Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"አልዘምትም! ወንድሜን አልገድልም ፣ በወንድሜ አልሞትም!"- በላይ በቀለ ወያ

Post by sarcasm » 01 Aug 2021, 11:35

የአቋም መግለጫ !!!
(በላይ በቀለ ወያ #ከሰላም ግንባር)


የዛሬ ሀያ ዓመት
በሁለት አካሎች ፣ የአስተሳሰብ ጥመት
ለብዙዎች እልቂት ፣ ለጥቂቶች ሹመት
ምክንያት የሆነ ፥ "ክተት" እና "ዝመት"
ልክ እንደ ነጋሪት
በሚጎሰም ጊዜ ፣ የኔ አባት ዘምቷል
የቀኝ አይኑንና ፣ የግራ እግሩን አቷል
በጦርነት ግንባር ፣ ፈሶ ቀርቷል ደሙ
ግን ግን እስከዛሬ
አልተፈታለትም
"አንድነት" የሚባል ፣ ያዘመተው ህልሙ።
ዛሬም አንድ ዓይና ነው ፣ ዛሬም ያነክሳል
ኢትዮ ኤርትራ
እርቅ ወረደ ሲባል ፣ ይስቃል ያለቅሳል
"ወይ ታሪክ" እያለ
ሳቅና እንባውን ፣ ባንድ ዓይኑ ያፈሳል
"ታሪኬ" የሚለው
ታሪክ ሲደገም ሲያይ ፣ ቁስሉን ያስታውሳል።
ይስቃል ያለቅሳል ፣ያለቅሳል ይስቃል
እኔ ግን እላለሁ
"ከታሪክ የሚማር ፣ ታሪክ መስራት ያውቃል
በነግ ታሪክ ያፍራል ፣ ከትላንት ማይማር
ዛሬ ላይ የነቃ
ሺ ህዝብ አያስበላም ፣ ለጥቂቶች ቁማር።
ስለዚህ አልዘምትም!
ወንድሜን አልገድልም ፣ በወንድሜ አልሞትም!
ጠንቅቄ አውቃለሁ!
ፍቅር ያሰረውን ፣ በጦር አይፈቱትም!
።።።።።
ከሀያ ዓመት ኋላ
ለብዙዎች እልቂት ፣ ለጥቂቶች ተድላ
ሀገር እንደ ድመት ፣ ልጇን እንድትበላ
በዛም በዚም በኩል
ዝመት ክተት ብሎ ፣ ጦሩን ያሰልፋል
ከታሪክ ተምሮ
"ታረቅ ተወያይ" ሚል ፣ እንዴት አንድ ይጠፋል?!
ነገ እርቅ ላይቀር
ሰው እንዴት ታሪኩን ፣ ፀፀት ላይ ይፅፋል?!
።።
እኔ ግን እላለሁ!
ባለጊዜ ያልፋል ፣ ሀገር ግን አታልፍም
ወንድሜን ገድዬ ፣ ፀፀቴን አልፅፍም
ለጥቂቶች ስልጣን ፣ ሺህ ሆኜ አልረግፍም!
ስለዚህ አልዘምትም
ወንድሜን አልገድልም ፣ በወንድሜ አልሞትም።
ለጥቂቶች ስልጣን ፣ ለጥቂቶች ቁማር
አውቃለሁኝና
በታሪኩ እንደሚያፍር ፣ ከታሪክ ማይማር
ላሉት ልቦና ይስጥ ፣ ለሞቱት ነፍስ ይማር!!!
Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አልዘምትም! ወንድሜን አልገድልም ፣ በወንድሜ አልሞትም!"- በላይ በቀለ ወያ

Post by sarcasm » 07 Aug 2021, 20:04

ለበጎ ነገር የረፈደ ጊዜ የለም ይባላል። መጨረሻው ላይቀዬር ነገር የሚሞቱ ዜጎችን ቁጥር መቀነስ ይሻለናል።




Please wait, video is loading...

Post Reply