Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12618
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

እልልልልል......በአዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን የጦር ሜዳው ውሎ ምን ይመስላል ?

Post by Thomas H » 11 Sep 2021, 11:13





























ምርኮኞቻችንን ስናጓጉዝ













Selam/
Senior Member
Posts: 11851
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: እልልልልል......በአዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን የጦር ሜዳው ውሎ ምን ይመስላል ?

Post by Selam/ » 11 Sep 2021, 11:29

Kichamam Mujahideen - ቅዱስ ዮሐንስ እንዴት ዋለ? የጤፉን ሊጥ አበሰላችሁት ወይስ ጥሬውን ቀረጠፋችሁት? Remember how Mujahideen celebrated the new year in Addis five or 10 years ago? ገና አርህ ይጠማሃል። ክፉ!
Thomas H wrote:
11 Sep 2021, 11:13




























ምርኮኞቻችንን ስናጓጉዝ













Thomas H
Senior Member
Posts: 12618
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: እልልልልል......በአዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን የጦር ሜዳው ውሎ ምን ይመስላል ?

Post by Thomas H » 11 Sep 2021, 18:54

ጀግኖቹ ወንድም እና እህት ሰቆጣን ነፃ ካወጡ በኋላ







Dimtsi Weyane አማርኛ
7h ·
ሰበር የድል ዜና
ጀግናው ሰራዊታችን ባስፈለገው ጊዜና ቦታ እየመረጠ የትኛውም ቦታ ይቆጣጠራል ብለን በገለፅነው መሰረት የጠላት ፋሽስት ኃይሎሎች በመደምሰስና በመበታተን የዋግ ኽምራ ዋና ከተማ የሆነችውን የሰቆጣ ከተማን ጨምሮ ሐሙሲት፣ ወለኽ ማርያም፣ ቡጉና ከተሞችን መልሶ ተቆጣጥሯል።
©©©©©©©©©©©©©©©©
ጀግናው ሰራዊታችን የጀመረውን መጠነ ሰፊ ማጥቃት በመቀጠል ታላላቅ ድሎችን አስመዝግቧል። ጠላት ከደቡብ ወሎ ወገል ጤና ከ3800 ሜትር በላይ ከፍታ ያላቸው ስትራተጂካዊ ቦታዎችን በመያዝ በስሪንቃ አቅጣጫ በሳንቃና ድልብ አድርጎ ወልደያን ለመቆጣጠር የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጀግና ሰራዊታችን ፀረ ማጥቃት መጀመሩን በገለፅነው መሰረት ጀግናው ሰራዊታችን ማጥቃቱን በመቀጠል ከጳግሜ 3 እስከ 5–2013 ዓ/ም ለተከታታይ ሦሥት ቀናት በቀበሮ ሜዳ፣ ተረፌና አሁን ተገኝ አካባቢዎች የነበረ 11ኛ፣21ኛ፣ 30ኛ እና 52ኛ የፋሽሽቱ አብዩ ክፍለ ሰራዊቶች አብዛኛው ኃይል ተደምስሶ የተቀረው ደግሞ ተበታትኗል። በነዚህ አካባቢዎች የነበረ የጠላት ኃይል ጀግናው ሰራዊታችን በሦሥት አቅጣጫ መግቢያና መውጫ እንዳይኖረው በማድረግና በመቁረጥ 5744 የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጪ አድርጓል።
በዚህ ስኬታማ ፀረ ማጥቃት 2515 ሙት፣ 3131 ቁስለኛ፣ 398 ደግሞ ምርኮኛ ሆኗል። 1 ቢኤም 21ሚ,ሜ ሮኬት፣ ሦሥት 122 ሚ,ሜ መድፍ፣ 2 ዙ23፣ በመቶዎች የሚቆጠር ዲሽካ፣ ብሬን፣ በሺዎች የሚቆጠር ክላሽና ተተኳሽ፣ በመቶዎች የሚቆጠር ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ መገናኛ ሬድዮዎች እንዲሁም 18 ተሽከርካሪዎች የሰራዊታችን ንብረት ሆኗል። በተጨማሪም 9 ተሽከርካሪዎች ጋይተዋል።
በሌላ አቅጣጫ ከጎንደር በአዲስ ዘመን ወደ ሰቆጣ የተንቀሳቀሰ ቴዎድሮስ፣ ሚኒሊክ፣ መቅደላ፣ ጋፋት የተሰኙ አራት የአማራ ልዩ ኃይል ብርጌዶች አንድ ክላሽ ለአምስት አስይዞ ያሰማራቸው፣ እንዲሁም ፋስ፣ ገጀሞና ገጀራ ይዘው የዘመቱ በሺዎችዎች የሚቆጠር የአማራ ኃይል፤ ሰራዊታችን ያደረገውን ውስን የቦታ ማሻሻያ ተጠቅሞ ከሰቆጣ ወደ ላሊበላ በመንቀሳቀስ በደብረ ዘቢጥ አካባቢ ያለው ኃይላችን ለማጥቃት የመጣው የጠላት ኃይል እንዲደመሰስና የተቀረውም እንዲበታተን አድርጓል።
ደጋግመን እንደገለፅነው ጠላት እየተጠቀመበት ለሚገኘው ደማዊ የጦርነት ስልት ግምት ውስጥ በማስገበት ለወታደራዊ ስራችን ባለው ትርጉም እየተመለከትን በውስን ቦታዎች ላይ ማሻሻያ ማድረጋችን የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ አስፈላጊ ነው ባልንበት ጊዜ የትኛውንም አካባቢ ተመልሰሰን መያዝ እንደምንችልም ገልፀን ነበር። በዚህም መሰረት ጀግናው ሰራዊታችን በዚህ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ የነበረውን ጠላት በመደምሰስና በመበታተን የዋግ ኽምራ ዋና ከተማ የሆነችውን የሰቆጣ ከተማን ጨምሮ ሐሙሲት፣ ወለኽ ማርያም፣ ቡጉና ከተሞችን መልሶ ተቆጣጥሯል።
ጀግናው ሰራዊታችን በዚሁ አቅጣጫ የጀመረውን ፀረ ማጥቃት አጠናክሮ በመቀጠል ከቡጉና ወደ አዲስ ዘመን እና ከሰቆጣ ወደ በለሳ በሚወሰወዱ አካባቢዎች እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት እግር በእግር በመከታተል እየቀጠቀጠ ዘመቻውን ቀጥሏል። የዚህ ዝርዝር ሪፖርት በቀጣይ እንደሚቀርብ የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ ያሳውቃል።
የ2014 አዲስ ዓመት በወርቃማ ድል ተጀምሯል። ተጠናክሮም ይቀጥላል።
ትግራይ ትስዕር !!
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ
መስከረም 1/2014 ዓ/ም

Post Reply