Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by sarcasm » 13 Aug 2021, 20:14

ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!

በሰሜን ወሎ የወያኔ አስተዳደር እየተመሰረተ ነው… #የወሎ_የክልልነት_ጥያቄ_እውን_ይሆናል!

መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁሙን ካነሳ ወዲህ እርምጃ ይወስዳል ብለን ብንጠብቅም በሰሜን ወሎ የጁ-ራያ ግንባር ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ በሰሜን ወሎ ችግሩ የከፋ ሆኖ ሳለ ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ወያኔ፡- ከዚህ በፊት በቆቦና በሌሎች የራያ አካባቢዎች ህዝብ እየሰበሰበች ከንቲባ እያስመረጠች የራሷን አሻንጉሊት አስተዳደር መፍጠሯ ይታወቃል፡፡ (A state within a state)

አሁን ደግሞ መርሳ፣ መሐል አምባ (ሱዳን ሰፈር) እና ሊብሶ ከተሞችን ተቆጣጥራ ህዝቡን ሰብስባ የቀበሌ አስተዳደር እያስመረጠች ነው፡፡ በመጋዘን ያለውን የእርዳታ እህል ለህዝብ በማከፋፈል “መንግስት ነኝ” እያለች ነው፡፡

#ወሎ_በአማራ_ክልል_መንግስት_ተክዷል!!! እነሆ ዘመዶቻችን በወያኔ አስተዳደር፤ እኛ በፌዴራል መንግስት አስተዳደር ስር ሆነናል፡፡ ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን የወሎ ምሁራንና ብልጽግና ውስጥ ያላችሁ የፖለቲካ ልሂቃን በያለንበት መምከር ይገባናል፡፡
በአማራ ክልል ሸፍጥ ወሎ በልማት ወደኋላ እንዲቀር መደረጉ ሳያንስ አሁን ይባስ ብሎ በጠላት ኃይል እንዲተዳደር ተፈርዶበታል፡፡ ታዲያ እንዴት ሆኖ፣ በየትኛው የሞራል ህግ ነው መቀመጫውን ባህር ዳር ባደረገው “የአማራ ክልል” ስር ሆነን የምንቀጥለው?

ይህ የችግር ጊዜ ያልፋል! - እንተያያለን!!!
Please wait, video is loading...

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Za-Ilmaknun » 13 Aug 2021, 20:32

It is a mistake to lump together people in one region based on ethnicity and language only. We should be working towards diversity at the local level. You are only encouraging chaos and and animosity among people when you segregate them in to apartheid style of administration like the one we have for the past 30 years.

Once the war with TPLF terror mongers is over, there will be a new political order that will go beyond the simplistic language and language only based selectively implemented federal system. You can't have a Tigrai Region while denying Wolayta with equal number of population same status. Ill intentions and falsehood only took you so far and backfired big time.
:mrgreen:

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by sarcasm » 13 Aug 2022, 09:23

By Brook Abegaz

"አማራ ክልል ከመግዘፉ የተነሳ ከልማትና ከእድገት አንጻር አሉታዊ አስተዋፅኦ እየፈጠረ ስለሆነ ከዚያ ችግር መውጣት፣ ፍትሀዊ የልማትና የሀብት ክፍፍል . . . "
·
ሙሉጌታ ከበደ የሚባሉ የህግ ባለሙያ የሆኑ ሰው የሰሞኑን የወሎ ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጥያቄወችን ጠይቀው፤ ከጥያቄወቹ መካከል እኔን የሚመለከተኝን እንደሚከተለው አድርጌ መልሻለሁ

ወንድማችን መልካም ጥያቄዎችን ነው ያነሳሀው፤ የሚመለከታቸው አካላትም ምላሽ መስጠት አለባቸው። በእኔ በኩል ሰሞኑን እየሰነዘርኩት ካለው ሀሳብ አንጻር የሚመለከተኝን ጥያቄወች ልመልስልህ

