Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆረስ፣ የእንቁጣጣሽ ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ ለምትፈልጉ!

Post by Horus » 09 Sep 2021, 21:54

ናጋ ቱማ፣
አንተንም እንኳን አደረሰህ!
ስለ ክረምት (ክርማን እንለዋለን) ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ። አንድ ጥያቄ አለኝ? በቦረና የእንቁጣጣ ማለዳ፣ ሲነጋጋ ወንዝ ሄዶ የመጠመቅ ባህል አለወይ? ከዚያ ሌላ ባብዛኛው ያልከው መሃል አገርም አንድ ነው ። ኬር!


Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11717
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ሆረስ፣ የእንቁጣጣሽ ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ ለምትፈልጉ!

Post by Noble Amhara » 10 Sep 2021, 13:46

Engicha is celebrated on both sides of the Abay River (Gojam and Western Shewa) it is practiced by ancient peoples of central Ethiopia I believe south of gojjam the gaffat people celebrate Engicha the same time gojames do. Do Ambo Wonchi Holeta and Gurage people also call Addis amet “Ingicha”


Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆረስ፣ የእንቁጣጣሽ ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ ለምትፈልጉ!

Post by Horus » 10 Sep 2021, 14:17

ኖብል አማራ፣
የጎጃም እንጊጫ ባህል ቪዲያ በማጋራትህ እናመሰናለን ! ወብ ነው ! በኛ አካባቢ ራሱ አዲስ አመት እንጊጫ አይባልም። እንጊጫ የሚባለው ሳሩና ከሳሩ እንደ አበባና መስቀል የሚሰሩት ናቸው ። የሴቶች አበባ ለቀማውና ከቤት ቤት እየዞሩ አበቤ፣ አበቤ የሚባለው እጅግ ደስ የሚል ዘፈን እየዘፈኑ ያበባ ስጦታ የሚሰጡበት ባህል አንዱ ትልቁ የእንቁጣጣሽ ባህል ነው ። በሰሜን ጉራጌ አዲስ አመት እለት አክራሚ ይባላል። ጋፋቶች በቋንቋ ወንድሞቻችን ነበሩ (የክስታኔ ጉራጌና ጋፋትኛ ይግባቡ ነበር)፤ ስለዚህ በባህልን መመሳሰል የነበረባቸው ይመስሉኛል ። እኔ ደጋ ዳሞት ጎጃንን አላውቀውም፣ ባህሎች መወራረስ ለማስተዋል ማለት ነው ። በጋፋት ቋንቋም አዲስ አመት ምን እንደሚባል የሚነግረን ሰው ቢኖር ደስ የሚል ነው ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5546
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሆረስ፣ የእንቁጣጣሽ ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ ለምትፈልጉ!

Post by Naga Tuma » 10 Sep 2021, 22:39

Horus wrote:
09 Sep 2021, 21:54
ናጋ ቱማ፣
አንተንም እንኳን አደረሰህ!
ስለ ክረምት (ክርማን እንለዋለን) ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ። አንድ ጥያቄ አለኝ? በቦረና የእንቁጣጣ ማለዳ፣ ሲነጋጋ ወንዝ ሄዶ የመጠመቅ ባህል አለወይ? ከዚያ ሌላ ባብዛኛው ያልከው መሃል አገርም አንድ ነው ። ኬር!
ሆረስ፣

ጊዜ ኣጥሮኝ ነዉ ሳልመልህ የዘገየሁኝ።

የእንቁጣጣሽ ቀን ወንዝ ሄዶ መታጠብን ኣላስታዉስም።

ቦረና ያልኩኝ ከቦረና ጎሳ ወደ መሃል የመጡትን ነዉ። የሰማሁኝ ኣፈታሪክ ሊበን የሚባል ሰዉ ከሶስት ባለቤቶቹ ጋር መጥቶ ወልሶን፣ ኣመያን፣ እና ኩታዬን ከእያንዳዳቸዉ ወለደ የሚል ነዉ። በጥናት ኣላረጋገጥኩም። ማረጋግጡ ግን ከባድ ኣይመስለኝም፤ ክአምስት መቶ ዐመታት የማይርቅ ስለሆነ።

Post Reply