Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአለም ኢኮኖሚያዊ ጦርነትና የአሜርካ መንፈራገጥ! THE NEW GLOBAL CHAOS!

Post by Horus » 22 Sep 2021, 21:46

ልብ በሉ አሜርካ ያለም ጢቦ ጉልቤ ሆና መቀጠል ስላልቻለች ኢዚህም እዚያ እቀባና ቅጣት እየጣለች ነው ። እቀባ በቻይና፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ኢራን፣ አምሬት፣ ኢትዮጵያ ሌላም ሌላም ላይ ..። ! ለብዙ ልበ ሽብርክና የዲፕሎማቲክ እና ፖለቲካ ትንቅንቅ እውነተኛ ዳይናሚክስ ለማይገባቸው ይህ አለም አቀፍ መፍረክረክ እግጅ ሊያስደነግጣቸው ይችላል !! ትክክለኛው እይታ ግን ይህ አይደለም።

ባሁን ወቅት አሜሪካ እያሳየችው ያለው ባህሪ የሃያልነትና ልበ ሙሉነት ሳይሆን የድካሟ ምልክት ነው ። አለም አሜርካንን የተከተለው ከሁሉ የተሻለ የፖለቲክና ኢኮኖሚ ሰርዓት አላቸው በሚል ነበር። ያ አድናቆትም ሆነ እምነት አሁን ፈርሷል። ከዚህ በኋላ ያለው ነገር ሁሉ የካራቦላ ቢሊያርዶ ጨዋታ ነው ። በዚህ ጨዋታ ጠረጴዛ ላይ ከተሰለፉት ጠጠሮች፣ (አገሮች) አንዱ ሲመታ ሌሎቹ ጠጠሮች (አገሮች) ሁሉ የነቃነቃሉ፣ ይሸጋሸጋሉ፣ ቦታቸውን አቋማቸውን ይለውጣሉ ። ይህ ነው የጌም ቲኦሪ አስተምሮት ።

አሜርካ አሁን ከምታደርገው ዘርፈ ብዙ አለም አቀፍ አልሸነፍ ባይ ትግል (ልክ እንደ ወያኔ) ራሷ ተላልጣ በሚቀጥለው አስተዳደር ወደ ኋላ ታፈገፍጋለች ። በዚህ ትርምስ አሸናፊ ሆነው የሚወጡት አገሮች ጽኑ እና ብልህ የሆነ፣ በፍርሃት ሳይርበተበቱ ባገኙት ቀዳዳና እድል ሁሉ በድፍረት ጨዋታውን የሚካፈሉት ናቸው። በተለይ ለኢትዮጵያ ይህ ከፈጣሪ የተላከ እድል ነው ። ገፋ ካለ የሚቀረው የበሰበሰ ስንዴ ነው ። ያ ደሞ ማንኛውም ኢትዮጵያ ለፍቶ፣ ጥሮ ግሮ አፈር ጭሮ በልቶ ማደር እንጂ በፈረጅ የመቀለብ በሽታን ወዲያ ማለት ይኖርበታል ። የኢኮኖሚ እድገት በግዜና በራሱ ህኛ ሂደት ይመጣል ። ኢትዮጵያ አለ እድገት 3 ሺ አመት ኖራለች ። ዛሬ ያለም ሃያላን ብጥብጥ እስኪረጋ የኛ እድገት ቢዘገይ ምንም ማለት አይደለም ።

የኢትዮጵያ አምላክ ጠላትቿን ሁሉ እየበታተነ፣ እያቧጨቀ፣ እየከፋፈለ ነው ! የወደ ፊቱ ነገር ሁሉ ብሩህ ነው ! ቀውስና መራኮት ያለው ባሮጌ የኒዮ ኮሎኒያል ሰራ ውስጥ ነው !!


Last edited by Horus on 22 Sep 2021, 22:13, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአለም ኢኮኖሚያዊ ጦርነትና የአሜርካ መንፈራገጥ!

Post by Horus » 22 Sep 2021, 22:12

TALK ABOUT GLOBAL CHAOS - LISTEN TO THIS !!


Post Reply