Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሱዳን ተላላኪነት ጣራ ነካ! በልኳ ቀሚስ እንዲሰፋላት ግድ ይላል!!

Post by Horus » 29 Jul 2021, 14:24

የሱዳን ጥጋብ ከምን ከምን የመነጨው? ማንን ተማምና ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ምትፈተፍት ?

አሜሪካ ጣልቃ የሚገባባቸው መንገዶች 5 ናቸው፤ (ሲ አይ ኤ የሚጠቀምባቸው ሞዴሎች)

አንድ፣ አቢይ አህመድ ከቻይናና ሩሲያ ርቆ ያሜሪካ ተላላኪ እንዲሆን በዚህ በዚያ ብለው ግፊትና ተጽዕኖ ማድረግ

ሁለት፣ የአቢይ መንግስት እንዳይረጋጋ ዴስታቢላይዝ ማድረግ (ኢኮኖሚ እቀባ ወዘተ)

ሶስት፣ የተራዘመ የውክልና ፕሮክሲ ጦርነት በአቢይ መንግስት ላይ ማካሄድ (ትህነግ፣ ሱዳን። ግብጽ)

አራት፣ በአቢይ መንግስት ላይ ኩዴታ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ (ዳዊት ወልደ ጎርጊስ መሰል ነባር ሰላዮችና የትግሬ ኤኔራሎችን በመጠቀም)

አምስት፣ ይህ ሁሉ ካልሆነ በአቢይ ላይ አሳሲኔሽን ግድያ መምከር ናቸው (የራሱ ያቢይ የቅርብ ዘበኞችን በመጠቀም)

ኢትዮጵያ ምን ማድረግ አለባት?
አንድ፣ ከዳር እስከ ዳር እንደ አንድ ሕዝብ እንደ አንድ ሰው መቆም፣
ሁለት፣ ያገር አንድነት ማጽናት፣
ሶስት፣ የመግስት አንድነት ማጽናት፣
አራር፣ የሰራዊትና ደህንነት አንድነት ማጽናት፣
አምስት፣ በአቢይ ዙሪያ ያሉ ዘቦችን 100% ታማኝ ማድረግ
ስድት፣ መፈንቅል የማድረግ እድል ያላቸው የጦርና የስለላ አካልትን 100% ቁጥጥር ማድረግ፣ ከመንግስት ውጭ ያሉት ወራዶች እንደ ዳዊትና ሰዬ መሰሎችን 100% ማጋለጥ ማድረግ፣
ሰባት፣ በፕሮክሲ ሚዋጋው ያሜርካ ግብጽ ተላላኪ የትግሬ ባንዳን ሙልጭ አድርጎ መደምሰስ፣
ስምንት፣ ያሜርካ የኢኮኖሚ ጦርነትን በህዝባዊ ትብብር፣ መዋጮ፣ የባንዳ ኢኮኖሚን በማክሰም መቋቋም
ዘጠኝ፣ ያሜርካንን ግፊት በፖለቲካና ዲፕሎማቲክ ህዝባዊ እምቢተኘት መታገል,
ኢትዮጵያ ድል አድራጊ !!