Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የአማራ የፖለቲካ ልሂቃን ወደ ቀልባችሁ ኑ። ትንፋሽ ሰብስባችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለነገ ለማሰብ ሞክሩ። ይህን ምስኪን ህዝብ ዛሬም አታስጨርሱት" ታምሩ ሁሊሶ

Post by sarcasm » 04 Aug 2021, 18:19

እንግዴህ ሳማንታ ፓወር ፍላጎቷን ግልጽ አድርጋለች። ሁሉም ከጥቅምት 24 በፊት ወደነበረበት ይመለስ ብላለች

በኢትዮጵያ ጉብኝቷም ይህንን ሃሳብ ነው ጠበቅ አድርጋ የምታነሳው። አብይ እንደሆነ እናቱ ይብዛም ይነስም ትነግሳለህ እንጂ አገር ትመራለህ ብለው ስላልነገሩት፤ የሚሰጠው መልስ የሚገመት ነው። እኔኮ ቆይቻለሁ ውጡ ካልኩኝ አማሮቹ እምቢ አሉኝ እንጂ ማለቱ አይቀርም። የአማራው ልሂቅ የወልቃይት ጉዳይ የኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው በሚል፤ከመላው ኢትዮጵያ ሰራዊት ክተት ተብሎለት እንዳትገላግሉኝ እያለ እየፎከረ ነው።

አብይ፤ ንግስናውን ትንሽ የሚያረዝ መስሎት፤ የአሜሪካ መንግስትን ሃሳብ ቢቀበልና በቃ እንውጣ፤ የብሄር ብሄረሰብ ልዩ ሃይሎችም ወደመጣችሁበት ተመለሱ ቢል፤አማራው ብቻውን በጓንዴ ይዋጋል? ምን ለማምጣት? የአማራ ልሂቃኖች ትልቁ የትግራይ ማስፈራሪያ ከላይ ሌላ ትግራይን የምትጠላ ኤርትራ አለችልን ነው። ይሄኛውን ነገር ብዙ በልባችሁ አታቆዩት። የአሜሪካኖቹን በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እየታያቸው ያለውን ፖሊሲ ካሰባችሁትና በትግራይና በኤርትራ መካከል ( ኢሳያስ ሲነቀል) የሚፈጠር የግኑኝነት አቅምን ግምት ውስጥ ከከተታችሁ፤ የምትሉት ጠላትነት ብዙ ሳይቆይ ሊቀየር የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው።

የአማራ የፖለቲካ ልሂቃንና "አንቂዎች" ወደ ቀልባችሁ ኑ። ትንፋሽ ሰብስባችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለነገ ለማሰብ ሞክሩ። ይህን ምስኪን ህዝብ ዛሬም አታስጨርሱት፤ወደፊትም ቢያንስ እየረገማችሁ እንዳይሞት አድርጉት።

ታምሩ ሁሊሶ
Please wait, video is loading...