እስከማውቀው ድረስ የወሎ ህዝብም ሆነ የወሎ ክልላዊ አስተዳደር ቢመሰረት ብለው አማራጭ ሀሳብ የሰነዘርነው ወገኖች ምንም አይነት የማንነትም ሆነ የእውቅና ስጡን ጥያቄ አላነሳነም። የማንነት ጥያቄም፣ ችግርም፣ ብዥታም፣ ግርታም የለብንም። በማንነት አጥር የታጠረና አንደኛውን ዜጋ ልጅ ሌላኛውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ የሚያደርግ አስተዳደራዊ ክልልም ሆነ ሌላ መዋቅር አንፈልግም። እንደምታውቀው በዘውግ ማንነት ደረጃ ካየነው ብዙሀኑ ወሎዬ አማራ ሲሆን ኦሮሞ፣ አገውና አርጎባ ደግሞ በወሎ ውስጥ ያሉ ዘውጋዊ ማንነታቸው የታወቁ ህዝቦች ናቸው።

ስለዚህ ወሎ ክልል ሲሆን ባለቤትነቱ የአንድ ብሄር ወይም ዘውግ ሳይሆን የእነዚህ ዘውጎችና ሌሎችም ካሉ እንዲሁም በአስተዳደር ግዛቱ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ዜጋ ስለሚሆን ኅብረ ብሄራዊ ቅርጽ ይኖረዋል ማለት ነው። ህገ መንግስቱ ክልልነት እውቅና ለመስጠት የግዴታ አንድ ብሄር ሁኑ ወይም የአንድ ብሄር መጠሪያ የግዴታ ነው ብሎ በአስገዳጅነት አያስቀምጥም። አለማስገደዱ ብቻ ሳይሆን ባሳለፍነው መስከረም ወር ከፋን ጨምሮ ከ18 በላይ ብሄሮች በአንድ ላይ ሆነው የብሄር ስም መጠሪያ የሌለው መልከአ ምድርን ታሳቢ ያደረገ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል የሚል ህጋዊ አስተዳደር ተመስርቷል።

ስለሆነም ከዚህ አንጻር ወሎ ራሱን የቻለ ክልል ለመሆን ህገ መንግስቱ ሳይሻሻል በዚሁ ህገ መንግስት ብቻ የክልል አስተዳደር ለመመስረት የሚያግደው ነገር የለም። ይሄ ሲሆን ህዝቡ የቀደመ የብሄር ማንነቱን እየጣለ ወሎ የሚባል ብሄር ሆነ ማለት አይደለም። ለምሳሌ እኔ የወሎን ክልልነት ስደግፍ የዘውግ ማንነቴ አማራ ሲሆን ከዘውግ ውጭ ደግሞ በየደረጃው ያሉት አካባቢያዊ ማንነቶቼ የሙጃ ልጅ ፣ ግዳኔ፣ ላስቴ፣ ወሎዬ ይሆናሉ ማለት ነው። ከሃይማኖት ማንነት አንጻር ደግሞ ኦርቶዶክስ ልባል እችላለሁ፣ ከምግብ አንጻር ሽሮና ሰላሱት ስለምወድ ሰላሱትና ሽሮ የሚወደው በሚል የምግብ ምርጫ መገለጫዬን ላደርግ እችላለሁ😜። (ያው ማንነት በጣም ብዙ ነገሮችን ስለሚያካትት ነው)

የአማራነት ዘውጌያዊ ማንነቴ እና እነዚህ አካባቢያዊ ማንነቶቼ ከ1983 በፊት አማራ ክልል የሚባለው ሳይፈጠር ነበሩ ፣ አማራ ክልል ተፈጥሮ ባለፉት 30 አመታትም አሉ ፣ ወደፊትም ወሎ ክልል ሲሆን መኖራቸው ይቀጥላል። ነገር ግን ወሎ ራሱን ችሎ ክልል ከሆነ በኋላ አማራ በሚባለው ስም የሚጠራ ክልል ሊኖር አይችልም ፤ እኛ የወሎ አማራወችም የባለቤትነት ህጋዊና ታሪካዊ መብት ስላለን እንጠይቃለን። በእርግጥ ወሎ ክልል ሆኖ ጎንደርና ጎጃም በአንድነት ይቀጥላሉ ብየ ከማስብ የሞተችው የምወዳት አያቴ አፈሩን አራግፋ ከሞት ተነስታ ትመጣለች ብዬ ማሰቡ ይቀለኛል።

