Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ ዋ!

Post by Horus » 17 Sep 2021, 22:55



አሜሪካ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ያላት አላማ ከትግሬ ጋር እንዳልተያያዘ አለም ያውቀዋል ። አሜርካ የአፍሪካን የተፈጥሮ ሃብት ለመቆጣጠርና ለመዝረፍ፣ ቀይ ባህርና ህንድ ውቅያኖስን ይዛ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክና ህንድ ከአካባባዊ ለማስወጣ ባለመችው ግብ ኢትዮጵያ ተላላኪ አሽከር እንደ ማትሆን ስላመኑ ነው። አፍሪካና ቅርብ ምስራቅ በአንድ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ደምሮ በግብጽ ፕሮክሲ አሸከርነት ጥቁር አፍሪካን ለመግዛት ያሰበ ነው ያሜርካ ቅዠት ።

ኢትዮጵያ ደግሞ ከዚህ የተሻለ እድል አጋጥሟት አያውቅም ። ልብ በሉ ! ኬኔዲ ለሃይለ ስላሴ ዲሲ አይደለም ኒው ዮርክ የከተማ ሰልፍ አድርገውላቸዋል ። ነገር ግን ወዳጅነት አይደለም፣ የአሽከርነት ጥያቄ ነበር። ዛሬ አቢይ አህመድ ስለፈለገ ወይ ስላልፈለገ አይደለም ። ስለትግሬ ወይ ስለ ሰው ምብት አይደለም ። ኢትዮጵያ እየገዘፈች ያለች አገር ስለሆነች ኢትዮጵያን አምበርክካ ግብጽን አለተፎካካሪ አፍሪካን እንድትጫን ነው ጨዋታው ። ይህን የማያውቅ አበሻ የለም ።

ትልቁ፣ ትልቁ ጥያቄ እኛ ይህን ወረራ እንዴ እንመልከተው ነው? እኔ ሺ ግዜ ብዬዋለሁ በዲፕሎማሲ ጦርነት ደካማ፣ አጎንባሽ፣ አሽከር አገር ምንግዜም እንደ ተገፋ፣ እንደ ተረገጠ ይኖራል ። ይህ ደሞ በፍጹም የኢትዮጵያዊ ባህሪ አይደለም ። ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ከ1896 ወዲህ ከሰማይ የላከላት ጸጋ ነው ።

በዚህ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ በኋላም ምናልባት በቀጥታ ያሜርካ ወረራ ምን ያክል ጠንካራ፣ ምን ያክል ብረት፤ ምን ያክል የጥቁር ዘር ነጻነት ምልክት እንደ ሆንን የምናረጋግጥበት ዘመን ተሰጥቶናል ።

አንድ ገናና፣ ህዝብ፣ አንድ አገር፣ አንድ መንግስት ሆነን ረሃብ፣ ወረራና ከበባ ሰብረን በዚያውም የአሜርካን ኢምፔሪያሊዝምን በአፍሪካ ምድር አሸንፈን ሁለተኛ የአፍሪካ ነጻነት ትግል መሪ መሆናችንን የምናረጋግጥበት አዲስ ሁለተኛ እድል ተከፍቶልናል፤ ልክ እነ ሚኒልክ ፣ እነ አባ መላ የመጀመሪያውን ያፍሪካ ነጻነት ትግል መሪ እንዲሆኑ ታድለው እንደ ነበረው !

ይህ ነው ዛሬ፣ ለዛሬ ትውልድ እግዚአብሄር የሰጠው የታላቅነት ጸጋ !! ይህን ጸጋ ነው ይህ ትውልድ በፍጹም ደስታና ጀግንነት ተቀብሎ ለዘመቻ መዝመም ያለበት!! ታላቅነት የሚወለደው ከፈተና እንጂ ከማጎንበስ ፣ከመንበርከክ አይደለም ። እኛ ብንፈልግ እንኳን አሜርካ ለማድረግ የወሰነው ከማድረግ በልመና አናስቆመውም ። በትግል ነው ከኢትዮጵያም ካፍሪካም የምናባርረው !

አሁን ምን ያደርጋል ፈሪ ማቀንቀኑ አይበጠስ ቅጠል ካልደረሰ ቀኑ እንዲል !!

ኢትዮጵያ ድል አድራጊ! ኢትዮጵያ አይነኬ፣ አይበገሬ !!!