Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ህውሃት ሴቶችና ህፃናትን ወደ ጦርነት በአደንዛዥ እፅ እያጦዘ እያስገባ ነው የሚለው ክስ ብዙም አላሳመነኝም። ምክንያቱም . . .

Post by sarcasm » 23 Jul 2021, 06:30

ህውሃት ሴቶችና ህፃናትን ወደ ጦርነት በአደንዛዥ እፅ እያጦዘ እያስገባ ነው የሚለው ክስ ብዙም አላሳመነኝም። ሴቶቹ ሲደፈሩ ስለነበር፤ ህፃናቱም ቤተሰቦቻቸው ሲገደሉ ሲያዩ ስለነበር traumatized ሁነው ወደጦርነቱ እየገቡ ይመስለኛል።

ዙሪያውን ከበህ አጥረህ ከረሀብ፣ ከሞትና አስገድዶ ከመደፈር ውጭ አማራጭ ያልሰጠኸው ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቢዋጋህ ሊገርምህ አይገባም። የሰው ልጅ የህልውና አደጋ ሲያጋጥመው fight or flight ያደርጋል። ይሄ human instincts ነው። ሲምፓታቲክ የነርቮች ስርዓት የሚፈጥሩት ስነ ህይወታዊ ምላሽ ነው።

በሱዳን በኤርትራ በአማራ በአፋር በየትኛውም ወሰን መውጫ አሳጥተህ ልትገለው ስትመጣ የሰው ልጅ መኖር ስለሚፈልግ ይፋለምሃል። መሸሻ የለውማ። ከሞት ውጭ ሌላ አማራጭ አልሰጠኸውማ። እጁን የሰጠውን ከገደልክ ፣ ሰላማዊ ዜጋውን ከረሸንክ፣ ሩጠው ያልጠገቡ ህፃናትን ገደል ውስጥ ከወረወርክ ነፍስ ያወቀ ከ7 እና 10 አመት በላይ የሆነ ሁሉ ቢዋጋህ መገረም የለብህም። ለመነቃቃት አደንዛዥ እፅም አያስፈልገውም።

ይህ ጦርነት በቃላት ሊገለፅ የማይችል ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ያመጣ በጅምላ በማበድ የተፈጠረ አሳፋሪ ክስተት ነው። መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስብ በእጅጉ አዝናለሁ ።
Please wait, video is loading...


Abdisa
Member+
Posts: 5754
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ህውሃት ሴቶችና ህፃናትን ወደ ጦርነት በአደንዛዥ እፅ እያጦዘ እያስገባ ነው የሚለው ክስ ብዙም አላሳመነኝም። ምክንያቱም . . .

Post by Abdisa » 23 Jul 2021, 10:40

sarcasm wrote:
23 Jul 2021, 06:30

ህውሃትን በሱዳን በኤርትራ በአማራ በአፋር በየትኛውም ወሰን መውጫ አሳጥተህ ልትገለው ስትመጣ ነፍስ ያወቀ ከ7 እና 10 አመት በላይ የሆነ በአደንዛዥ እፅ እያጦዘ ሁሉ ቢዋጋህ መገረም የለብህም።
:lol: :lol: :lol: :lol:

Post Reply