Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ወያኔ የባህር ዳርን ወጣት ገደለ" ሲባል እውነት እየመሰለኝ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራዮች የተዛባ አመለካከት ነበረኝ። ለካስ ገራፊዎቹ የእኛዎቹ ጉዶች ናቸው"

Post by sarcasm » 30 Jul 2021, 17:16

ውጭ ሀገር እያለሁ "ወያኔ የባህር ዳርን ወጣት ገደለ" ሲባል እውነት እየመሰለኝ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራዮች የተዛባ አመለካከት ነበረኝ። ከለውጡ በሁዋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሼ ከቀበሌ እስከ ክልል ያለውን ጉድ ከተመለከትኩ በሁዋላ ግን ግለሂስ አድርጌ አመለካከቴን ቀየርኩ ፤ የትግራይ ህዝብንም በይፋ ይቅርታ ጠየኩ። ለካስ ገራፊዎቹ የእኛዎቹ ጉዶች ናቸው። አሳሪዎቹ መሃላችን የበቀሉ እምቦጮች ናቸው። ገዳዮቹ አብረውን የሚኖሩት ጎረቤቶቻችን ናቸው። ዘራፊዎቹና መሬት ነጣቂዎቹ ከሌላ የመጡ ሳይሆን እዚሁ የሚኖሩ ስግብግቦች ናቸው።

እኔን ያሳደደኝና የበደለኝ አንድም ትግሬ የለም። ዛሬ ወንድሞቻችንን የሚያስረውና የሚያሳድደው ማን ነው? "ተላላኪ ነበርን" ያሉን ሰዎች፣ ይልኩን ነበር ያሉት ወያኔ መቀሌ ከሄደም በሁዋላ መዝረፍ፣ ማሰር ፣መግረፍና መግደል አላቆሙም።

ስለዚህ በፊትም ታዘው ሳይሆን አምነውበት ወንጀል ሲሰሩ የነበሩ ወንጀሎች ናቸው ማለት ነው። ዛሬ ከቀድሞ ጎዶቻቸው ጋር ከተጣሉ እነሱ ራሳቸው ከፊት ተሰልፈው ይግጠሙ እንጅ እኛ ምን በወጣን እንሞትላቸዋለን? በጭራሽ! እናስተውል፤እንመርምር!

Haileyesus Adamu
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "ወያኔ የባህር ዳርን ወጣት ገደለ" ሲባል እውነት እየመሰለኝ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራዮች የተዛባ አመለካከት ነበረኝ። ለካስ ገራፊዎቹ የእኛዎቹ ጉዶች ናቸው"

Post by Abere » 30 Jul 2021, 17:28

ይኸ ዝም ብሎ ተቀምጧል እንዴ? ይመጣል የተባለው ዐፄ ቴዎድሮስ ዘሳልሥ (ሦስተኛው) የሰላም ንጉሥ እርሱ መስሎኝ። ወይጉዲ! ሀሺሻሙ ቴዎድሮስ ነው ማለት ነው። ኃይለ ሀሺሽ ቢለው ይሻላል የፌስቡክ ስመ-ንግሥናውን :lol: :lol: :lol:

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ወያኔ የባህር ዳርን ወጣት ገደለ" ሲባል እውነት እየመሰለኝ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራዮች የተዛባ አመለካከት ነበረኝ። ለካስ ገራፊዎቹ የእኛዎቹ ጉዶች ናቸው"

Post by sarcasm » 17 Sep 2021, 17:33

sarcasm wrote:
30 Jul 2021, 17:16
ዛሬ ወንድሞቻችንን የሚያስረውና የሚያሳድደው ማን ነው? "ተላላኪ ነበርን" ያሉን ሰዎች፣ ይልኩን ነበር ያሉት ወያኔ መቀሌ ከሄደም በሁዋላ መዝረፍ፣ ማሰር ፣መግረፍና መግደል አላቆሙም።

ስለዚህ በፊትም ታዘው ሳይሆን አምነውበት ወንጀል ሲሰሩ የነበሩ ወንጀሎች ናቸው ማለት ነው። ዛሬ ከቀድሞ ጎዶቻቸው ጋር ከተጣሉ እነሱ ራሳቸው ከፊት ተሰልፈው ይግጠሙ እንጅ እኛ ምን በወጣን እንሞትላቸዋለን? በጭራሽ! እናስተውል፤እንመርምር!

Haileyesus Adamu
Please wait, video is loading...

Post Reply