የወሎ ክልልነት ጥያቄ ኢትዮጲያን ከዘር ፖለቲካ ለማውጣት፣ በየቦታው የሚጨፈጨፈው አብዛኛው ወሎዬ በመሆኑ ወገናችንን የሚታደግ የፖለቲካ አስተዳደርና እሳቤ መፍጠር፣ አማራ ክልል ከመግዘፉ የተነሳ ከልማትና ከእድገት አንጻር አሉታዊ አስተዋፅኦ እየፈጠረ ስለሆነ ከዚያ ችግር መውጣት፣ ፍትሀዊ የልማትና የሀብት ክፍፍል፣ ወሎየው ጎልቶ የሚወጣበትና በአገር አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚሆንበትን የፖለቲካ ማዕቀፍ ማንበር፣ እጅግ የምንኮራበትና መኖር የምንፈልገውን ወሎዬ እሴትና ማኅበረሰባዊ የአብሮነት ዘይቤ በማስጠበቅና ከወሎ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ ገቢር ሆኖ የችግር መፍቻ እንዲሆን ለማድረግ፣ ወዘተ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

የሚመለከታቸውን አካላት አናግራችኋል ወይ ለሚለው ጥያቄ? ጉዳዩ በውስን ሰወች በምክክር ደረጃ የተጀመረ እንጂ ያበቃና ያለቀ ነገር አይደለም። ወሎን ያክል ግዛት በውስን ሰወች ምክክር ብቻ ነገሩን ለማስኬድ መሞከር እብደት ነው። ስለሆነም አንተ ያነሳሀቸውን አካላትም ብቻ ሳይሆን የሚመለከተው ጋር ሁሉ በጋራ እንመክራለን፤ ህዝብ ይወያይበታል ለሌላ አካባቢወችም ምሳሌ የሆነ አካሄድ ይፈጠራል። ከምክር ቤቶች አንጻር የብሄረሰብ አስተዳደር መዋቅር ያላቸው በብሄረሰብ አስተዳደር ምክርቤቱ የብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ለሌላቸው ደግሞ በወረዳ ምክር ቤታቸው ውሳኔ ይሠጡበታል ለዚህም ተገቢውን ስራ መስራት ያስፈልጋል።

ከዚህ ውጭ ያሉት ጥያቄወች እኔን አይመለከቱኝም!

Brook Abegaz
17 h ·
Chuchu Alebachew
17 h ·

Please wait, video is loading...

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Assegid S. » 13 Aug 2022, 10:46

ሰላም Sarcasm;

በዚህ post ላይ ሁለት ነገሮችን ማንሳት ወደድኩ፦ ኣንድ አስተያየትና ኣንድ ጥያቄ። ለጽሑፉ አቅራቢ ክብደት ለመስጠት የተጠቀመከው ሐረግ (የልደቱ ጓደኛ) በእኔ እምነት ፀሐፊውን በዜሮ አባዝቶታል። በእርቃን ቃል ስገልፀው፦ የባንዳው ጓደኛ ብለህ እንደፃፍከው ነው የተሰማኝ። ይህ ደግሞ የእኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ስሜት እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ዘመን ተሻጋሪ የሆን ብሒል አለና ... Tell me your friends and I will tell you who you are.

ቀጣይ ጥያቄዬ ... ኢትዮጵያን በቋንቋና ዘር መሰነጣጠቁ ለትግራይ ጠቅሟታል ብለህ ታስባለህ? አሁንስ በሁለተኛ ደረጃ ወርዶ ወሎን እንደ ክልል ከኣማራው አስተዳደር ላይ መቁረሱ፥ ለተምቤን፣ ኢሮብ ... ማደሪያ ለሆነችው ትግራይ ይጠቅማል? በእኔ እምነት ዘረኝነት እንደ ተስቦ በሽታ ነው ... በኣጥርና ድንበር አይከለልም።

By the way, ብዙዎች ሳርካዝምን በሴት ፆታ ሲገለፁት አነባለሁ። የሚቻል ከሆነ ... ኢትዮጵያዊ ሴትነት ያኮራል እንጂ አያሳፍርምና ዛሬ ግልፅ ቢሆንልን? 8) አለበለዚያ ግን ከሚቀጥለው ጊዜ ጀምሮ በአንቱታ @እርሶ እያልኩ Address ማድረግ እጀምራለሁ። ኣንድም ከስህተት ለመዳን ሁለትም ለአክብሮት ይሆነኛል 8)

