Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Horus » 24 Jul 2021, 14:39

Samsara
Member
Posts: 16
Joined: 25 Jun 2019, 00:10

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Samsara » 24 Jul 2021, 15:01

ደስ ይላል፣ በዚህ አጋጣሚ ጥያቄ ልጠይቅህ፣ ለምንድነው ብዙ ጉራጌዎች የኦሮሞ አያት እና ቅድመ አያት ስም ያላቸው? ታሪካዊ አመጣጡን ለማወቅ ነው ፣

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Horus » 24 Jul 2021, 15:26

Samsara wrote:
24 Jul 2021, 15:01
ደስ ይላል፣ በዚህ አጋጣሚ ጥያቄ ልጠይቅህ፣ ለምንድነው ብዙ ጉራጌዎች የኦሮሞ አያት እና ቅድመ አያት ስም ያላቸው? ታሪካዊ አመጣጡን ለማወቅ ነው ፣
ሳምሳራ
ይህ ካንድ በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች ባህሪ ነው ። አማራና ኦሮሞ ድንበር ላይ ያሉ ህዝቦች ባይሊጓል ናቸው። ቆንጆ ነው ብለው ባሰቡት ቃል ይሰይማሉ። በኦሮሞና ጉራጌ ድንበር ያሉት ኦሮሞችም ጉራጌዎችም ስም የለዋወጣሉ። ይህ ብቻ አይደለም ላንተ ኦሮምኛ ሚመስልህ ቃል አመጣጡ ጉራጌኛ ሆኖ ታገኘዋለህ ። ምሳሌ ልስጥህ
ደበላ የኦሮሞ ስም ይመስልሃል፣ ግን ድበል ማለት ድገም፣ ሰብስብ ግዕዝ ነው ። በሌላ በኩል ለምሳሌ የታዬ ደንዳ አሬዶ ስም ወሰድ። አሬዶ የኦሮሞ ቃል ይመስልሃል፣ ግን አረዳ፣ አርዴ ግዕዝ ሲሆን ልጅ፣ ወልዴ ማለት ማለት ነው። ለምሳሌ ባጫ ደበሌን ወሰድ ። ባጫ ማለት ባሻ ማለት ነው ። አለቃ፣ ሃይሉ እንደ ማለት ነው ። ኬሮ፣ ኬር ማለት ጉራጌኛ ነው ። ጋሪ ኦሮሞም ጉራጌም የሚሰየሙበት ቃል ነው፣ የቃሉ ስር ኬር፣ ኬሮ የሚለው ነው ። ሰላማዊ፣ ጤና ማለት ነው። ስለዚህ የጥያቄህ መልስ ባይሊጓል ወይም ባለሁለት ሶስት ቋንቋ ተናጋሪ መሆን ማለት ነው ። ይህ የሸዋ ሁሉ ባህሪ ነው ። ስም ምን ጎሳ፣ ምን ዘር እንደ ሆንክ አያሳይም!

Samsara
Member
Posts: 16
Joined: 25 Jun 2019, 00:10

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Samsara » 24 Jul 2021, 15:43

እሺ፣ ለዝርዝር መልስህ አመሰግናለሁ፣ ትርጉማቸውን ስላነሳህ በዚሁ ዲባባ የሚለውን ብትነግረኝ ደስ ይለኛል ፣ ይሄም በጉራጌዎች ውስጥ ስላየሁት ነው

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Horus » 24 Jul 2021, 16:02

Samsara wrote:
24 Jul 2021, 15:43
እሺ፣ ለዝርዝር መልስህ አመሰግናለሁ፣ ትርጉማቸውን ስላነሳህ በዚሁ ዲባባ የሚለውን ብትነግረኝ ደስ ይለኛል ፣ ይሄም በጉራጌዎች ውስጥ ስላየሁት ነው
ዲባባ ደበበ ማለት ነው፣ ድባብ ያለው ሆነ ማለት ነው!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Guest1 » 24 Jul 2021, 17:00

ደበላ= ደበለ= ዲባል ወይም ድበል። ያስኬዳል። ኬሮ=ኬር=ኽይር አረብኛ ነው። ጋሪ በኦሮምኛ ጥሩ፤ ደህና ነው። ከስልጤ/ጉራጌኛም የመጣ ሊሆን ይችላል። ባይለጓል? context ሳይኖር መገመት አይቻልም። ባለሟል፤ ባለ = ያለው= ባለቤት። ባይ ተቃራኒ ባይመጣ ባይሞላ። ባይ ግራ ታጋባለች። ክክክክክክ
ዣንጥላ= ጃንጥላ ጸሃይ= ጠሃይ ሰላሳ= ሸላሻ ማለሳለስ = ማለሳለሻ ባጫ ባሻ? እንሞክራ! ክክክክክክ ሻማ = ጫማ ጨረቃ= ሸራቃ? ቢጫ = ቢሻ? ወይ ጉድ! ሌሎች ምሳሌዎች አምጣ እንጂ ይህን መቀበል ያዳግታል።
ስም ምን ጎሳ፣ ምን ዘር እንደ ሆንክ አያሳይም!
ትክክል። (ብዙውን ጊዜ)።

