Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጥሪ ለኦሮሞ፥ አማራ፥ አፋር፥ ሶማሊ፥ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ

Post by sarcasm » 27 Jul 2021, 17:32

አብይ አሕመድ እና ጀሌዎቹ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው እስር እየተጠባበቁ ያሉ ያበቃላቸው ወንጀሎች ናቸው። እነሱ በቀቢፀ ተስፋ እናነተን ይዘው ለመጥፋት፥ የዘር ማጥፋት ከባድ ወንጀል ከናንተ፥ ከልጆቻችሁ እና ከታሪካችሁ ኣጣብቀው ትውልዳችሁ ኣንገቱ ቀና እንዳይል ኣድርገው ለመጥፋት ወስነዋል። ይህ ከባድ ወንጀል ኣይለቅም። በአይሁዶች ዘር የማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ህዝቦች እስከ አሁን ያፍሩበታል፥ ሲያፍሩበትም ይኖራሉ። ይህንን መቸም ሳትገነዘቡት ቀርታችሁ ኣይደለም።

የዘር ማጥፋት ከመሰለ ከባድ ወንጀል ራስችሁን እንድታርቁ፥ ትውልድና እና ታሪካችሁ ከማቈሸስ እንትቈጠቡ ወገናችሁ የሆነውን የትግራይ ህዝብ ጥሪ ያቀርብላቸዋል። የትግራይ ህዝብ ጠላታችሁ ሆኖ ኣያውቅም፥ ሊሆንም ኣይችምልም። ስለዚህ በዓለም የተከሰሱ ወንጀለኞች ይዟችሁ እንዲጠፉ ኣትፍቀዱ። ራሳችሁን ከኣስነዋሪ እና ከባድ ከሆኖው የዘር ማጥፋት ወንጀል ኣርቁ ብቻ ሳይሆን፥ ይህንን ዓለምአቀፍ ወንጀል ወጥታችሁ ኰንኑ! ከትግራይ ህዝብ ጐን ቈማችሁ ራሳችሁንና፥ ትውልድን እና ታሪካችሁን የምታዱንበት ጊዜ ኣሁን ነው።

ይህ በተናጠልም ለእያንዳዱ ሰው ይመለከታል። ወንጀለኞች መጠየቃቸው ኣይቀርም። ስለዚህ እያንዳድንዱ ሰው ራሱን ከነዚህ ወንጀለኞች በትብብርም ይሁን በሌላ ግኑኝነት ካለው ይጠየቃል። ይቀጣልም፥ ሲያፍርም ይኖራል! ስለዚህ በግልም ከዚህ ከባድ የዘር ማጥፋት ወንጀል መራቅ ያስፈልጋል። ኣሁን!
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጥሪ ለኦሮሞ፥ አማራ፥ አፋር፥ ሶማሊ፥ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ

Post by Abere » 27 Jul 2021, 18:16

መፍትሄው እኮ ቅንነት ካለ ቀላል ነው። ወያኔ ለምን ወረራ ውስጥ ገባ? ለምን ከትግራይ ክፍለ ሀገር በማለፍ የሌሎች የሰላም ጠንቅ ይሆናል? ትንኮሳ ከቆመ እኮ ዕልቂት አይኖርም። ለመደማመጥ ከተፈለገ የጥይት ድምፅ ቆሞ ወያኔዎች ከወረሩት የአማራ ቦታዎች ራያ፣ሁመራ፣ወልቃይት ወጠተው መነጋገር ይቻላል። የሚሞተው ከሁሉም ወገን ያለው የኛው ወገን ነው። ዋ!ትግሬን ብቻ ትገድሉና በታሪክ ተወቃሽ ትሆናላችሁ ማለት ፌዝ ነው። ወያኔም 5 ሚሊዮን አማራ አጥፍታ ችለናል። የዚህ ጦርነት ብቸኛ ተጠያቂ ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው። የሚያሳዝነው ግን የዚህ ዘመን ትውልድ ሁነን ይህን በማየታችን ነው። ሰው ጠፍቶ ፤ ሽማግሌ አልቆ የፈረንጅ መጫውቻ መቆመሪያ መሆናችን። በእውነት ትግሬ አብዷል ቆም ብሎ ማሰብ አለበት። ሰው ከጠፋ መሬት ምን ይሰራል። ባዶ ቦታ ዘመድ አይሆን።

Post Reply