Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
sarcasm
Member
Posts: 4183
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የእኔና የአንተ ልዩነት By Dr. Binyam ZeChristos

Post by sarcasm » 12 Sep 2021, 18:45

#የእኔና_የአንተ_ልዩነት

√ ያኔ ሲጀመር፣ "ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጠረ የተባለው ነገር ተጣርቶ ወንጀለኛው ይጠየቅ" ብዬ ስልህ፣ አንተ ግን "ትግራይ መመታት አለበት" ብለህ ለጦር እጅህን ያነሳህ የጦር ሰው ነህ።

√ "ሕዝብና ፓርቲ ይለያያል" ብሎ የመጣው የብልጽግና ሠራዊት እግሩ እንደገባ ፓርቲን ትቶ ሕዝቡን እየገደለና እያረደ መሆኑን በመረጃም በማስረጃም ነገርኩህ። አንተ ግን "ከመከላከያ ጎን ጋር እቆማለሁ" ብለህ በመጮህ ከደም አፍሳሾች ጋር መቆምህን ነገርከኝ።

√ "የአማራ ልዩ ሐይል ከትግራይ መውጣት እንዳለበት፣ የመሬት ጥያቄ ካለበትም በጠረቤዛ ዙርያ ያድርገው እንጂ እንደ አረመኔ ተጋሩን ገድሎና ጨፍጭፎ የሚወስደው ቦታ የለም" ብዬ ስልህ፣ መሬታችን ስለሆነ እንወስደዋለን ብለህ የደነፋክ፣ ግን ደግሞ ሱዳን የአማራን መሬት "መሬቴ ነው" ብላ ስትወር "እንዴት በሃይል መሬት ይወረራል?"' ብለህ የምታለቅስ ማበድህን ያላወቅህ ሰው ነህ።

√ ሕዳር 19 ቀን ብልጽግና መቐለ ሲገባ፣ ከተማውን እንዴት ባለ ከባድ መሣርያ ሲደበድባት እንደዋለና ብዙ ንጹሓን ዜጎች ደማቸው ፈሶ ሰውነታቸው ተቆራርጦ እንደሞተ የዓይን ምስክር ሆኜ ነገርኩህ። አንተ ግን ከዚያ ይልቅ "በገብርኤል በዕለተ ቀኑ መቐለ ተያዘች" ብለህ የፈሪሳዊነትህን ጥግ የመሰከርክ፣ "አንድ ሰው ሳይሞት ነው መቐለ የገባነው" ለሚለው ዜና ያጨበጨብክ ምስኪን ሰው ነህ።

√ የእህቶቼን በአሲድ መቃጠል በሺድዮ ሳሳይህ፣ የእናቶቼን መደፈር በፎቶ ሳስረዳህ፣ የህፃናቶች ሰውነት መቆራረጥ ከራሳቸው ከገዳዮቹ ወታደሮች አንደበት እንካን እያሰማሁህ፣ በኢትዮጵያዊነት ወግ "ያሳዝናል፣ እውነት ከሆነ ይህንን አወግዛለሁ" የምትልበትን አቅም አጥተህ "ውሸት ነው! የህወሐት ፕሮፓጋንዳ ነው" ብለሀኝ ያረፍከውና ሰውነትህን እንድጠረጥረው ያደረከኝ ሰው ነህ።

√ የሻዕብያ ወታደሮች ጨዋ እህቶቼን ለ10 ሲደፍሯቸው፣ ብልታቸው ውስጥ ሚስማርና ድንጋይ ሲከቱበት፣ ቤት እያቃጠሉ ማንካና ሹካ ሲሰርቁ ለምን ዝም እንዳልክ ስጠይቅህ፣ የዓለም ሚድያዎች እንኳን የተቀበሉትን እውነት "የኤርትራ ወታደሮች አልገቡም" ብለህ የሸመጠጥከኝ፣ መንግስት ራሱ ሻዕብያዎች መግባታቸው ሲያምን ደግሞ "ራሳቸውን ለመከላከል ነው የገቡት" ብለህ በእህቶቼ ላይ ያፌዝክ፣ ካንተ ጋር እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ በመጠራቴ እንዳፍር ያደረከኝ ማፈርያ ሰው ነህ።

√ የብልጽግና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ መከላከያ ሠራዊት (TDF) ተቀጥቅጦ ነው ከትግራይ የወጣው ብዬ የተማረኩትን የሠራዊቱ የበላይ አመራሮችን ምስክር አድርጌ ነገርኩህ፣ አንተ ግን አሁንም "የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ" ፣ አልያም "የፅሞና ጊዜ ለመስጠት ነው" ብለህ የምታስብ ድኩም፣ ሠርዊቱ እንኳን እንዲያ ብሎ ቢወጣ በዓብዪ የተሾሙት ጊዜያዊ ኣመራሮች ለምን እንደፈረጠጡ እንኳን መጠየቅ ያቃተህ ምስኪን!

√ አንተኮ በትግራይ የተማረኩትን ከ10,000 በላይ ወታደሮች መንገድ ላይ እንደ በግ ሲግተለተሉ ኣይተህ "የታላቁ ሩጫ ከሆነ ሀገር ኣምጥታችሁ ሬንጀር ልብሳቸውን ደግሞ ኢዲት አድርጋችሁ ነው እንጂ የተማረከ የለም" ብለህ በራስህ ላይ ይምታሾፍ ሰው እኮ ነው! ይህንን ጭንቅላት የተሸከመውን የአንገትህን የትዕግስቱን ፅናት አደንቃለሁ!

√ ባንተ ጭብጨባና ድጋፍ ተጋሩን ለመጨፍጨፍ የመጡ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ግን ደግሞ የተማረኩ ወታደሮችን በረሃብ ከደረቀው ጉሮሮኣችን እያበላንና እያጠጣን እንደሆነ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም ያለንን አብስለን እንኳን እንዳንበላ "ለትግራይ መብራትና ስልክ እንዳይለቀቅላት" ከሚሉት ዘንድ ተሰልፈሃል።

√ እኔ በምግብ እጦት ምክንያት ስንት ሰው እየረገፈ እንደሆነን እርዳታዎች እንዲገቡ የቻልከውን እንድታደርግ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም "እርዳታውን ህወሐት ልትወስዱው ትችላለችና ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ መቅረብ የለበትም" ብለህ፣ አሁንም በተጋሩ ሞት ልትረማመድ መሻትህን ገለፅክ።

√ አንተ ህወሓት እንዲጠፋ ትጸልያለህ፣ እኔም ብልፅግና እንዲደመሰስ እሻለሁ። ምኞታችን ባልከፋ፣ አንተ ግን ህወሐትን ለማጥፋት አስፉላጊ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለህ የተጋሩን መጨፍጨፍ Justifiy ለማድረግ ትደክማለህ፣ እኔ ግን ብልጽግናን ለማጥፋት የአንድም አማራም ሆነ ኦሮሞ ወንድሜ ደም እንዲፈስ አልፈቅድም!

By Dr. Binyam ZeChristos (Member of Mahbere Kidusan)

https://www.facebook.com/permalink.php? ... 0385873052

Post Reply