Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5523
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by Naga Tuma » 04 Aug 2021, 21:18

ከሁለት ቀናት በፊት ኼር የሚል የሰው ስም ዉስጥ ኣየሁ። ስሙን እንዳየሁ ሰዉየዉ ኢትዮጵያዊ ይሆን ብዬ ኣሰብኩ።

ደርሼ ሳየዉ ከሩቅ ምስራቅ መሆኑን ገመትኩኝ። እንዴት ኼር ስሙ ዉስጥ ሊታይ ቻለ ብዬ እራሴን መልሼ መላልሼ ጠየኩኝ።

ከዛም ከኣሁን በፊት የተዋወኩትን የኔፓል ሰዉ ስሙ ሃሪ (Hari) የሚባል ኣስታወስኩኝ። ትርጉሙን ጠይቄዉ ነበር። ትርጉሙ ጌታ፣ እግዝኣብሄር፣ እንደምንለዉ ኣይነት የለኝ መሰለኝ።

ኣሁን ኼር የሚለዉን የሌላ ሰዉ ስም ዉስጥ ሳይ እና ያኔ የሰማሁትን ሳስታዉስ ኣእምሮዬ ቶሎ ሆረስ ኬር ወደሚለዉ ሮጠ።

ከዛም የእንግሊዙን ሃሪ ፖተር የሚባል የልበወለድ ስም ኣስተወስኩኝ።

ከዛን ቀን (August 2, 2021) ጀምሮ ኼር፣ ኬር፣ እና ሃሪ ይገናኙ ይሆን ብዬ ስጠይቅ ቆየሁ።

ሆረስ፣

በትክክል ካስታወስኩ ኼር እና ኬር የወራረሳሉ ብለሃል። ሃሪ ከሁለቱም የሚገናኝ ይሆን?

አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ የፎረሙ ተሳታፊዎች፣ ሃረ፣ ሃሪ፣ እና ሄረ ከኼር እና ኬር ጋር ግጥምጥሞሽ ነዉ ወይስ የምያገናኛቸዉ ኣለ?

ከድምጽ (spoken language) ወደ ምልክት (written language) ሽግግር የታየበት የጥንት ዘመን ፈረኦኖች የከ እና ኸን ድምጾች ለመለየት ምን ያህል እንዳሰቡ እና እንደለፉ በዚህ ዘመን ይታያችሁዋል?

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by EPRDF » 05 Aug 2021, 03:48

ኦቦ ናጋ ቱማ፣

በመጀመሪያ ኬር የሚለውን አባባል ከውይይታችን ዓውድ አውጣው። ምክንያቱም የኣማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ን ፕሮናውንስ ማድረግ የማይችሉ እንደ ፕሮናውንስ አድርገውት ኼር ከማለት ፋንታ ኬር ብለው የቃሉን ትክክለኛ ፕሮናወንሲዬሽን ደብዛውን ስላጠፉት።

ለምሳሌ፣ የሐረር ኦሮሞ ኾቱ ሲል የሸዋ ኦሮሞ ኮቱ ይላል። የሸዋ ኦሮሞ የአማርኛ ቋንቋ ኢንፍሉዌንስ ስላለበት ኸ ኹ ኺ ን ፕሮናውንስ ማድረግ አይችልም።

ኼር ከመስረቱ የአረብኛ ቃል ነው። ትክክለኛ አጠራሩም ኼይር ነው። ከ መሐል አለች፣ ግን በተለምዶ እየተዋጠች መጣችና ኼር የሚለው ድምፅ እየጎላ መጣ። ኼይር ትርጉሙም፣ ደግ፣ደህና፣ መልካም፣ የተሻለ፣ ጥሩ ነገር የሚሉትን የአማርኛ ቃላት ያጠቃልላል፣ ትርጓሜውም በዐረፍተነገርህ አጠቃቀም ላይ ይመረኮዛል ግን ከላይ ከዘረዘርኩዋቸው የቃላት ትርጉም ውጭ አይሆንም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30837
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by Horus » 05 Aug 2021, 04:41

EPRDF
እኛ አሁን ሞቅ ያለ ግዜያዊ ፖለቲካ ላይ ስለሆንን ይህን ነገር ዛሬ አልመልሰውም ብዬ ነበር ። ሆኖም የተሳሳተ (እውቀት ላይ ያልቆመ) ነገር እያመጣህ ስለሆነ ይህን ለማለት ተገድጃለሁ ። አሁን ልብ ብለው ተከታተል።

የናጋ ቱማ ኪዩሪዎሲቲ ጥያቄ የሂንዱ ሃሬ (እንደ ሃሬ ክሪሽና) እና የእንግሊዙ ሃሪ (እንደ ንጉስ ሃሪ) ኬር (በጉራጌ)፣ ኧይር (ወሎ) አንድ ናቸው ዎይ ነው ያለው?

