Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከሠመራ ወደ አዲስ አበባ ተሸኙ

Post by sarcasm » 27 Jul 2021, 15:41

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከሠመራ ወደ አዲስ አበባ ተሸኙ

#Ethiopia | በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የነበሩ 324 ተማሪዎች ዛሬ ከአፋር ክልል ሠመራ ከተማ ወደ አዲስ አበባ መሸኘታቸውን የሠመራ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።
የመከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልልን ለቆ ከወጣ ጀምሮ በክልሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ ወላጆችን ሲያሳስብ ቆይቷል።

የተማሪ ወላጆችም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት ልጆቻቸውን እንዲያገናኛቸው ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል።
የሠመራ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዱራህማን ከድር ለኢዜአ እንዳሉት፤ ትናንት ማታ ከአፋር አብዓላ ድንበር 324 ተማሪዎች ወደ ሠመራ ዩኒቨርስቲ ገብተዋል።

ተማሪዎቹ ሠመራ ዩኒቨርስቲ አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መሸኘታቸውንም ገልጸዋል።
ተጨማሪ ከ400 በላይ ተማሪዎች ከአብዓላ ወደ ሠመራ ከተማ ዛሬ እንደሚገቡም ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የሠመራ ዩኒቨርስቲ አስፈላጊውን መስተንግዶ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ እንደሸኛቸውም ዶክተር አብዱራህማን አረጋግጠዋል።
Please wait, video is loading...