መልካም ሰንበት ... Sarcasm

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by sarcasm » 14 Aug 2022, 09:59

Assegid S. wrote:
13 Aug 2022, 10:46

ሰላም ጋሽ አሠግድ

ስለ ልደቱ ያለዎት ኣስተያየት በብዙ ዓመት የተገነባ ስለሚመስለኝ ኣለመንካቱ እመርጣለሁኝ።

ብዙ ሰው Eden እና እኔ ኣንድ ሰው ነን ብሎ ስለሚናገርና ደግሞ በኣብዛኛው Eden የሴት ስም ስለ ሆን ይሆናል የተጠራጠሩት። እኔ ወንድ ነኝ።

On the number of regional administration, although it should depend on people's choice according to the constitution, more smaller regions could help to resolve some of the current problems. Ethiopia had 30 administration regions during Derg's last few years. 1930s Ethiopia had 19 administration regions. Switzerland has 26 administration regions although its population is less than 9 million.

https://en.wikipedia.org/wiki/Provinces_of_Ethiopia

On በቋንቋና ዘር መሰነጣጠቁ, Ethiopia and all other multi-ethnic countries have always been been divided along ethnic lines. But now politicians are using ethnicity for political killings. The politicians in previous administration were not determined to cleanse areas from different ethnicity by killing the other ethnicity. Now politicians in some Oromia region areas are killing Amharas and the Amhara politicians in some Amhara region areas are killing Oromos. Amhara region's ethnic cleaning of Tigrayans in Western Tigray is now internationally recognized 21st century crime.

Checkout Ethiopian Anthropologist's professional analysis on በጎሳ መከፋፈል
Please wait, video is loading...

Misraq
Senior Member
Posts: 12279
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Misraq » 14 Aug 2022, 10:47

Brook Abegaz is the cadre of both Biltsigina and Ezema. In a nutshell, brook Abegaz is natural enemy of Agame Sarcasm. But since Brook Abegaz the Banda follows Biltsigina Oromuma and Ezema ajanda to divide Amharas he is considered a friend for Agames.

That how we know agames are our #1 enemies and should fight them to the end. Some foolish Amharas started to advocate for agames for the seige to be lifted. How wrong this innocent Amharas are. Agames are happy to work with Biltsigina and Ezema if it helps to hurt Amharas.

ከይሲ ሕዝብ

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Assegid S. » 14 Aug 2022, 11:18

ሰላም ወንድም Sarcasm;

ጥያቄዬን በመመለስህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። በተቀረው አስተያየትህ ላይም ቢሆን ከሞላ ጎደል እስማማለሁ። ነገር ግን ሀገራችን ውስጥ የተከሰተውንና እየተከሰተ ያለውን socio-political ቀውስ በተመለከተ፥ ሁላችንም የየራሳችን እውነትና እምነት ስለሚኖረን አሁን ላይ በተለይም በእንዲህ ያለ አጭርና ውስን መድረክ ላይ argue ማድረግ እጅግ እንደሚከብድ ሰለማውቅ፥ ምናልባት ወደፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚኖረን ሰፊና አመቺ (in situ) discussion መተዉ መልካም መስሎ ይሰማኛል።

Sarcasm, when it comes to politics, I HARDLY TRUST THE INTERNATIONAL BODIES AND THE SO CALLED INTELLECTUALS. እነዚህ አሳርዘው የሚያለብሱ - አስርበው የሚያጎርሱ ምዕራባውያን ያለ ጥቅምና ሻጥር ኣንዳች ነገር ያምናሉ ወይም ይደግፋሉ ብዬ እንደማላስብ ሁሉ፥ ትምህርት ቤት የሄደም አላዋቂ በሙሉ ተምሮና ኣውቆ ይወጣል የሚል እምነት የለኝም። Post ላደረከው ቪዲዮ በድጋሚ አመስግኜ ... ከ"ምሁሩ" ሐሳብ ጋር ግን በፍፁም አልስማማም፦ ምክንያቱም በዚች ሁለት ደቂቃ ውስጥ እንኩዋን የማውቀውን ሐቅ ሲዋሹ ስለተመለከትኳቸው።

መልካም የሥራ ሳምንት! ሳርካዝም 8)

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by sarcasm » 15 Aug 2022, 20:17