መልሱ አው ነው። አንተ አንድ ነገር ብቻ ነው የምታውቀው የአረብኛው አባባል (የአረብኛው አነባበብ)።

ይህን የምለው ለናጋ ቱማ ነው፣
Naga - ይህ እጅግ ጥንታዊና ብዙ ቅርንጫፍ ያለው በሁሉም ቋንቋዎች በጣም ተቀራራቢና ብዙ ግዜ ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ቃል ነው ።

የቃል ፈጣሪዎች ጥንታዊ ግብጾች ናቸው፣ ካ (ቃ፣ጋ፣ ሃ፣ ሻ)ማለት ሃይል ማለት ነው ። ራ ማለት ሰማይ፣ ጸሃይ፣ ብርሃን፣ በላይ፣ ከላይ ያለ ማለት ነው ። ችግሩ በቀምጥ (በድሮ ኮፕት) አነባበን ድምጻቸው ምን እንደ ነበረ ዛሬ በትክክል የሚያውቅ የለም። ድምጽና አክሰት (ቅላጼ) ከህዝብ ህዝብ የጎሮሮ ጄኔቲክስ ይለያያል። አገው ቀ፣ ጸ፣ ጠ፣ ጨ ይላል፣ ይህን ድምጽ የማይችሉ ህዝቦች ብዙ ናቸው። ለማንኝውም ....
Kara ካራ ኦሪጂናሉ የግብጽ ነው ። ዛሬ በኢትዮፒክ ጠን ካራ የምንለው ማለት
ካራ ሃይል ማለት ነው ።
ካራ ሳንጃ፣ ሰንዳ፣ ጎራዴ ማለት ነው ፣ ትርጉሙ ሃይል ያለው መሳሪያ ማለት ነው
Kair - Hair, Heir, Hail ኃይል ማለት ነው ፣ የአረብኛው ንባቤ ያለው እዚህ ነው ።
ካራ ፟ የፈጣሪ ስም ስለነበር በግብጽ (ሆሬ፣ ሃሩ፣ ሆረስ .... ብዙ ነው) ሌላ ትርጉሙ ጌታም ሎርድ፣ ሃያል ማለት ነው
ሃሬ ክሪሽና ሎርድ ክሪሽና ማለት ነው ።
Harry ሃሪ በአሮጌ እንግሊዝኛ ንጉስ፣ ጦረኛ፣ ጦር አዛዝ፣ ወራሪ ማለት ነው ።
በብዙ የስሎቫክና ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቆር፣ ቆሬ፣ ቆሪያ ማለት ጦርነት ማለት ነው
ይህ የሃይልና ሃያልነት ትርጉሙ ማለትም ጠንካራ እንዴት ጤና፣ ድህንነት ወይም ኬር ከሚለው ተያያዘ ካልክ መልሱ አንድ ጤና፣ ደህና፣ ዌል ይሆነ ነገር ጠንካራ ነገር ነው ። ዌልነስ ማለት ጥንካሬ ማለት ነው።

ኢፒዲአራኤ ፟ በካና ራ መሃል ይ ስለመግባቱ ያልከው ስህተት ነው ። ያ ኔዛል ነ፣ ዜዛል ለ ይባላል። ሰዎች አንድ ቃል በቀላሉ ማለት ሲከብዳቸው፣ ሲሰቀጥጣቸው ነ ወይም ለ ያስገባሉ ። ያን ለማወቅ ፊሎሎጂ ማወቅ አለብህ፣ የቃሉን ትክክለኛ ታሪክ ማወቅ አለብህ ።
ካር ከር ትክክል ሲሆን ካይር፣ ከይር፣ ሀይር የሚለው ቃሉን ለማለስለስ በተለምዶ የተጨመረ ነው ። ያን ያደረጉት አረቦች ናቸው።
በእኔ ግምት ቁርዓን ውስጥ ያለ ይመስለኛል ። ለምሳሌ ሸሪዓ (ሕግ፣ ሴራ፣ ሰርዓት) ኬር፣ ኬይር ጋር አንድ ቃል ነው ።
በእኔ ግምት ራሱ አላህ (አላ) የሚለው ቃል ራሱ ካራ ነው፣ ፈጣሪ ሃይል ማለት ነው ።
ለዛሬ ይብቃችሁ .... ኬር!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by Guest1 » 05 Aug 2021, 07:47

በትክክል ካስታወስኩ ኼር እና ኬር የወራረሳሉ ብለሃል። ሃሪ ከሁለቱም የሚገናኝ ይሆን?

አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ የፎረሙ ተሳታፊዎች፣ ሃረ፣ ሃሪ፣ እና ሄረ ከኼር እና ኬር ጋር ግጥምጥሞሽ ነዉ ወይስ የምያገናኛቸዉ ኣለ?

ከድምጽ (spoken language) ወደ ምልክት (written language) ሽግግር የታየበት የጥንት ዘመን ፈረኦኖች የከ እና ኸን ድምጾች ለመለየት ምን ያህል እንዳሰቡ እና እንደለፉ በዚህ ዘመን ይታያችሁዋል?