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Horus » 24 Jul 2021, 21:44

Guest1 wrote:
24 Jul 2021, 17:00
ደበላ= ደበለ= ዲባል ወይም ድበል። ያስኬዳል። ኬሮ=ኬር=ኽይር አረብኛ ነው። ጋሪ በኦሮምኛ ጥሩ፤ ደህና ነው። ከስልጤ/ጉራጌኛም የመጣ ሊሆን ይችላል። ባይለጓል? context ሳይኖር መገመት አይቻልም። ባለሟል፤ ባለ = ያለው= ባለቤት። ባይ ተቃራኒ ባይመጣ ባይሞላ። ባይ ግራ ታጋባለች። ክክክክክክ
ዣንጥላ= ጃንጥላ ጸሃይ= ጠሃይ ሰላሳ= ሸላሻ ማለሳለስ = ማለሳለሻ ባጫ ባሻ? እንሞክራ! ክክክክክክ ሻማ = ጫማ ጨረቃ= ሸራቃ? ቢጫ = ቢሻ? ወይ ጉድ! ሌሎች ምሳሌዎች አምጣ እንጂ ይህን መቀበል ያዳግታል።
ስም ምን ጎሳ፣ ምን ዘር እንደ ሆንክ አያሳይም!
ትክክል። (ብዙውን ጊዜ)።
guest1
ስልጤኛ ቋንቋኮ አንዱ የጉራጌኛ ቋንቋ ነው ። የዛሬ 30 አመት መለስ የሚባል ቆሻሻ ትግሬ የጉራጌን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ተላላኪ ካድሬዎችን ገዝቶ ስልጤን አይደለም ስላለ የተለወጠ ነገር የለም ። በማታቀው አትቀባጥር !
ትክክል ነው ኬር (በወሎ ሕይር ነው ሚባል) ትልቅ የሴም ቃል ነው ። ሴራ ጉራጌኛ ነው ። በግዕዝ ሴራት (ስርዓት) ይባላል፣ በአረብኛ ሸሪዓ ይባላል፣ ህግ፣ ደንብ፣ ኦርደር ማለት ነው ። ሴራ ማለት ተንኮል ማለት አይደለም! ደምብ፣ ስርዓት ማለት ነው ። ኦሮሞችም ሴራ ነው የሚሉት ።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ዘቢዳር ተራራ እና የጉራጌ ውብ ተፈጥሮ

Post by Guest1 » 25 Jul 2021, 13:06

guest1
ስልጤኛ ቋንቋኮ አንዱ የጉራጌኛ ቋንቋ ነው ። የዛሬ 30 አመት መለስ የሚባል ቆሻሻ ትግሬ የጉራጌን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ተላላኪ ካድሬዎችን ገዝቶ ስልጤን አይደለም ስላለ የተለወጠ ነገር የለም ። በማታቀው አትቀባጥር !
አሳቅከን! ክክክክክክክክክክክክክ
በሁሉም ጉራግኛ የሚገኝ ወይም ከስልጤ ብቻ የመጣ ሊሆን ይችላል ነበር። ሁሉም ደበላ የሚሉ ከሆነ ጥሩ። ፓለቲካ ከጀመርን ሊንጨቃጨቅ አይደል! ይቅር ክክክክክክክ
በግዕዝ ሴራት (ስርዓት) ይባላል፣ በአረብኛ ሸሪዓ ይባላል፣ ህግ፣ ደንብ፣ ኦርደር ማለት ነው ። ሴራ ማለት ተንኮል ማለት አይደለም! ደምብ፣ ስርዓት ማለት ነው ። ኦሮሞችም ሴራ ነው የሚሉት ።
ሻሪአ ህግ ደንብ..። ሻሪአ ፍርድ ቤት ሻሪአ የእስልምና ህግ ደንብ ሻሪአ ወደ ማስሪ መዝገበ ቃል ዘው ልበል ክክክክክክክክክክክክክክክክክክክክ
law = qanuun እንደገመትኩት sharia = Islamic law

መኪና መኪናት ፡) ቢንት በናት ነቢይ ነቢያት ሴራ ሴራአት ሴር ሴራት??
ስር ስርኣት = structure/ system/ order
ያም ሆነ ይህ ሴራ ቢያንስ ሁለት ትርጉም አለው። 1. ደንብ 2 ተንኮል (ሴረኛ) 3. ባህላዊ ደንብ? አሁን ትዝ ያለኝ ስነ ስርኣት። ክክክክክክክ አሁን ደግሞ ስርና አባ ገዳ! ወይ ጉድ!! `ና` ከዬት ብቅ አለች? ክክክክ...

Post Reply