"ጦርነቱን አቁሙና ተደራደሩ" ማለት የምትነጋገሩበት ቋንቋ ጥይት ሳይሆን ሓሳብ ይሁን ነው። መደራደር ማለት የግድ መታረቅ ማለትም አይደለም። በጦርነትም በድርድርም ውድድር፣ ፉክክር አለ። በጦርነትና በድርድር መካከል ያለው ልዩነት፡
በጦርነት ሜዳ በጠመንጃ ነው ምትደባደበው፤ በድርድር ሜዳ ግን በሐሳብ ነው ምትከራከረው። ጨዋታው በጠመንጃ ሲሆን የሚጠፋ ህይወት አለ፣ የሚፈናቀል ዜጋ አለ፣ በር ተዘግቶበት የሚራብ ህዝብ አለ።፣ የሚወድም ንብረት አለ፤ ኢኮኖሚውም ይቃወሳል። በድርድር ሜዳ ግን ሞት፣ መፈናቀል፣ረሀብ፣ ውድመት የለም። ምክንያቱም ሐሳብ አይገድልም፣ ሐሳብ አያፈናቅልም፣ አያስርብም፣ አያወድምም!
"ጦርነት አቁሙና ተደራደሩ" ስል በየአከባቢው የሚጠፋ ህይወት አይኑር፣ ህዝባችን አይፈናቀል፣ የተራበው አስቸኳይ እርዳታ ያግኝ፣ ሀብታችን አይውደም፣ ጥላቻ ተወግዶ ፍቅራችን ተመልሶ ሀገር ሰላም ይሁን ማለቴ ነው።
Please wait, video is loading...