Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎች በሌላ ክልል ውስጥ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት (የአማራ ክልል የትግራይ ክልል መሬት መውረር) አንድም ቀን ደግፈው አያውቁም።"

Post by sarcasm » 04 Aug 2021, 13:56

By Dereje Gerefa Tullu

አንድ በጣም እርግጠኛ መሆን የሚቻለው የፌደራል መንግስት

1 የክልል ልዩ ኃይሎች በሌላ ክልል ውስጥ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት አንድም ቀን ደግፈው አያውቁም። ለወደፍቱም ይደግፋሉ ቢዬ አላስብም። ችግሩ በጊዜ ነገሮችን አለመፈፀም ነው። አሁንም ወይ ዛሬ ወይም የዛሬ ወር አሊያም የዛሬ ሁለት ወር እሄንን በግልፅ ተቀብሎ ማስፈፀሙ አይቀርም ። ያንን የማያደርግ ከሆነ ከማይወጣው አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል።

ከዚህ አንፃር የላይኞቹ እሄ ይጠፋቸዋል ቢዬ አልገምትም።

የሰሞኑ የልዩ ኃይል ዘመቻም የህዋሃትን ወደ አፋር መስፋፋት ለመገደብ የተረገ ዘመቻ ነው ብዬ ኣምናለሁ። በኔ ግምት የክልል ልዩ ሃይሎችን በቀጥታ ከማዝመት ለጊዜውም ቢሆን በአንድ የፌደራል እዝ ስር ልዩ ኃይሎችን ማዋቀር እና በፌደራል ፖሊስ ስር እንዲመሩ ማድረግ ህገመንግስታዊም ሞራላዊም ነው።

2 የፌደራል መንግስት የኤርትራ መንግስት ከትግራይ ክልል መውጣት እንዳለበት ከተናገረ ቆይቷል። ችግሩ የነበረው እሄንን በአግባቡ ማስፈፀሙ ላይ ነው።
የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል ከመውጣቱ በፊት የኤርትራ ኃይል ከአብዛኛው የትግራይ አከባቢ መውጣቱ ይታወቃል። የፌደራል መንግስቱ ከትግራይ ከወጣ በኃላ የኤርትራ ኃይል ተመልሶ ከገባ ያ ሌላ ታሪክ ነው። አቀራረቡም ሌላ ነው።

3 የፌደራል መንግስት ከትግራይ ጋር ተያይዞ ያላቀረበው እና ማቅረብ ያለበት ጠቅለል ያለ የሳላም ፓኬጅ ነው። አሁን ያንን በግልፅ በማቅረብ proactive ሆኖ ዲፕሎማሲውንም ሆነ የሰላሙን መንገድ መምራት አለበት። አሁን ባለው ሁኔታ መንግስት የሰላም መንገዱን ቀድሞ ካልመራ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ለመምራት ተንሳፍስፏል።

4 የኢትዮጵያ መንግስት ችግሮች ያሉት ትግራይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢ መሆኑን ተረድቶ ሁሉን አቀፍ Dialogue በመጀመር ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀስ መጀመር ለሀገራችንም ሆነ ለህዝባችን እጅግ ወሳኝ መሆኑን መረዳት አለበት።አሁን ላለንበት አጣብቂኝ ሁሉን አቀፍ ውይይት ወደ መፍትሄው ያቀርበናል።
Please wait, video is loading...