Assegid S. wrote:
14 Aug 2022, 11:18
ሰላም ወንድም Sarcasm;

ጥያቄዬን በመመለስህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። በተቀረው አስተያየትህ ላይም ቢሆን ከሞላ ጎደል እስማማለሁ። ነገር ግን ሀገራችን ውስጥ የተከሰተውንና እየተከሰተ ያለውን socio-political ቀውስ በተመለከተ፥ ሁላችንም የየራሳችን እውነትና እምነት ስለሚኖረን አሁን ላይ በተለይም በእንዲህ ያለ አጭርና ውስን መድረክ ላይ argue ማድረግ እጅግ እንደሚከብድ ሰለማውቅ፥ ምናልባት ወደፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚኖረን ሰፊና አመቺ (in situ) discussion መተዉ መልካም መስሎ ይሰማኛል።

Sarcasm, when it comes to politics, I HARDLY TRUST THE INTERNATIONAL BODIES AND THE SO CALLED INTELLECTUALS. እነዚህ አሳርዘው የሚያለብሱ - አስርበው የሚያጎርሱ ምዕራባውያን ያለ ጥቅምና ሻጥር ኣንዳች ነገር ያምናሉ ወይም ይደግፋሉ ብዬ እንደማላስብ ሁሉ፥ ትምህርት ቤት የሄደም አላዋቂ በሙሉ ተምሮና ኣውቆ ይወጣል የሚል እምነት የለኝም። Post ላደረከው ቪዲዮ በድጋሚ አመስግኜ ... ከ"ምሁሩ" ሐሳብ ጋር ግን በፍፁም አልስማማም፦ ምክንያቱም በዚች ሁለት ደቂቃ ውስጥ እንኩዋን የማውቀውን ሐቅ ሲዋሹ ስለተመለከትኳቸው።

መልካም የሥራ ሳምንት! ሳርካዝም 8)
ሰላም ጋሽ አሠግድ,

I cannot disagree with you on those who are generally called intellectuals. They haven't done a lot to help their communities although our political culture is really violent and extremist which doesn't encourage some intellectuals to engage in public arena.

On the international community, it is better to have realistic expectation and accept they have interest they are supposed to protect. But, it is difficult to discount their positive contribution to the general public which is being killed and starved by its own politicians. Tewodros has put their role eloquently in the below clip from 11:30. It is almost impossible to argue against his points.

መልካም ሳምንት

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Assegid S. » 16 Aug 2022, 15:51

Hello Sarcasm; thanks a lot for the post. ይህን ፕሮግራም አይቼው አላውቅም ነበር … በድጋሚ በጣም አመሰግናለሁ።

Sarcasm, Tewodros የሚያነሳው ነጥብ ለእኔ ወጥነት የሌለው ዥጉርጉር ሆኖ ነው ያገኘሁት። አንድ አካል በድርድር ውስጥ ጥቅም ካለውና እርሱን ለማስጠበቅ ተሳታፊ ከሆነ “ተደራዳሪ” እንጂ ”አደራዳሪ” ሊሆን ፈፅሞ አይችልም። ኣፍሪካ-ህብረት ተደራዳሪዎቹን በድርድሩ ነጥቦች ላይ እንዲስማሙ ለማስገደድ “አቅምና ልምድ” የለውም … ያንን ሐሳብ በትክክል እጋራለሁ። የኣፍሪካ ችግር በኣፍሪካውያን ብቻ መፈታት አለበት የሚለውን አመለካከት እየደገፍኩም ቢሆን። ነገር ግን “አደራዳሪ የራሱን ጥቅም ለማስጥበቅ ተሳታፊ የሚሆን ተደራዳሪም ጭምር ነው (መሆንም አለበት)” የሚለው ሐሳብ ግን ለእኔ እርስ በእርሱ የሚጋጭና illogical ነው።

በእኔ እምነት “አደራዳሪ” ማለት በምንም አይነት መልኩ ለራሱ ጥቅም ያልወገነ … በድርድሩ ወቅት ለሚነሱ ነጥቦች አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ተገቢ ነው የሚለውን ምክረ ሓሳብ የሚያቀርብና የማያስማሙ አጀንዳዎች ላይ የራሱን አቋም (ጥቅም ) ለማስጠበቅ ሳይሆን የተደራዳሪዎቹን ፍላጎት ያማከለ አማራጮችን ለመጠቆም የሚቀመጥ አካል ነው። በተለምዷዊ አነጋገር፦ አደራዳሪ እንደ ዳኛ neutral መሆን አለበት።

