ዙሪያውን ከበህ አጥረህ ከረሀብ፣ ከሞትና አስገድዶ ከመደፈር ውጭ አማራጭ ያልሰጠኸው ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቢዋጋህ ሊገርምህ አይገባም። የሰው ልጅ የህልውና አደጋ ሲያጋጥመው fight or flight ያደርጋል። ይሄ human instincts ነው። ሲምፓታቲክ የነርቮች ስርዓት የሚፈጥሩት ስነ ህይወታዊ ምላሽ ነው።
በሱዳን በኤርትራ በአማራ በአፋር በየትኛውም ወሰን መውጫ አሳጥተህ ልትገለው ስትመጣ የሰው ልጅ መኖር ስለሚፈልግ ይፋለምሃል። መሸሻ የለውማ። ከሞት ውጭ ሌላ አማራጭ አልሰጠኸውማ። እጁን የሰጠውን ከገደልክ ፣ ሰላማዊ ዜጋውን ከረሸንክ፣ ሩጠው ያልጠገቡ ህፃናትን ገደል ውስጥ ከወረወርክ ነፍስ ያወቀ ከ7 እና 10 አመት በላይ የሆነ ሁሉ ቢዋጋህ መገረም የለብህም። ለመነቃቃት አደንዛዥ እፅም አያስፈልገውም።
ይህ ጦርነት በቃላት ሊገለፅ የማይችል ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ያመጣ በጅምላ በማበድ የተፈጠረ አሳፋሪ ክስተት ነው። መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስብ በእጅጉ አዝናለሁ ።
Please wait, video is loading...