Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 24 Aug 2021, 20:42

Obviously the general public prefers the current conflict to stop and the problems to be resolved in negotiation table. But is there a peace lobby in Ethiopia? Is it bigger than few people here and there ?
Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 25 Aug 2021, 18:58

It seems that the peace lobby is alive in Ethiopia. I really admire Dr Wedajeneh's brave speech.



sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 14 Sep 2021, 08:00

ድርድር ብናውቅበት ጦርነት ውስጥ አንገባም ነበር። ድርድር ብናውቅ እኮ ጦርነቱ አይራዘምም ነበር። ድርድር ብናውቅ ...

ዓለማችን ሰፊ የመደራደሪያ መድረክ ናት ይባላል። እኛም ብንወድም ባንወድም ተደራዳሪዎች ነን።
ሁላችንም የሆነ ፍላጎት አለን። አንዳንዴ ፍላጎቶቻችን ግጭት ውስጥ ይከቱናል። ቤት ውስጥ በሪሞት የሚጣሉ ልጆች አልገጠሟችሁም? በተራ የሚጣሉ የታክሲ ሾፌሮችስ? በሃሳብ የሚጋጩ ፖለቲከኞችስ?
የግጭት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች ብዙ ናቸው።
ለመሆኑ የምንፈልገው ምንድን ነው?
ሰላም፣ ጤና፣ ነጻነት፣ ፍትህ፣ ፍቅር፣ ተሰሚነት፣ ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ክብር፣... ምን ትፈልጋለህ? አንዳንዶች እነዚህን እንዴት እንደሚያገኙ ከሌሎች በተሻለ ያውቃሉ። ይህንን የሚያውቁት ጥሩ ተደራዳሪዎች ናቸው።
ድርድር ብናውቅ እኮ ድሃ አንሆንም ነበር። ድርድር ብናውቅበት ጦርነት ውስጥ አንገባም ነበር። ድርድር ብናውቅ እኮ ጦርነቱ አይራዘምም ነበር። ድርድር ብናውቅ ...
ሰው ከባለቤቱ፣ ከልጆቹ፣ ከወንድሞችና እህቶቹ፣ ከወላጆቹ፣ ከጎረቤቱ፣ ከትራፊክ ፖሊሱ፣ ከአለቃው፣ ከአበዳሪው፣ ከስፖንሰሩ፣ ከቀበሌ ኃላፊ፣ ከአከራዩ፣ ከሠራተኛው፣ ከጓደኞቹ፣ ... ይደራደራል።
አውቀንም ይሁን ሳናውቀው ሁሌም እንደራደራለን። የደመወዝ ጭማሪ ይሁን የግዢና ሽያጭ፣ አለያም የመኪና ቅድሚያ ልለፍ ወይም የቢሮ ቦታ ምርጫ ብቻ በአንድም በሌላ ድርድር ውስጥ ነን።
ለመሆኑ መደራደር ትችላለህ? በድርድር ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
ድርድር በዋነኛነት በ3 ጉዳዮች ዙሪያ ይሽከረከራል፣ በመረጃ፣ በጊዜ፣ እና በኃይል ዙሪያ።
፩) መረጃ :- ስለተደራዳሪውና በድርድር ስለተነሳው ጉዳይ ከሌላው ተደራዳሪ የተሻለ መረጃ ያለውና ስስ ብልቱን ያወቀውና ያንን ነጥብ በድርድሩ የሚጠቀምበት ከድርድሩ የበለጠ ውጤት ይዞ መውጣት ይችላል።
ለምሳሌ የግዢ ክፍያ ውሳኔ ላይ እንዴት መደራደር እንዳለብህ ታውቃለህ? እቃህን ከስንት በታች መሸጥ እንደሌለብህ ታውቃለህ?
፪) ጊዜ :- የጊዜ እጥረት ያለበት ተደራዳሪ ከሌላኛው ወገን በድርድሩ ያነሰ ውጤት ይዞ ለሙውጣት የተጋለጠ ነው። የጊዜ ጥበት ወይም ማዘግየት ሲገጥመህ ምን ታደርጋለህ?
ገና ከመጀመሪያው ያለ አግባብ እንዳትጎዳ እና እንዳትሰምጥ መረማመጃ ነጥቦችህን በተገቢ ቦታዎች እያስቀመጥህ መሄድህን አትርሳ።
ጊዜህን በተልካሻ ጉዳይ በልተው ጫና ውስጥ ሊከቱህ ሲሉ በጊዜ አማራጭህን ፈልግ።
፫) የኃይል/ዓቅም ጉዳይ :- ዓቅምህ ደካማ ከሆነ ተደራዳሪህ በሚፈቅድልህ ልክ ብቻ ልትሄድ ትገደዳለህ። ዓቅም ግን የእይታ ጉዳይ ነው።
ለምሳሌ ያንተ ከፋይ የሆነው ሰው እርሱም የባንክ እና የአበዳሪ ጫና አለበት። በዚህ ከፋይህ ቢሆንም በሌላ በኩል የባንክ ብድሩን ለመክፈል የጊዜ ጫና አለበት።
ለክፍያ ድርድር ከፋይህ ለምን እንደፈለገህ እወቅ?
ደካማነት ከተሰማህ ደካማ ነህ። ለድርድሩ ስትገባ ጥንካሬ ያለህ መስሎህ ከተሰማህም እንደዚያው ለተደራዳሪህ ጠንክረህ ትታያለህ።
ድርድር በጊዜ፣ በገንዘብ፣ በዓቅም ወይ በመረጃ ዙሪያ መደረጉን አውቀህ ከድርድር በፊት በቂ ዝግጅት አድርግ።
ከዛሬ 2000 ዓመት በፊት የነበሩ ሰዎችም ይደራደሩ ነበር፣ ዛሬም ይደራደራሉ፣ ነገም ይደራደራሉ። ተቃራኒ ፍላጎቶችና የሀብት እጥረት እስካለ ድረስ ድርድር ይኖራል።
ሁሌም የተሻለ ኑሮ የሚኖረው የተሻለ መደራደር የሚችለው ነው።
ድርድር የአንድ ቀን የድንገቴ ጉዳይ አይደለም።
ስለ ድርድር አጥና፣ ተለማመድ።
You can negotiate anything.