Naga Tuma
Member+
Posts: 5523
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by Naga Tuma » 05 Aug 2021, 19:30

ሆረስ፣

ካለህ ጊዜ ወስደህ ለግምቴ ማብራሪያ ስለሰጠሀን በጣም ኣመሰግናለሁ።

ከኣሁን በፊት ቋንቋ እንደ ዲኤንኤ ነዉ ስትል ኣስተዉያለሁ። ኣሁን ሳስበዉ ከዲኤንኤ በላይም ይመስልኛል። በማይክሮስኮፕ ማየት የማያስፈልግ፣ በግልጽ የሚሰማ ድምጽ ስላለዉ። በተጨማሪ ዲኤንኤ ከቋንቋ በላይ ቶሎ የመለዋወጥ ሁነታ ያለዉ ይመስለኛል።

ኣሁን ለምሳሌ እንዲሆኑ ሰበ/ሰብ፣ ኼር/ኬር፣ እና ሄረ/ሸርያ የተባሉ ሶስት ቃላት ብቻ የሰው ዘርን ረጅም ታሪክ ኣምቀዉ የያዙ ናቸዉ ብል የተጋነነ ኣይመስልኝም። ድንቅ ነዉ። የዶክተር ቴዎድሮስ ካሳሁንን ዞሮ መጀመርያ ቅኝት ዝንተኣለም ማዳመጥ ነዉ።

ለመረጃ እንዲሆንህ መሰረታቸዉ የቦረና ቋንቋ የሚመስለኝ ሃረ ማለት ኣዲስ፣ ሃሪ ሽበት ማለት ናቸዉ። ሄረም መሰረቱ የቦረና ቋንቋ መሆኑን በዉል ባላዉቅም ትርጉሙ መተዳደርያ ደንብ (ኮንስቲትዩሽን) ሆሮ ጥቅም ላይ የዋለ ነዉ። ሰበ እና ሻብያ፣ ኼር እና ኼይር፣ እና ሄረ እና ሽርያ የትርጉም ልዩነት ኣላቸዉ የሚባል ኣይመስልኝም።

ሌላ መረጃ እንዲሆንህ ኣባ ቆሮ ያደኩበት አከባቢ የተለመደ መደባኛ ስም ነዉ ማለት ይቻላል። ካስተዋሉ ታሪክ ስንቱ ይወራ?

ኣንዳንድ ወጋኖቻችን ለምን የሎሬት ጸጋዬ ችግኞች ሆኖ መቆየት እንደሚመቻችዉ ኣይገባኝም። ሎሬቱ ተነስቶ ኣንተን የታሪክ ዛፍ ባየ።

ስለ ሃረ እና ሃሪ ካነሳን መተሃራን ኣዲስ ጸጉር ማለት በወጣትነት ጊዜ የሰማሁትን ጫወታ እና በስመ ኣብ ጸሎት ያስታዉሳል። ኣብ ወይም አባ ደንብ ኣዉጪ ኣዲስ ጸጉር ወይም ሽበት ያነበረዉ ሰዉ ይሆን፣ ጥንት ጊዜ? ይህ ደግሞ በታሪክ የመጀመርያዉ ኣብ ማን ነበረ ወደሚለዉ ጥያቄ ይወስደናል። በስመ ኣብ ከዛ ሲወራረድ የመጣ ነዉ። ሽበት ያለኝ ነዉ ማለት ያኔ የተጀመረ ይሆን? መጠይቅ ኣይከፋም፣ ጫወታ ቢመስልም። ለማሰላሰል ያህል ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5523
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኼር፣ ኬር፣ ሃሪ

Post by Naga Tuma » 16 Sep 2021, 01:18

ስለ ሃሪ ወይም ሽበት የጠቀስኩኝ ጊዜ ከዛ በፊት ኣስተዉዬ የነበረዉን የሃሪ እና የእንግሊዘኛዉ ቋንቋ ሄየርን (hair) መመሳሰል ዘነጋሁ። ሰሞኑን ኣስታወስኩኝ።

የሄየር ቃል አመጣጥ፥ Middle English: heer; Old English: hǣr; Dutch, German: haar; Old Norse: hār; perhaps from Middle English: haire; Old French, Old High German: hāria; Old English: hǣre; Old Norse: hǣra.

የቃሉ አመጣጥ ምንጭ dictionary.com ነዉ።

ሃሪን ወይም ሽበትን እና ኣብን ወይም አባን ሳስታዉስ ደግሞ የጀርመኑን ሴይንት ንኮለስን ኣስታወስኩኝ። የእኛም የመጀመርያዉ ሽበታሙ ኣብ እንደ ጀርመኑ ሴይንት ንኮለስ ሲከበር የኖረ ቢሆን ምን ይባል ነበር?

Post Reply