Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12583
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ትግራዋይ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ማን ነበር?

Post by Thomas H » 31 Jul 2021, 12:02

መልካም ልደት !

ከ 134 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ደራሲ፣ ሀኪምና የምጣኔ ሐብት ጥናት ባለሙያ የነበሩት ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የተወለዱበት ዕለት ነበር።

ነጋድራስ ገ/ሕይወት የተወለዱት ታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወደኋላ መቅረት አሳስቧቸው ከእድሜያቸው በላይ የደከሙ ምሁር ናቸው፡፡ ምዕራባውያን ተግብረዋቸው ታዋቂና ገናና የሆኑባቸውን የምጣኔ ሀብት ሳይንስ (Economics) ጽንሰ ሃሳቦች ነጋድራስ ገብረሕይወት ከብዙ ዓመታት በፊት ቀድመው ያውቋቸው ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፣ የነጋድራስ ገብረሕይወት ሃሳቦች የረቀቁና የመጠቁ በመሆናቸው ለብዙ ምርምሮችና የፖሊሲ ሃሳቦች ግንባር ቀደም ግብዓት እንደሚሆኑም ምሁራኑ ይስማማሉ፡፡
የነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝን የምጣኔ ሀብት ጽንሰ ሃሳቦች አዋቂነት ደጋግመው ከሚናገሩት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት የምጣኔ ሀብት ጥናት ባለሙያው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ፣ ‹‹ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ በምጣኔ ሐብት ዘርፍ፣ በተለይም በልማታዊ ምጣኔ ሀብት (Development Economics) መስክ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የዓለማችን ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው›› ይላሉ፡፡


‹‹መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር›› የተባለውና ‹‹State and Economy of Early 20th Century Ethiopia›› ተብሎ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ የታተመው መጽሐፋቸው፣ ለብዙ ችግሮች መፍትሄ የሚሆኑና እጅግ የበዛ ፋይዳ ያላቸውን የምጣኔ ሀብት ጽንሰ ሃሳቦችን ያካተተ መጽሐፍ ነው፡፡
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ወደ ጀርመንና አውስትራሊያ በመሄድ የሕክምና ትምህርት አጥንተዋል፡፡ ትግራይ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝን በሞት የተነጠቀችው ገና በጎልማሳነት እድሜያቸው የመጀመሪያ ዓመታት ነበር፡፡











Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ትግራዋይ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ማን ነበር?

Post by Abe Abraham » 31 Jul 2021, 13:43



Tigrayans are very funny. Ruth gual Tafere, Tigraweyti ? :lol: Negadras Wedi Tigré Baykedagn, Tigraway ? Addis Alem Balema, Tigraway ? Getachew Reda, Tigraway ? atayo kidma rHuQ kiedka techawet !! :lol: :lol:

Post Reply