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 24 Sep 2021, 19:30

As we work hard to to win peace in #Ethiopia and move forward on our #prosperity path, let there be a collective resolve that there should no longer be war in Ethiopia. As @AbiyAhmedAli notes, war is the epitome of hell. Guns should be silenced for good.Full effort in building Ethiopia

Eyob Tekalign Tolina(PhD)
@EyobTolina
State Minister, Ministry of Finance , Ethiopia

Axumezana
Senior Member
Posts: 13223
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by Axumezana » 24 Sep 2021, 19:50

I agree the way out is negotiation toward peace and coexistence.
- PP can't finish TPLF and TPLF can't finish PP.
- No peace no prosperity
- No 100%™victory in civil war necessitates peace deal
- No zero sum peace deal but win- win
- No zero sum victory but win-win

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 02 Nov 2021, 18:44

The peace lobby at elite level is very thin. But still alive and kicking.


sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 07 Nov 2021, 09:29

ዲሽታ ጊና ዛሬ በመስቀል አደባባይ ያደረገው ንግግር "በሽምግልና ይሻላላል!" ብሏል



sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 16 May 2022, 07:43

።።።።
ለሠላም ለእርቅና ለአብሮነት ረፍዶ አያውቅም!!!


አንዳንዶች ደግሞ "ከዚህም ከዚያም በኩል ካለፈው ጦርነት ተምራችሁ ለሰላም ለአብሮነትና ለእርቅ ቅድሚያ ስጡ።" ስትላቸው "እቺ የወያኔ ማዘናጊያ ናት😂" ይሉሃል። ጎበዝ መች አባህ ነቅተህ የምታውቀውን ነው ስለማዘናጋት የምትዘበዝበው? ለመንቃትኮ ዓመት እስከ አመት በመላው ሀገሪቱ ወገኖችህ በብሔራቸው ምክንያት ሲታረዱና ሲፈናቀሉ ማየቱ ከበቂ በላይ ነበር ።

ለመንቃትኮ በወያኔ ስትወረር ስጋና ደማቸውን ገብረው የተዋደቁልህ ፋኖዎች ከጦርነቱ በኋላ እየታደኑ ፣ እየተሳደዱ ዛሬም ድረስ እየታሰሩ ማየትህ ብቻ በቂ ነበር። ስለሰላም ሲወራ ስለማዘናጋት የምታወራው መቼ ነቅተህ የምታውቀውን ነው?ከዓመት እስአ ዓመት በየቦታው የሚደርስብህ ዘር ተኮር ጥቃት ብቻውን ፋኖን ለመቀላቀል ፣ ለመርዳትና ፣ ለመደገፍ በቂ አልነበረም እንዴ? ምነው ታዲያ እስከዛሬ ሳትነቃ ?