ከቃለምልልሱ ለመረዳት እንደቻልኩት፦ Tewodros ምዕራብያውያኑ ፍፁም የሆን የሞራል ልዕልና ያላቸው፣ ዘውትር ከእውነት ጋር የወገኑ መላዕክት አድርጎ ተቀብሏቸዋል። ለዛም ነው “high moral value ያላቸው፣ ለእውነትና ለሰብዓዊነት ብቻ የቆሙ" ናቸው ብሎ የሚያወድሳቸው። እርሱ በዛ መልኩ ሊስላቸውና ሊቀበላቸው መብት እንዳለው እያመንኩ፤ የእኔ እምነትና ምልከታ ደግሞ ፍፁም በተቃራኒው ነው።

ለማጠቃለል ያህል፦ አደራዳሪዎች ከድርድሩ ጠረፔዛ የሚዘግኑት ጥሬ መኖር የለበትም ብዬ ስል … ፍላጎታቸውን ይዘው ወደ ጠረፔዛው መቅረብ የለባቸው እያልኩ እንጂ የድርድሩ ውጤት በየትኛውም አቅጣጫ ቢደመደም እነርሱም ሆኑ ሌላው በድርድሩ ላይ ያልተካተተ የዓለም ኣካል ተጎጂ ወይንም ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም ማለቴ ግን አይደለም። We all are interconnected: politically, socially, and economically.

ያም ቢሆን ግን፦ “አደራዳሪ” ጥቅሙን በ samsonite ሻንጣ ሸክፎ የሚቀመጥ primary or second degree “ተደራዳሪ” ሳይሆን … ቀድሜ እንዳልኩት በድርድሩ ወቅት ለድርድሩ ተሳታፊዎች አስተማማኝ env’t ከመፍጠር በተጨማሪ፥ ከዕውቀትና ልምድ አኳያ የሚኖረውን ተሞክሮ ያለ ኣንዳች አስገዳጅ ሁኔታ (ከራሱ ጥቅምም ይሁን ከየትኛውም ተደራዳሪ ኣንፃር ሳይወግን) በገለልተኝነት የሚያካፍል፤ ድርድሩ ያለ ስኬት የሚጠቃለል ወይም የሚቋረጥ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ለተቀረው ዓለምና የዚህን ድርድር ውጤት ከሰብዓዊነትም ሆነ ከግለሰባዊ (ሀገራዊ) ጥቅም አኳያ አግባቢም ይሁን አስገዳጅ እርምጃ ሊወስዱ ለሚችሉ አካላት ነፃና ያልተዛባ ሪፖርት ማቅረብ ነው ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ … “አደራዳሪ በድርድሩ ውስጥ እንዲከበርና እንዲጠበቅ የሚፈልገው ጥቅምና እሴት ያለው አካል መሆን አለበት” የሚለውን የTewodros ምልከታ በፍፁም የማልቀበለውና ከ”ተደራዳሪ” definition ፈፅሞ ያልተለየ ነው። ይኼ ነው የእኔ ምልከታ ወንድም Sarcasm 8)

Wish you a nice weekdays.

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (የልደቱ ጓደኛና የኢዴፓ መስራች)

Post by Abere » 16 Aug 2022, 17:48

ከመቼ ወድህ ነው ይህ ለወሎ ህዝብ ተቆርቋሪነት የመጣው? ወይ ጉድ የሚቆረቆሩት ደግሞ እኮ ወያኔዎች እና የዓአብይ አህመድ ደጋፊ ኦነጎች ወይም ተከፋዮች ናቸው። ሁሉን አይነት ግፍ በወሎ ላይ ወያኔዎችም ብልጽግና ኦነጎችም ፈጽማችኋል - ይህኛው ዘደ ደግሞ ምን ዓይነት ግፍ ልትፈጽሙ አስባችሁ ይሆን? የሚደንቀው ግን ሁለታችሁም ያልተሳካላችሁ ውዳቂዎች የታሪክ አተላዎች ናችሁ።

Post Reply