Hello Sarcasm; thanks a lot for the post. ይህን ፕሮግራም አይቼው አላውቅም ነበር … በድጋሚ በጣም አመሰግናለሁ።
Sarcasm, Tewodros የሚያነሳው ነጥብ ለእኔ ወጥነት የሌለው ዥጉርጉር ሆኖ ነው ያገኘሁት። አንድ አካል በድርድር ውስጥ ጥቅም ካለውና እርሱን ለማስጠበቅ ተሳታፊ ከሆነ “
ተደራዳሪ” እንጂ ”
አደራዳሪ” ሊሆን ፈፅሞ አይችልም። ኣፍሪካ-ህብረት ተደራዳሪዎቹን በድርድሩ ነጥቦች ላይ እንዲስማሙ ለማስገደድ “
አቅምና ልምድ” የለውም … ያንን ሐሳብ በትክክል እጋራለሁ። የኣፍሪካ ችግር በኣፍሪካውያን ብቻ መፈታት አለበት የሚለውን አመለካከት እየደገፍኩም ቢሆን። ነገር ግን “
አደራዳሪ የራሱን ጥቅም ለማስጥበቅ ተሳታፊ የሚሆን ተደራዳሪም ጭምር ነው (መሆንም አለበት)” የሚለው ሐሳብ ግን ለእኔ እርስ በእርሱ የሚጋጭና illogical ነው።
በእኔ እምነት “
አደራዳሪ” ማለት በምንም አይነት መልኩ ለራሱ ጥቅም ያልወገነ … በድርድሩ ወቅት ለሚነሱ ነጥቦች አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ተገቢ ነው የሚለውን
ምክረ ሓሳብ የሚያቀርብና የማያስማሙ አጀንዳዎች ላይ የራሱን አቋም (ጥቅም ) ለማስጠበቅ ሳይሆን የተደራዳሪዎቹን ፍላጎት ያማከለ አማራጮችን ለመጠቆም የሚቀመጥ አካል ነው። በተለምዷዊ አነጋገር፦ አደራዳሪ እንደ ዳኛ neutral መሆን አለበት።
ከቃለምልልሱ ለመረዳት እንደቻልኩት፦ Tewodros ምዕራብያውያኑ ፍፁም የሆን የሞራል ልዕልና ያላቸው፣ ዘውትር ከእውነት ጋር የወገኑ መላዕክት አድርጎ ተቀብሏቸዋል። ለዛም ነው “
high moral value ያላቸው፣ ለእውነትና ለሰብዓዊነት ብቻ የቆሙ" ናቸው ብሎ የሚያወድሳቸው። እርሱ በዛ መልኩ ሊስላቸውና ሊቀበላቸው መብት እንዳለው እያመንኩ፤ የእኔ እምነትና ምልከታ ደግሞ ፍፁም በተቃራኒው ነው።
ለማጠቃለል ያህል፦ አደራዳሪዎች ከድርድሩ ጠረፔዛ የሚዘግኑት ጥሬ መኖር የለበትም ብዬ ስል … ፍላጎታቸውን ይዘው ወደ ጠረፔዛው መቅረብ የለባቸው እያልኩ እንጂ የድርድሩ ውጤት በየትኛውም አቅጣጫ ቢደመደም እነርሱም ሆኑ ሌላው በድርድሩ ላይ ያልተካተተ የዓለም ኣካል ተጎጂ ወይንም ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም ማለቴ ግን አይደለም። We all are interconnected: politically, socially, and economically.
ያም ቢሆን ግን፦ “
አደራዳሪ” ጥቅሙን በ samsonite ሻንጣ ሸክፎ የሚቀመጥ primary or second degree “
ተደራዳሪ” ሳይሆን … ቀድሜ እንዳልኩት በድርድሩ ወቅት ለድርድሩ ተሳታፊዎች አስተማማኝ env’t ከመፍጠር በተጨማሪ፥ ከዕውቀትና ልምድ አኳያ የሚኖረውን ተሞክሮ ያለ ኣንዳች አስገዳጅ ሁኔታ (ከራሱ ጥቅምም ይሁን ከየትኛውም ተደራዳሪ ኣንፃር ሳይወግን) በገለልተኝነት የሚያካፍል፤ ድርድሩ ያለ ስኬት የሚጠቃለል ወይም የሚቋረጥ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ለተቀረው ዓለምና የዚህን ድርድር ውጤት
ከሰብዓዊነትም ሆነ
ከግለሰባዊ (ሀገራዊ) ጥቅም አኳያ
አግባቢም ይሁን
አስገዳጅ እርምጃ ሊወስዱ ለሚችሉ አካላት ነፃና ያልተዛባ ሪፖርት ማቅረብ ነው ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ … “
አደራዳሪ በድርድሩ ውስጥ እንዲከበርና እንዲጠበቅ የሚፈልገው ጥቅምና እሴት ያለው አካል መሆን አለበት” የሚለውን የTewodros ምልከታ በፍፁም የማልቀበለውና ከ”ተደራዳሪ” definition ፈፅሞ ያልተለየ ነው። ይኼ ነው የእኔ ምልከታ ወንድም Sarcasm
Wish you a nice weekdays.