Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ቓልብ ጠይፉር ስለ "የመፈንቅለ-መንግስቱ ሙከራ " ሲናገር ፥ ይህ ጣዕም የሌለው (ሰመጅ) ትያትራዊ ጨወታ ነው ። ....."

Post by Abe Abraham » 21 Sep 2021, 19:45


ነገሩ ለማጣራት ትንሽ ጊዜ ቢያስፈልግም ሱዳናዊ የፖለቲካ ነጣፊ (ናሽጥ/ኣክቲቪስት ) ቓልብ ጠይፉር ስለ " የመፈንቅለ-መንግስቱ ሙከራ " ምን ይላል ?






ቓልብ ጠይፉር ፥ ይህ ጣዕም የሌለው ( ሰመጅ ) ትያትራዊ ጨወታ ነው ። ማን ነው በዚህ የሚታለለው ? የተገለበጠው ማን ነው የሚገለብጠው ? ። ( ብዙ በኣል-በሺር ጊዜ በቁልፍ ቦታዎች የነበሩ ሰዎች እስካሁን እዛ ኣሉ ማለቱ ነው ። ጥያቄው ራስህን መገልበጥ እንዴት ይሆን የሚል ነው ። ) ሁሉ ነገር ፡ ፖሊስ ወታደርና የስለላ ሃይሎች ፡ በእጃቸው እያለ እንዴት ብሎ ነው መፈንቅለ-መንግስት መሞከርን የሚታሰበው ?

በጠይፉር ኣባባል በወታደሮች የሚመራው የሱዳን መንግስት በዚህ " የሽግግር ጊዜ " የተለያዩ ብድሆዎች (ቻለንጅስ) እያጋጠሙት ስላሉ ጣዕምና ሽታ የሌለው ትያትራ ጨወታ ሰርቶ ህዝብን ኣገሪትዋ በከባድ ኣደጋ ትገኛለች ብሎ ኣስታምኖ ስልጣኑን ለማራዘምና ኣዲስ ውክልና ( ተፍዊድ ) እንዲሰጠው ይፈልጋል ። ልክ እንደ ኣል-ሲሲ በግብጽ ያደረገው ማለት ነው ። ይህ ማለት ጸረ-መንግስት የሆነ እንቅስቃሴ ኣልተደረገም ማለት ኣይደለም ። ሁኔታው - የቤትህን በር ከፍተህ እንትናን ገብቶ እንዲሰርቅ ኣደፋፍረው ብለህ ለኣንድ ሰው መምርያ ሰጥተህ ቤቴን ሌባ ገባበትና ሌባውን (የተታለለ) ደሞ በቁጥጥሬ ስር ይገኛል ስትል - የሚመስል ነው ። በትንሹ የጠይፉር ኣስተሳሰብ እንደሱ ይመስላል ። ያ ከሆነ ልክ በልክ ሰመጅ/ዲስተይስፉል የሚል ቅጽል-ስም ይገባዋል ።