Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና፣ ስለ ቆቦ እና አካባቢው የዛሬ የተጋድሎ ውሎ

Post by Ejersa » 22 Jul 2021, 18:52

ቆቦ ከተማን እቆጣጠራለሁ ብሎ በቀን ቅዠት የናወዘው ሀይል በአጣዋ ተራራ በተለያዬ አቅጣጫ ሲወር የዋለው ሀይል ረግፏል።

:arrow: በሀሺሽ ተነቃቅቶ በመንጋ የሚመጣውን ሀይል፣ ህዝቡ ከህዝባዊ ሠራዊቱ ጋር ሆኖ ለባንዳ እጅ በማይሰጠው ወኔው ከትላንት ማታ እስከ ዛሬ ማምሻ ድረስ ሲያጭደው ውሎ የተረፈው በጣት የሚቆጠረው የባንዳው ሀይል ሸሽቶ ከዓይን ሲሰወር ተጠናቋል።

:arrow: ተራራ ለተራራ ወደ አራዱም ተጠግቶ ከትላንት ጀምሮ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የነበረው ተቆርጦ የቀረው ሀይል፣ በህዝባዊ ሀይሉ ሲወቀጥ ውሎ፣ በኮማንዶ ተፈጭቶ ታሪኩ ተጠናቋል።

:arrow: በቀዩ ጋሪያ፣ አጠዋ፣ ሀገረ ገነት፣ ቀመሌ እና አካባቢው የወዳደቀው በድናቸው ቀብሮ ለመጨረስ ገና ከ 15 ቀን በላይ ይጠይቃል። ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተዳምሮ ቶሎ መቅበር ካልተቻለ ሌላ ተላላፊ በሽታ እንዳያመጣብን በሚል ህብረተሰቡ ሰግቷል! በህይወት ከመጡት ይልቅ ሬሳቸው እንዳይበክለን አስግቶናል።

:arrow: ከህዝቡ እና ከሠራዊቱ እኛው ጋር አብረው የኖሩ የጁንታው አስተኳሾች ፣ የብሬን ተኳሾች ከእነ ብሬናቸው እንዲሁም የሬዲዮ መገናኙ የያዙ የጁንታው የመረጃ ሰዎች ተይዘዋል!

:arrow: በጣም የሚገርመው አንዱ የእነሱ ደህንነት የነበረ ሰው፣ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ሲደረግላቸው ጥሪውንተቀብሎ አብሮ ሲሰለጥን የነበረ እና በአካውንቱ 12 ሚሊዮን ብር የተገኘበት ነው።

:arrow: የቆቦ እና አካባቢው ህዝብ እንዲህ ‘ድል አደረግን’ አይነት ፉከራ ባይመቸውም፣ በተደጋጋሚ ከሩቅ ሀገር ሆናችሁ ለምትጠይቁኝ ለሁላችሁም መመለስ ስለሚቸገረኝ ብቻ የፃፍኩት መሆኑን መግለፅ እወዳለሁ።

Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ሰበር ዜና፣ ስለ ቆቦ እና አካባቢው የዛሬ የተጋድሎ ውሎ

Post by Ejersa » 22 Jul 2021, 19:11

የቆቦ ኤችአይቪ መቆጣጠሪያ ሴክረቴሪያል ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አፈወርቅ የተባለው ግለሰብ የሬድዩ መገናኛ ይዞ ከባድ መሳሪያዎችን ሲያስተኩስ እና ሲያስደበድብ በተደረገው ህዝባዊ ክትትል ከእነ ሙሉ መገናኛው በቁጥጥር ስር ውሎ እየተመረመረ ይገኛል (እርምጃ ሳይወሰድበትም አይቀርም)። የቆቦ ህዝብ ይሄንን ጁንታ ከያዘ በኋላ የከባድ መሳሪያ ተኩሱ ሙሉ ለሙሉ ቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወልዲያ ከተማ የሽብር ቡድኑ አባላት ሴተኛ አዳሪ መስለው ገብተው ተይዘዋል። ጉዳዮ ሲመረመር የጁንታው የልዩ ኃይል አባላት መሆናቸው የአንዳንዶቹ ተረጋግጧል።

Post Reply