Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

30 በመቶ የኢትዮጵያ ክልሎች ጦርነት ላይ ናቸው፤ ይህም ሀገሪቱ ወደማንችለው ጉዳት እወሰዳት ነው-የኢዜማው አቶ አማንይሁን ረዳ

Post by sarcasm » 09 Sep 2021, 06:38

የሰሜኑ የሀገሪቱ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ምን አይነት ጫና እያሳደረ ነው?

30 በመቶ የኢትዮጵያ ክልሎች ጦርነት ላይ ናቸው፤ ይህም ሀገሪቱ ወደማንችለው ጉዳት እወሰዳት ነው- አቶ አማን ይሁን ረዳ
አል-ዐይን



የመንግስት በጀት የጦርነት ወጪዎችን ለመሸፈን እየዋለ መሆኑ ጦርነቱ ያልተካሄደባቸውን ክልሎች ሳይቀር ይጎዳል ብለዋል

በትግራይ ክልል የነበረው የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ልዩ ሀይል መጠቃቱን ተከትሎ ነበር ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት የገባችው።

ይህ ጦርነት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታስቦ ቢጀመርም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተካሂዶ የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ መውጣቱ ይታወሳል።

መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ የትግራይ ህዝብ ያልተቆራረጠ የሰብዓዊ ድጋፎችን እንዲያገኝ እና አርሶ አደሮች ወደ ክረምት የግብርና ስራ እንዲመለሱ በሚል ከትግራይ ለመውጣቱ በምክንያትነት ስቀምጧል።

ይሁንና አሁን ላይ ጦርነቱ ከተግራይ በተጨማሪ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተዛምቶ እድሜው ለጦርነት የደረሰ እና የጦር መሳሪያ ያላቸው ዜጎች ወደ ጦርነት እንዲገቡ በርካታ ክልሎች የክተት አዋጆችን በማሰማት ላይ ናቸው።

ቶ አማንይሁን ረዳ በሙያቸው የንግድ አማካሪ ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያም ተሳታፊ ናቸው። እሳቸው እንዳሉት አሁን ላይ 30 በመቶ የኢትዮጵያ ክልሎች ጦርነት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ጦርነቱ ሰብአዊ ጉዳቱ እንዳለ ሆኖ ልንወጣው ወደማንችለው ጉዳት እየወሰደን ነው ብለዋል።

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጦርነት የሚሸከም አይደለም የሚሉት አቶ አማን ይሁን በዓለማችን ላይ ከተካሄዱ ጦርነቶች በስምምነት ያልተፈታ ጦርነት ባለመኖሩ ወደጦርነት የገቡ አካላት ወደ ስምምነት እንዲመጡ አሳስበዋል።

በጦርነቱ ለምነን እና ተበድረን የገነባናቸውን መሰረተ ልማቶች እያሳጣን ነው፤ ጦርነቱ በመቀጠሉ ምክንያት ተጨማሪ ጉዳት ላለማስተናገዱ ምንም ዋሰትና የለንም እና ስምምነት የግድ መሆን አለበት ብለዋል።

“ወቅቱ የግብርና ስራዎች የሚከናወንበት ዋነኛው የእርሻ ስራ ነው፤ ለስራ ዝግጁ የሆነ እና ማምረት የሚችል ወጣት ደግሞ ወደ ጦርነት እየተመመ መሆኑ ዜጎቻችንን ከማሳጣት አልፎ በኢትዮጵያ የምርት እጥረት እንዲፈጠር እንደሚያደርግም” አቶ አማንይሁን ተናግረዋል።

“ወትሮም ቢሆን በብዙ ምክንያቶች እየተፈተነ ያለው ኢኮኖሚያችን ወደተራዘመ ጦርነት መግባቱ እንደ ስንዴ እና መሰል የግብርና ምርቶችን ከውጭ እያስገባች ኢኮኖሚዋን የምትደጉምን አገር ትልቅ ኪሳራ ላይ ይጥላል” ሲሉም አክለዋል።

Continue reading https://am.al-ain.com/article/north-eth ... mic-impact

አል ዐይን አማርኛ ይህ በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት ወዴት ያመራል? ምንስ አይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል? ሲል የፖለቲካ-ኦኮኖሚ ምሁራንን ጠይቋል።