Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ ግዙፍ የጦር ሃይል እየገነባች ነው - ጠ/ሚ አቢይ አህመድ

Post by Horus » 11 Sep 2021, 22:06

እኔ ሆረስ ይህ ግዙፍ የሚለው ቁጥር 1 ሚሊዮን ስለው ነበር !! ይህ ደሞ ለጆሪዬ ሙዚቃ ነው! ትንሽ ጦር ይዘን ትልቅ አገር ማቆም አንችልም! ትንሽ ጉልበት ላይ ቆመን ትልቅ ዲፕሎማሲ መታገል አንችልም ! የአንድ አገር ዲፕሎማሲያዊ ጉልበት በጦር ሃይሏ ልክ የተሰፈረ ስለሆነ ! ኢትዮጵያ እንደ ሱዳን ባለች ባረብ ድጎማ በምትኖር አገር እየተደፈርን የመላ አፍሪካ መሪ መሆን ቀርቶ ድምበሯን እንኳ ማስከበር አትችልም ። ግዙፍ የጦር ሃይል መፈለጋችን የመጀመሪያ የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ፤ ማለትም አንድነቷ የጸና፣ ጠንካራ፣ እስቴብለ ኢትዮጵያ ! አንድ ሕዝብ፣ አንድ አገር፣ አንድ መንግስት፣ አንድ ሰራዊት !! ሌላው ልቤን ያሞቀው ነገር፣ ጠ/ሚሩ ሽፍታው ዉጊያ መለማመጃችን ነው ያለ እጅግ ትክክል እና እኔ እዚህ ፎረም ላይ ደጋግሜ ብዬዋለሁ ። ለነሱዳንና ግብጽ እና ደጋፊዎቻቸው መላክ የሚቻለው አጭር መልክት ያ ነው ። የአንድ ሳምንት የሜዳ ጦርነት ጌም ሳይሆን ሙሉ አመት በሰሜን ተራሮችና በረሃ ሸለቆዎች የምር ዉጊያ እያደረገ ያለው ያበሻ ጦር ለወዳጅም ለጠላትም ፣ ለሃያሉም ለትንሹም ህያው መልክት እየሰጠ ነው ።

የድል አዲስ አመት ለጦሩ !!!