Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33280
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

(((EGYPT & AGAMES WILL KILL THEMSELVES))): ሱዳን ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንድትሸጥላት ጠየቀች!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 05 Aug 2021, 08:31

Natnael Mekonnen
3ftSmoponsoredht ·
ሱዳን ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንድትሸጥላት ጠየቀች።

#Ethiopia : ሱዳንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ተናግረዋል።

በቅርቡ ሱዳን አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንደምትፈልግ ማሳወቋን ተከትሎ ባለፈው ወር የተቋሙ ሠራተኞች ወደ ካርቱም አቅንተው እንደነበረና የሱዳን ባለሙያዎችም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ውይይቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ለኬንያ የኤሌትሪክ ሃይል አቅርቦት 500 ኪሎ ዋት መሸከም የሚችል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የገለጹት አቶ አንዱዓለም፤ የኬንያ ፓርላማ ተወካዮች በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ አልፎ ታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ሁለት ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ የሚያስችል መሠረተ ልማት ያነሱት ኃላፊው ሶማሌላንድም ከኢትዮጵያ ሃይል ለማግኘት እንድትችል በዓለም ባንክ ድጋፍ ኢስት አፍሪካ ፖወር ፖሊሲ ከሚባል ተቋም ጋር ጥናት እየተደረገ መሆኑ አመልክትዋል።

ደቡብ ሱዳንም ሃይል እንዲቀርብላት በደብዳቤ ፍላጎቷን መግለጿን ጠቁመው፤ ይህን ተከትሎ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማከናወን የሚያስችል ጥናት ለማድረግ የባለሙያዎች ቡድን በቅርቡ ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚያቀና ተናግረዋል። (ENA) See Less