ጎበዝ ጦርነቱ እዚህ ኪቦርድ በቀደደው አፍህ የምታቀረሽበት ፌስቡክ ላይ አይደለም። ሥለ ሠላም ሲወራ ስለማዘናጋት ከማውራትህ በፊት መንቃት ካለብህ ጊዜ እጅግ ብዙ ዘግይተሃልና ወርደህ የነቁትን ተቀላቀል ።


።።።።
ለሠላም ለእርቅና ለአብሮነት ረፍዶ አያውቅም!!!

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Does Ethiopia really have a "peace constituency"? | Is there a peace lobby in Ethiopia?

Post by sarcasm » 24 Sep 2022, 09:25

It is amazing some people were brave enough to write the below on the first day of the War on Tigray!

ኢትዮጵያ እንደ ርብቃ በሆድዋ ያሉ ልጆችዋ እየተዋጉባት "እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?" ብላ እየጮኸች ነው:: ለእናት ልጆችዋ ቢጋደሉላት ምን ይጠቅማታል? ሟቹም ልጅዋ ገዳዩም ልጅዋ ነውና ከመቁሰል በቀር ምንም አታገኝም:: ዳዊት ልጁ አቤሴሎም ሌላ ልጁን አምኖንን በገደለ ጊዜ ያለቀሰውን ለቅሶ ኢትዮጵያ ታለቅሳለች:: በዚህ መካከል ምስኪኑ ወገናችን ይረግፋል:: እጅ እጁን ሲቆርጥ ደስታና ፉከራ የለም:: ብንችል በዚህ ሰዓት በጸጸት እንጸልይ:: ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ ዝም እንበል:: የሀገርን ሰላም የምትፈልጉ ሁላችሁ ከሩቅ በለው በለው ማለት ትታችሁ ማረን ማረን በሉ::
በሩቅ ሆነን አይነካንም ብለን እየፎከርን በምስኪኑ ላይ እሳት የምናነድ አንሁን:: በወገን ሞት ተደስተን እንደባዕድ ሀገር ጦርነት የድል ዜማ ብናዜም እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ይፈርድብናል:: ጦርነትን የምናወግዘው በሰላም ዘመን ሳይሆን በእንዲህ ዓይነቱ ጊዜ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ቢለዋወጥ የማይለወጥ አቋምዋ ይህ ነው:: በየሜዳው እየወደቀ ያለው የዚህ ወገን የዚህ ወገን ሳይሆን "ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" ወንድማማች አትበሉ ይሉናል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንኳን የአንድ ሀገር ሰው ዓለም ሁሉ ወንድም ነው እያለን ምን እናድርግ? ልክ ነው ቃየል ጨካኝ ነው ክፉ ነው ነገር ግን የአቤል ወንድም ነው::

ከራሳችን በላይ ሌላ ጠላት የለንምና ጌታ ሆይ ከራሳችን አድነን:: ራሳችን እያራገብን ከመቃጠል አድነን:: ልባችንን መልስልን:: ኢትዮጵያ እጅዋን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ትታ ራስዋ ላይ ቃታ የሳበችበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ጌታ ሆይ በዓይነ ምሕረትህ ተመልክተህ እኛው ያነደድነውን እሳት አብርድልን:: በትግራይ በአማራ በኦሮሚያ ያሉ በዚህ እሳት ዙሪያ የሚማገዱ ወገኖቻችንን ከጥፋት ይጠብቅልን:: በግራም በቀኝም የተሰለፉት በድህነት የሚኖሩ አንድ ውኃ የጠጡ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው:: አባቶቻቸው ሳይለያዩ አብረው ከብዙ ጠላት ጋር ታግለው ባቆዩአት መሬት ላይ ወንድማማቾች ጦር እየተሳበቁ ነውና በቸርነትህ ልባቸውን አራራ:: በወንድምን ደም እንደ ቃየን ከመቅበዝበዝ በቀር ትርፍ እንደሌለ አሳያቸው:: ጠግቦ በልቶ ሳያድር ተመስገን ማለትን ያልተወ ሕዝብህን ጌታ ሆይ በምሕረትህ አድነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 25 2013 ዓ.ም.
Please wait, video is loading...

Post Reply