Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የትግላችን መናሻ አገው ምድር የትግላችን መዳረሻ አገውን የክልል ባለቤት ማድረግ ነው - Agaw Rise

Post by sarcasm » 24 Jul 2021, 18:54

የትግላችን መናሻ አገው ምድር የትግላችን መዳረሻ አገውን የክልል ባለቤት ማድረግ ነው፦

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አገውነት ምስጢር ነው፤ አገውነት ጥበብ ነው፤ አገውነት ታሪክ ሰሪነት ነው፤ አገውነት ለተነሳለት ዓላማ የትኛውንም መስዋትነት በመክፈል ግብ መምታት ነው፤ አገውነት ንዋይ ፍቅርን በሩቁ መፀየፍ ነው፤ አገውነት የዕውቀት አምባነት ነው፤ አገውነት አጭበርባሪነትን ማጋለጥ እና መታገል ነው፤ አገውነት የወይራን ቀንበጥ ከጥፋት ውሃ በኋላ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲሉ ሰማይንና ምድርን ማስታረቅ ነው፤ አገውነት ከንኆ ጀምሮ የዓለም ተምሳሌትነትን ማስመስከረ ነው፤ አገውነት የስልጣኔን መነሻ ከፑንት እስከ ዳማት ለትውልድ ትውልድ ማውረስ ነው፤ አገውነት ከአክሱም ስልጣኔ እስከ ላሊ በላ ለትውልድ ማስተላለፍ ነው፤ አገውነት ከፋሲል ግንብ ህንፃ መገንባት እስከ አዳዲ ማሪያም ማነፅ ድረስ ታሪክ ሰሪነት ነው። አዎ አገውነት ዘመን ተሸጋሪነትና አድማሳዊነት ነው የምንለው በእነዚህ ዘመን በማይሽራቸው ምክንያቶች ነው።

አገውነት ኢትዮጵያዊነት ነው። የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የዕድገት መሠረቱ አገውነት ነው። አዎ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የስልጣኔ ባለቤት አገው ነው። በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የስልጣኔ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ግለሰብ (ማህበረሰብ) ካለ በመረጃ ሳይሆን በማስረጃ ላይ ተመስርተን መከራከር እንችላለን። አገው ዕድልና መድረክ እንጂ ያጣው ማስረጃው እልፍ አልፍ ነው። አገውነትን ለማጥፋት የሚሯሯጡትም እልፍ አልፍ የአገው ታሪክ ሰሪነትና ገድል ሰሪነትን ለመዝረፍ ነው።

ሰለሞናውያን አገውነትን በስም ለመጥራት የሚያዳግታቸው ነገር ቢኖር ከተራራ በላይ የገዘፈ ታሪክ፣ ገድል እና ለኢትዮጵያ ያወረሱት ሁሉን አቀፍ ዘመነ ተሻጋሪ የሰው ሰራሽ ሀብቶችን ያወረሱ የማህበረሰብ ክፍሎች ስያሜ የያዘ በመሆኑ ነው።

አገው የዛሬውን አያርግ እንጂ ለኢትዮጵያ መሠረት ነው የምንለው እንደሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎ ለሚድያ ፍጆታ በጉራ ላይ ተመስርተን ሳይሆን አንቱ በተባሉ አገራ አቀፍና ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች ባረጋገጡት ተጨባጭ ግኝት ላይ ተመስረተን ነው። አገውነት ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካውያንና ለዓለም ማህበሰብ ተምሳሌትነትን ያረጋገጠ መሆኑን በተጨባጭ የግኝት ማስረጃ በማስደገፍ ነው። ከአገው በላይ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ቀደምት የስልጣኔ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል እስኪ ይምጣ?
በዘመነኞቹ የአገው ጠላቶች የአገው ማንነት እንዲጠፋ ( ከታሪክ ድርሳናት እንዲሰረዝ) ቢፈረጅበትም በፈጣሪ ዘንድ የተቀደሰና የተወደሰ በመሆኑ በምድርም ሆነ በሰማይ ቋንቋችንና ማንነታችን እንዲጠፋ በፈጣሪ ፍርድ አልተሰጠውም። ምክንያቱም አገውነት በሲና በረሃ በባቢሎን ከተማ በንጉስ ናምሩድ የተወሰነውን ሰማይ ጠቀስ ህንፃን ለመገንባት በመሞከሩ የዓለም ህዝቦች የሚምግባቡበ አንድ አገውኛ ቋንቋ በእግዚአብሔር እርግማን በዓለማችን በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ቋንቋዎች እንዲበዙ ከመፈረዱ በፊት የነበረ በዓለማችን ብቸኛ የሰው ልጆች ከፈጣሪ ጋር ይግባቡበት የነበረ የተቀደሰ ቋንቋ ነው አገውኛ።

አገዎች መረዳትና ማወቅ ያለባችሁ ሃቅ ነገር ቢኖር አገውነት በዘመነኞቹ ፀረ-አገዎች የማይጠፋ ግን ማንነታችን በትልቅ ፈተና ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባውና ለአገውነት መከታና ጋሻ፥ ግድግዳና ግንብ እንድንሆን እኔንና በእኔ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ነበልባል እና ነብሮ የአገው ልጆችን ለምሳሌ አምጥቶልን አሁን ላይ አገውነት ዳግም ወደ ቀድም ገናናነት እንዲመለስ እየተደረገ ይገኛል። ይብላኝ ለፀረ-አገዎች እንጂ። የአገው ህዝብን ግን ህገ መንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን "የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትነትን" በክንዳችን እውን እናደርጋለን።

::::::::::::::::::::::::::::: አገውነት ዘመን ተሻጋሪነት!!!!::::::::::::::::::
Please wait, video is loading...

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: የትግላችን መናሻ አገው ምድር የትግላችን መዳረሻ አገውን የክልል ባለቤት ማድረግ ነው - Agaw Rise

Post by Noble Amhara » 24 Jul 2021, 18:57

Another gimbcadre of TPLF opening a new Facebook account writing only in amarigna claiming to be agew :mrgreen: :mrgreen:
Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: የትግላችን መናሻ አገው ምድር የትግላችን መዳረሻ አገውን የክልል ባለቤት ማድረግ ነው - Agaw Rise

Post by Sam Ebalalehu » 24 Jul 2021, 19:04

Eden that is why exactly Ethiopians hate TPLF to death. You guys are merchants of division. The more Ethiopians are divided, the TPLF knuckleheads think, the better for TPLF. Wrong mathematics at the wrong time.

Post Reply