Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

ሰው መሳይ ጭራቅ ታምራት ላይኔ!

Post by Masud » 25 Jul 2021, 03:37



ሰው መሳይ #ጭራቅ!
የምዕራባውያን ወኪል የጁንታዉ አዳኝ ታምራት ላይኔ !!!
የቀድሞው የብአዴን ታጋይ እና የመለስ ዜናዊ የወጥ ቤት ሀላፊ ታምራት ላይኔ በስልጣን ዘመኑ ለአንድም ጊዜ በራሱ ውሳኔ ምንም አይነት ስራ ሰርቶ እንደማያውቅ በእጅጉ የሚነገርለት፣ በአማራ ስም የቆመ ፖለቲከኛ፣ ነገር ግን አማራን ክፉኛ የሚጠላ የህወሀት ታማኝ ተላላኪ ነበር። ይህ ግለሰብ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኦነግን ስም ሽፋን በማድረግ በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ ከ 215,000 በላይ አማራዎች እና የአማራ ተወላጆች ምንም በማያውቁት ሁኔታ በታምራት ላይኔ አመራር ሰጪነት ተገድለው በጅምላ ተቀብረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ህወሀት በዚሁ በምስራቅ አካባቢ ላደረገው "ኦነግን የማፅዳት ዘመቻ" በሚል በከፈተው ኦፐሬሽን የአመራርነቱን ቦታ ወስዶ ሲያስፈፅም የነበረ ግለሰብ ነው። በዚህም ዘመቻ ከ 137,000 በላይ ኦሮሞዎች ተገድለዋል፤ ከ 75,000 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል። ይህ የመለስ ዜናዊ ተልዕኮ አስፈፃሚ፣ ለህወሀትን የበላይነት ለማረጋገጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆችን በማስገደል በጅምላ መቃብር ውስጥ እንዲቀበሩ አድርጓል። ይህን ወንጀል በመፈፀሙም የራስ መተማመኑን በማጣቱ ህወሀት ባልረባ ምክንያት ስታስረው ፀጥ ለጥ ብሎ ተቀብሎ ሲማቅቅ የነበረው። አሁንም በህወሀት የተሰጠው ክህነት ስላለቀቀው በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ግፍ ሲፈፅም ከነበረው ህወሀት ጎን በመሰለፍ ሽማግሌ ልሁን እያለ ያለው። ውድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በተለይ ኦሮሞ እና አማራ ይህ ግለሰብ በድጋሚ ከህወሀት የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም እላይ ታች የሚል ታሪካዊ ጠላታችን ስለሆነ በትኩረት ልንከታተለው ይገባል።
From FB