Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና፣ በአፋር ክልል በኩል ትንኮሳ የፈጸመው የአሸባሪው የህወሃት ቡድን ተደመሰሰ!!!!

Post by Ejersa » 21 Jul 2021, 14:43

የአሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በሚባል አካባቢ “ሜይዴይ” በሚል የሰየመው ሃይል የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት የአስታወቀ። የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአለሌ ሱሉላ አካባቢ የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል። በተጨማሪም በቆቦ በከፈተው ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት መከላከያ ሠራዊት በወሰደው የመከላከል እርምጃ ቡድኑ መደምሰሱን ጠቁመው፤ ለውጊያ ያሰማራቸው በርካታ ህጻናት መማረካቸውን ኮሎኔል ጌትነት ተናግረዋል።

መንግስት ለትግራይ ህዝብ በማሰብ የወሰደውን የተናጠል ተኩስ አቁም ቡድኑ የሽብር ተግባር ለመፈጸም እንደመልካም አጋጣሚ እንደወሰደው ጠቅሰው፤ አሸባሪው ሕወሃት ትንኮሳ ከፈጸመ የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጠዋል።

አሸባሪው ሕወሃት ሃይል ትንኮሳ ያለማቆሙን በማየት ለመከላከያ ሰራዊት መንግስት ትዕዛዝ ከሰጠ በቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለማጥፋት ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

Weyane.is.dead
Member+
Posts: 6796
Joined: 19 Oct 2017, 11:19

Re: ሰበር ዜና፣ በአፋር ክልል በኩል ትንኮሳ የፈጸመው የአሸባሪው የህወሃት ቡድን ተደመሰሰ!!!!

Post by Weyane.is.dead » 21 Jul 2021, 15:16

Another defeat for terrorist tplf :mrgreen:
Ejersa wrote:
21 Jul 2021, 14:43

Post Reply