Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33275
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ: ሁሉም አማራ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ጥሪ አቀረቡ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 25 Jul 2021, 10:56

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
1tcSponhsorehedm ·
ሁሉም አማራ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ አቀረቡ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በዳንሻ ከተማ ዛሬ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል። የሰልፉ ዓላማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ክብር ለመስጠት፣ ለሁለተኛው ዙር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ደስታን ለመግለጽ፣ አሸባሪውን ትህነግ ማውገዝ እና ሕዝቡ የሕልውና ዘመቻው ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ ነው ተብሏል።
ውስጣዊ አንድነትን በማጠንከር የጋራ ጠላትን በብቃት መመከት እንደሚገባ በሰልፉ ተነስቷል። ለዚህም ሕዝቡን መስለው ለጠላት የሚሠሩ አካላትን መምከር ይገባል፤ የማያርፉ ከሆነ ግን ለሕዝቡ ህልውና ሲባል የማያዳግም ርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተመላክቷል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ "ዛሬ የተገናኘነው ዲስኩር ለማሰማት ሳይሆን የመጣብንን ወራሪ አውቀን የመጨረሻውን ፍልሚያ ለመግጠም ነው" ብለዋል። ኮሎኔሉ አሸባሪው ትህነግ አማራን ለማጥፋት መነሳቱን አንስተዋል፡፡ ይህንን ለመመከትም የአማራ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት አድርጎ በነቂስ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ነው ጥሪ ያቀረቡት።
የህልውና ዘመቻው የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ራስን ለመከላከልና ለማስከበር መሰለፍ ይገባል ብለዋል። ለአማራና ለኢትዮጵያ መሞት ክብር ነው ብለን ቀድመን መሰለፍ አለብንም ብለዋል። ኮሎኔል ደመቀ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ቁርጥ ቀን በመሆኑ ማንኛውም የታጠቀና ትጥቅ የሌለው ኀይል ወደ ማክሰኞ ገበያ፣ ወፍ አርግፍና ሑመራ መክተትና በጋራ ዘምቶ ጠላትን ማሸነፍ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ክብራችንን ስለምንመርጥ ሁላችንም ለሀገራችን መሞት ይገባናል ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የሃይማኖት አባቶችም ጦር ግንባር ድረስ ተሰልፈው በጸሎትና በዱአ ሊያግዙ ይገባል ብለዋል። አቅም ያለው ታጥቆ መግጠም ያልቻለ ደግሞ በሞራልና በስንቅ አቅርቦት ሊደግፍ እንደሚገባም አሳስበዋል። በርሃ ያለ ባለመሳሪያ ሁሉ ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንዲከትም መመሪያ ሰጥተዋል።
የከተማው ሕዝብ በሰልፉ ላይ "የማንነት ጥያቄ ዴሞክራሲያዊ መብታችን ነው፤ የአማራ ሕዝብ በሀገር መከላከያ ሠራዊት አይደራደርም፤ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለፋኖና ሚሊሻ እንዲሁም ለመከላከያ ክብር ይገባል፤ እኛ አማራዎች የምናወራርደው እንጂ የሚያወራረድብን ሂሳብ የለም፤” እና መሰል መልእክቶችን አንግቦ ነው አደባባይ የወጣው፡፡ አስተያየታቸውን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎችም ስለ ክብራቸው፣ ስለ ነጻነታቸውና ስለ ሀገራቸው ሕልውና ሲሉ ግንባር ለመሰለፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። በሰላማዊ ሰልፉ የዞኑን አስተዳዳሪ ጨምሮ ሌሎች አካላትም ተገኝተዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

EthioRedSea
Member
Posts: 4089
Joined: 31 Aug 2019, 11:55

Re: ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ: ሁሉም አማራ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ጥሪ አቀረቡ!!! WEEY GUUD !!!

Post by EthioRedSea » 25 Jul 2021, 11:50

Hamachenawi Tarik! Kill yourself! Amara people are not idiots to follow this guy. they know Tigray is their partner now and in the future.

Post Reply