Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የአፋርና የኦሮምያ ልዩ ሃይል በአፋር አካባቢ እንዲሁም የአማራ ልዩ ሃይልና መከላከያ በቆቦና በራያ አካባቢ የተቀናጀ ዘመቻ አድርገው የህወሃትን የመጀመሪያ ዙር የማጥቃት እርምጃ አኮላሽተዋል!

Post by Ejersa » 21 Jul 2021, 18:42

ህወሃት አሁንም ህጻናትን በአሳዛኝ ሁኔታ እያስጨረሰ ነው። እንደ ህወሃቶች ብናስብ ኖሮ የሚደርሱንን ቪዲዮዎች እና ፎቶግራፎች በመልቀቅ የፕሮፓጋንዳው ዘመቻውን ማጦዝ ይቻል ነበር። ግን በህጻናት መርገፍ የሚደሰት ስብዕና የለንም። በሰው እልቂት የሚደሰት ስብዕና ያላቸው ካሉ፣ እነሱ የህወሃት ደጋፊ መሆን አለባቸው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋርና የኦሮምያ ልዩ ሃይል በአፋር አካባቢ እንዲሁም የአማራ ልዩ ሃይልና መከላከያ በቆቦና በራያ አካባቢ የተቀናጀ ዘመቻ አድርገው የህወሃትን የመጀመሪያ ዙር የማጥቃት እርምጃ አኮላሽተዋል። በጣም ያስደሰተኝ ግን ሰራዊቱ ድሉን እንደ ህወሃቶች አስከሬን እያሳያ አለመፎከሩ ነው።

የጦር ዲሲፕሊንና ስብዕና ማለት ይህ ነው። የኢትዮጵያ አለኝታዎች እየተዋጉ ያሉት ለሰው ልጅ ህይወት ደንታ ከማይሰጥ ሃይል ጋር ቢሆንም፣ በ እሱ ደረጃ ባለመውረድ የሞራል የበላይነታቸውን ማሳየታቸው የስልጣኔያቸውን ደረጃ ያሳያል። ይህ የእውነትና የፍትህ ትግል ላይቋጭ አልተጀመረም።

ቄሮ ታሪክ ሠርቷል!
ወያኔን በመጣል ሒደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበረውን ቄሮ ራስ ተፈሪን የሚጠሉ ራስታ አክቲቪስቶችን ጨምሮ ሕዝቅኤል ይሁን ፀጋዬ ወያኔን ለማዳን ተነስ እያሉ ከእንቅልፍ ሲነቁ ቢጮኹ ቢጮኹ ዘወር በሉ አላቸው፡፡ ቄሮ እንዴውም ወያኔን እዚያው ሒደን አብረን እንቀብራለን በማለት 10ሺ ሚሊሻ አዋጥቶ ላከ፡፡ የቁራ ጩኸት ሆነ!!

በአረርቲ፣ በፈንታሌ፣ በሸኖ ወዘተረፈ ከአማራ ክልል ጋር ባለው ድንበር ወሬ እየፈበረኩ ቢቀሰቅሱ የሚሰማ ጠፋ፡፡ ቢቢሲ ኦሮምኛው ሁሉ በመጮህ ማይክራፎን አዋጥቷል፡፡ ቄሮ የሚመራው በኦሮሞ ብልጽግና መሆኑን ገና የተረዱ አልመሰለኝም፡፡


Post Reply