Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የቀነጨረው ብልፅግና ፖለቲካዊ አካሄድ!! አማራ እያደረገ ያለውን የህልውና ጦርነት አሸናፊ መሆነ ከፈለገ ....

Post by Wedi » 23 Jul 2021, 19:45

የቀነጨረው ብልፅግና ፖለቲካዊ አካሄድ!!

አማራ እያደረገ ያለውን የህልውና ጦርነት አሸናፊ መሆነ ከፈለገ ከፌደራል መንግስቱም ሆነ ከመከላከያው ራሱን ነጥሎ በራሱ በአማራው ልጆችት የሚታዘዝ ህዝባዊ ሰራዊት አደራጅቶ ሊታገል ይገባዋል!!


****************
በሰልማን መሀመድ የተፃፈ

የቀነጨረው ብልፅግና ፖለቲካዊ አካሄድ
-
ብልፅግና ለአለም አቀፉን ማህበረሰብ የህወሀትን ማንነት አሳያለሁ በሚል የከሰረ ሎጂክ ህወሀት በራያ እና በአፋር የምታደርገውን መስፋፋት ቆሞ እየተመለከተ ነው።

ህወሀት ከምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አንፃር አፋርን በ ዞን 4 ወይም 2 በኩል እንደምትወር ይታወቅ ነበር። እኛም ምንድን ነው የምትጠብቁት ስንላቸው "ትእዛዝ አልተሰጠንም" ሲሉ ቆዩ ይህን ጊዜ 3 ነገሮችን አሰብን

1-- Conversational ጦርነት ለማድረግ ታስቦ ከከተማ እስኪወጡ እየተጠበቀ ነው።
2-- ሰላማዊ ሰዎች የጦርነቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ህወሀት ሙሉ ሀይሉን ከከተሞች እስኪያስወጣ እየተጠበቀ ነው።
3-- ህዝባዊ ድጋፍ ከሚያገኝበት አከባቢ እስከሚወጣ እየተጠበቀ ነው።

👉 የሆነው ግን በተቃራኒው ነው የተፈራው ደርሶ ህወሀት በአፋር ዞን 4 "ያሎ" እና "እዋ" ወረዳን ወሮ ይዞ የትግራይን ባንዲራ በመስቀል የአስተዳዳር መዋቅር ከመዘርጋት አልፎ ተርፎ የግጭት መከላከያ "Buffer Zone" ብለው ከፍተኛ መጠን ያለው ምግብ እና መሳርያ ማከማቸቱን ተያያዘው ይህን ሲያይ የአፋር ህዝብ አጉረመረመ ይህን ጊዜ መንግስት ተብዬው ትላንት እና ከትላንት ወዲያ በ MI-35 ሄሊኮፕተር በታገዘ የመልሶ ማጥቃት ወረዳዎቹን ካስለቀቁ በኋላ ዛሬ ያለ ምንም ውጊያ አከባቢውን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ለምን?

👉 በራያ ግምባር ቆቦ ከተማ ላይ ከድንቢ እስከ አገረ ገነት ፤ ከዲማ እስከ ዞብል ከበባ ሲፈፅም መከላከያው ያውቅ ነበር ፤ በዋጃ በኩል ወደ ቆቦ አቅጣጫ ከ10 ያላነሰ Howitzer መድፍ ሲጠመድ ፣ ZU-23-2 አየር መቃወሚያ ከዋጃ እስከ ሰሌን ዉሃ ሲመላለስ ፣ 122mm BM-21 (በተለምዶ አርባ ጎራሽ የሚባለው) ጫካ ዉስጥ በቅጠል ተሸፍኖ ጥቃት ለመፈፀም ሲጠባበቁ መከላከያው ያውቅ ነበር #አየርሀይሉን ተጠቅሞም እነዚህን መሳሪያዎች ማምከን ይችሉ ነበር ነገር ግን "ትእዛዝ አልተሰጠኝም" እያሉ ቆቦና ወልድያ ቁጭ ብለው ቢራ ሲገለብጡ ነበር። ልክ እንደ አፋር ሁሉ የራያ ቆቦ ወጣት እኛ ራሳችን እንዋጋለን ብሎ ሲነሳ ነው መከላከያ ተብዬው እኛ አለን ብሎ በዞብል በኩል ለአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የከባድ መሳሪያ ሽፋን ማድረግ ጀመረው።
.
የአለም ተስፋ ነኝ የሚለው ብልፅግና ይህን ሁሉ የሚጋጋጠው የህወሀትን ተስፋፊነት ፣ ሴት ደፋሪነት ፣ አውዳሚነት ፣ አፈናቃይነት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳያለሁ ብሎ ነው።
.
እዉነታው ግን ብልፅግና አፋርን እና ራያ ቆቦን ሆነ ብሎ በህወሀት እንዲወረሩ አድርጎ "እዩልኝ ፍረዱኝ" እያለ ቢጋጋጥ ምእራባውያን ለብልፅግና የሚራራ አንጀት አላሳዩም ሌላው ቀርቶ ህወሀት የአለም አቀፉን የጦርነት ህግ (International Humanitarian law) እና አለም አቀፉ የህፃናት መብቶች ስምምነትን (Conversation on right of child) በግልፅ ሲጥስ እየተመለከቱ እንኳን ጥርሳቸውን አልነከሱበትም።
.
በዚህ የብልፅግና ቀሽም የፖለቲካ ጭዋታ ግን ከ54,000 በላይ የአፋር ወንድሞቻችን ተፈናቅለዋል ፣ ከ80 በላይ ሴቶች አፋር ላይ ተደፍረው ደሴ ሆስፒታል ተኝተዋል ፣ ከራያ አላማጣ እና ኮረም ከ20,000 በላይ ሰው ተፈናቅሎ ቆቦ ወልድያ እና መርሳ ገብቷል ፣ በኮረምና በአላማጣ ብቻ ከ90 በላይ ንፁሀን ተገድለዋል።
.
ይህ ሁሉ ዋጋ የሚከፈለው ግን የህወሀትን አረመኔነት አጋለጬ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ከጎኔ አሰልፋለሁ ከሚል መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነታ ያላገናዘበ ከንቱ ምኞት የተነሳ ነው።
.
በሌላ በኩል ኦህዴድ /ODP/ መራሹ መንግስት ይሄን የምእራባውያን regime Change (የመንግስት አገዛዝ ለውጥ) ፍላጎት መረዳት አቅቶት ፤ ህወሀት ለስልጣኑ ስጋት እስካልሆነች ድረስ በትንሽ በትንሹ እየደቆሰ እድሜዋን እንዲቀጥል እንጂ ሙሉ ለሙሉ የመደምሰስ ፍላጎት እንደሌለው እያንዳንዱ እርምጃዎቹ ምስክር ናቸው። ቢያንስ 200 መኪና ሙሉ ወታደር ከመቀሌ ለማስወጣት ምርጫው እስኪያልፍ የጠበቀ አጭበርባሪ መንግስት መሆኑ አይተናል።
.
መፍትሄው
.
አማራ እንደ ህዝብ ከፌደራል መንግስቱም ሆነ ከመከላከያው ራሱን ነጥሎ በራሱ በአማራው የሚታዘዝ ህዝባዊ ሰራዊት እና አለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት። አሁን ባለን ሀይል እየተከላከልን በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ከ 350,000 እስከ 500,000 የሚሆን ጠንካራና ተገዳዳሪ ሰራዊት አሰልጥኖ ብቁ ያድርግ።