Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12528
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Read : ገለልተኛው አክቲቪስት ሰለ ጦር ሜዳው ውሎ ምን አለ ?

Post by Thomas H » 17 Sep 2021, 13:55

Haileyesus Adamu
3h ·
ሰላም ጤና ይስጥልኝ!

ሰላም ጤና ይስጥልኝ!
ሁላችሁም እንደምታውቁት ይህ ጦርነት ከትግራይ ክልል ወጥቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ከተዛመተ ሁለት ወር በላይ ሆነው።
በብአዴን በሳል አመራር ፣ በጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ፣ በአይበገሬው መከላከያ ፣ በደፋሮቹ የአማራ ሚሊሻዎች ፣ በነበልባሎቹ ፋኖዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ጀኔራሎቻችን አንፀባራቂ ድል አላማጣና ኮረም ላይ የተደመሰሰው የህውሃት ሀይል ወደ ቆቦ ራያ ሸሽቶ ገብቷል። ቆቦ ላይ ገብቶ የነበረው የህውሃት ወራሪ ሀይል ከላይ በተጠቀሱት ጀግኖች መፈናፈኛ ሲያጣ ወደ ግዳን እና ላስታ ፈርጥጦ ሂዷል።
የተወሰነው ሀይሉ ተከዜን አቋርጦ ጠለምት ማይፀብሪ ቢገባም አሁንም በአማራ ክልል በሳል አመራሮች በአማራ ልዩ ሀይልና በመከላከያ ጥምረት ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል ። በርግጥ ጥቂት የተረፈው ሀይል ከማይፀብሪ ሸሽቶ አዲአርቃይ ገብቷል። አዲአርቃይና ዛሬማ ላይ በአይበገሬዎቹ ፋኖዎች በአማራ ልዩ ሀይልና በመከላከያ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ ቢሆንም የተወሰነ ሀይሉ በዳባትና ደባርቅ መካከል ቆርጦ ገብቷል። መደምሰሱ ግን አይቀሬ ነው።
ላስታ ገብቶ የነበረው የህውሃት ሀይል ሙሉ በሙሉ ቢደመሰስም የተወሰኑ ሀይሎቹ አሁንም ድረስ ላሊበላ አሉ። ቀሪው የተደመሰሰ ሀይል ወደ ዋግ ሸሽቶ ሂዷል። ጁንታው ሙሉ በሙሉ ቢደመሰስም የተወሰነ ሀይሉ ሰቆጣ ላይ እየተቅለበለበ ነው። አሁን ላይ ይህ የተደመሰሰው፣ ለወሬ ነጋሪ ያልተረፈውና እምሽክ የተደረገው ሀይል ርዝራዦች በወረባቦ በኩል ሾልከው በመግባት ወደ ሀይቅ ደሴና ኮምቦልቻ እየተጠጉ ነው። በርግጥ እነዚህ የተደመሰሱ የህውሃት ሀይሎች ደሴና ኮምቦልቻ ላይ ድንገት ሰርገው ቢገቡ እንኳ አሁንም መደምሰሳቸው አይቀሬ ነው። ከተደመሰሱ በሁዋላም ወደ አዲስ አባባ ይገሠግሣሉ ግን አሁንም መደምሰሳቸው አይቀርም።