Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

"እናቴን ገድለው በጅብ አስበሏት" - የአሸባሪው ህወሓት ግፍ ሰለባ የሆነችው አይሻ ሰይድ

Post by Hameddibewoyane » 21 Sep 2021, 08:10

(ኢ.ፕ.ድ)

አይሻ ሰይድ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪ ናት። በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የደረሰባትን ግፍ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተናግራለች።

"አሸባሪው ህወሓት በአካባቢያችን ላይ ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ያገኘውን ሁሉ መግደል ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪም በመደናገጥ እግሩ ወደመራው ሸሸ። እኔም የ75 ዓመት አዛውንት የሆነችውን እናቴን ይዤ ለመሸሽ ሞከርኩ። ነገር ግን አቅሟ ደከመ ብዙም መጓዝ አልቻለችም። አውሬዎቹ የአሻባሪው ታጣቂዎች ደረሱብን። እናቴን መንገድ ላይ ገደሏት፤ እኔ እንደምንም ብዬ ነብሴን አተረፍኩ" ትላለች አይሻ።

"ሁሌም ሀዘኔ ከውስጤ እንዳይወጣ የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር መተኪያ የሌላት እናቴን እንኳን መቅበር አለመቻሌ ነው" የምትለው አይሻ፤ የእናቷን አስከሬን ጅብ እንደበላው ትናገራለች።

"..እናቴን የሰው ጅቦች ገደሉብኝ። አስከሬኗን ለጅብ ሠጥተው ሄዱ። አስከሬኗን ከሌሎች አስከሬኖች መካከል መለየት እስኪያቅተኝ ድረስ ተቸገርኩ። ....መጨረሻ ላይ በእጇ፣ በፀጉሯና በጥርሷ ለየኋት ..." ያለችን ፊቷ በእንባ ሞልቶ መናገር እየተቸገረች ነው።

"...ከሦስት ወር በፊት አባቴ ታሞ ሞተ ከዘመድ ጋር አልቅሼ ቀበርኩት። ሀዘን ላይ እያለሁ ነው ሌላ ሀዘን የመጣበኝ። እናቴን ግፈኞች ገድለዋት በወጉ አፈር ማልበስ ተሳነኝ።

እኔ እንጃ! እነዚህ የሰው ፍጡር ናቸው ብዬ አላስብም" ስትል ከዓይኖቿ መንታ መንታ ሆኖ በሚወርደው እንባ ጭምር መሪር ሀዘኗን ገልፃለች።