸው በሚል ነበር። ያ አድናቆትም ሆነ እምነት አሁን ፈርሷል። ከዚህ በኋላ ያለው ነገር ሁሉ የካራቦላ ቢሊያርዶ ጨዋታ ነው ። በዚህ ጨዋታ ጠረጴዛ ላይ ከተሰለፉት ጠጠሮች፣ (አገሮች) አንዱ ሲመታ ሌሎቹ ጠጠሮች (አገሮች) ሁሉ የነቃነቃሉ፣ ይሸጋሸጋሉ፣ ቦታቸውን አቋማቸውን ይለውጣሉ ። ይህ ነው የጌም ቲኦሪ አስተምሮት ።
አሜርካ አሁን ከምታደርገው ዘርፈ ብዙ አለም አቀፍ አልሸነፍ ባይ ትግል (ልክ እንደ ወያኔ) ራሷ ተላልጣ በሚቀጥለው አስተዳደር ወደ ኋላ ታፈገፍጋለች ። በዚህ ትርምስ አሸናፊ ሆነው የሚወጡት አገሮች ጽኑ እና ብልህ የሆነ፣ በፍርሃት ሳይርበተበቱ ባገኙት ቀዳዳና እድል ሁሉ በድፍረት ጨዋታውን የሚካፈሉት ናቸው። በተለይ ለኢትዮጵያ ይህ ከፈጣሪ የተላከ እድል ነው ። ገፋ ካለ የሚቀረው የበሰበሰ ስንዴ ነው ። ያ ደሞ ማንኛውም ኢትዮጵያ ለፍቶ፣ ጥሮ ግሮ አፈር ጭሮ በልቶ ማደር እንጂ በፈረጅ የመቀለብ በሽታን ወዲያ ማለት ይኖርበታል ። የኢኮኖሚ እድገት በግዜና በራሱ ህኛ ሂደት ይመጣል ። ኢትዮጵያ አለ እድገት 3 ሺ አመት ኖራለች ። ዛሬ ያለም ሃያላን ብጥብጥ እስኪረጋ የኛ እድገት ቢዘገይ ምንም ማለት አይደለም ።
የኢትዮጵያ አምላክ ጠላትቿን ሁሉ እየበታተነ፣ እያቧጨቀ፣ እየከፋፈለ ነው ! የወደ ፊቱ ነገር ሁሉ ብሩህ ነው ! ቀውስና መራኮት ያለው ባሮጌ የኒዮ ኮሎኒያል ሰራ ውስጥ ነው !!